ከደመወዛቸው ላይ በግድ ለአባይ ግድብ መቆረጡን ሰራተኞች ተቃወሙ

 

 በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ከዚህ በፊት ለአንድ ዓመት አቅማችን ሳይፈቅድ ከወር ደመወዛችን ላይ ሲቀቆረጥ ነበር፤ አሁን ግን ካለብን የኑሮ ውድነት የተነሳ አቅማችን አይፈቅድም ስለዚህ ያለፈቃዳችን ሊቆረጥብን አይገባም ሲሉ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ፒቲሽን ተፈራርመው ማስገባታቸው የደረሰን መረጃ አየመንግስት  ሰራተኞች በግድ ለአባይ ግድብ ከደመወዛቸው ላይ እንዳይቆረጥብን ሲሉ ፒቲሽን መልክቷል፡፡

ሰራተኞቹ በቁጥር ወደ 36 የሚደርሱ በዞኑ በተለያየ የመንግስት መስሪያ ቤት የሚሰሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን የተሰጣቸው ምላሽ ግን የለም፡፡ እንደሰራተኞቹ ገለፃ ከሆነ “በአሁን ወቅት በሀገሪቱ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ተከስቶ እያለ ያለፈቃዳችን ለአንድ ዓመት ያህል ተቆርጧዋል፤ አሁን ግን አንችልም፡፡ ስለዚህ አሁንም በኢህአዴግ ካድሬዎች አማካኝነት ያለፈቃዳችን ከደመወዛችን ላይ እንዳይቆረጥ እስከመጨረሻው እንታገላለን” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በተለይ በዞኑ አረካ ወረዳ ያሉ የግብርና ሰራተኞች ድርጊቱን ተቃውመው አቤቱታ ለወረዳው አስተዳደርና ግብርና ፅ/ቤት ቢያቀርቡም አቤቱታቸውን ውድቅ እንዳደረጉባቸው በመግለፅ በጋራ የተስማሙ ሰራተኞች እስከ ፍርድ ቤት ድረስ በመሄድ ክስ እንደሚመሰርቱ አስታውቀዋል፡፡ ስለጉዳዩ ለማጣራት የዝግጅት ክፍሉ ወደወረዳው ዋና አስተዳደር አቶ ደመቀ ደጀኔ ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም አልተሳካም፡፡፡

ይሁን እንጂ በድጋሚ ወደወረዳው ግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ጴጥሮስን ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው “ተቆረጠ የተባለው ደመወዝ ሰራተኞቹ በተስማሙት መሰረት ነው፤ በርግጥ በታህሣስ 2005 ዓ.ም. ሊቀረጥ ሲል ወቅቱ በዓል ስለነበረ እንዳይቆረጥብን ስላሉ ቅሬታቸውን የተቀበልን ቢሆንም ኋላ ከጥር 2005 ዓ.ም. ጀምሮ 2ኛ ዙር እንዲቆረጥ በተስማሙት መሰረት መቆረጥ ተጀምሯል፡፡ በዚህም ዙሪያ አንዳንድ ግለሰቦች ከወር ደመወዛቸው ላይ እንዳይቆረጥ ቅሬታ ያቀረቡ ቢሆንም ከተጀመረ በኋላ ማስተናገድ እንደማንችል ተነጋግረን ተግባብተናል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አረካ ወረዳ በደቡብ ክል ወላይታ ዞን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተወለዱበትና ምርጫ የተወዳደሩበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: