በአፍር ክልል በተከሰተው ርሃብ የሟቾች ቁጥር 22 መድረሱ ተሰማ፡፡ በክልሉ ዞን ሁለት አሚባራ ወረዳን ጨምሮ በዞን አንድ በሚገኙ ኤረርሲ፣ኤልዳዓልና ቢሩ ወረዳዎች የተከሰተው ርሃብ እስካሁን ድረስ ችግሩ ሊቀረፍ ባለመቻሉ የሟቾች ቁጥር እያሻቀበ መሄዱንና ወደሌሎች የክልሉ ወረዳዎችም መዛመቱን ምንጮቻችን በተለይ ለአዲስ ሚዲያ ገልፀዋል፡፡
የአፋር ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የስራ ሂደት ሃላፊ የሆኑት አቶ መሐመድ ያዮ ስለተከሰተው ርሃብ “በአካባቢው ጠረፋማ ወረዳዎች የተከሰተው በዋነኝነት የውሃ እጥረት ቢሆንም የምግብ እጥረቱም አለ፡፡ የክልሉ መንግስት 2 ሚሊዮበሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አፋር ክልል በተከሰተው ርሃብ የሟቾች ቁጥር 22 መድረሱ ን ብር በመመደብ ውሃ በቦቲ ተሸከርካሪ እየወሰደ ለአካባቢው ማኀበረሰብ እያደረሰ ነው፣ ምግብ ግን በበቂ ሁኔታ በመጋዘናች ተከማችቶ የሚገኝ በመሆኑ እየተሰጣቸው ከመሆኑም በተጨማሪ በአካባቢው ያሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም የበሰሉ አልሚ ምግቦችን እያዳረሱ ነው፡፡ በአሁን ወቅት ግን በአካባቢው ዝናብ በመዝነቡ የውሃውን እጥረት ችግር ተቀርፏል “ ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም የእንሰሳቱን የውሃና የምግብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ አጎራባች የአማራ ክልል ወረዳዎች ጥሩ ትብብር እያደረጉልን ቢሆንም አብዛኛው አጎራባች ቦታ ተክሎች ተተክለው በአጥር በመከለሉ ለፀጥታ ችግር ሊፈጥር ይችላል በሚል ማሳሰቡ እንዳልቀረ ገልፀውልናል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ታረቀኝ ፅጌ በበኩላቸው በሶማሌና አፋር በተለያየ ጊዜ ድርቅ ስለሚከሰት በቂ የሆነ የምግብ ክምችት ስላለ ወደስፍራ ተልኳል፡፡ የተከሰተውም ድርቅ እንጂ ርሃብ አይደልም ሲሉ አክለዋል፡፡ የአዲስ ሚዲያ መረጃዎች እንዳመለከቱት ከሆነ በአካባቢው ያለው ርሃብ እየተባባሰ ወደ አጎራባች ወረዳዎችም መዛመቱን ያስረዳል፡፡ አዲስ ሚዲያ ባለፈው በክልሉ ዞን አንድ ቢሩና ኤልዳዓል ወረዳ በተከሰተው ርሃብ የ 8 ሰዎች መሞታቸውን መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን ኤረርሲና አሚባራ ወረዳ የሚባሉ ሌላ ወረዳዎችም ችግሩ በመከሰቱ የሟቾች ቁጥር ወደ 22 መድረሱ ተጠቁሟል፡፡