አንድነት ፓርቲ በይፋ ህዝባዊ የተቃውሞ ንቅናቄ ጀመረ

 

udj logo pic.አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) ፓርቲ ገዥው የፓርቲ ኢህአዴግን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን እየጣሰ ነው በሚል ዛሬ ሰኔ 13 ቀን 2005 ዓ.ም.  ይፋዊ ህዝባዊ ንቅናቄ መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ፓርቲው አዲስ አበባ ቀበና በሚገኘው ዋና ፅህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት”(Millions of Voices For Freedom) በሚል መሪ ቃል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

 የሚሊዮኖችን ድምፅ በመሰብሰብ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጋጨውን የፀረ ሽብርተኝነት ህግ በመቃወም እንዲሰረዝ የተቃውሞ ስምምነት ፊርማ(ፒቲሽን) በማሰባሰብ ለእስር ተዳረጉ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የኃይማኖት ነፃነት ጠያቂዎች እንዲፈቱ እንጠይቃለን ብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀገሪቱ በተለያየ ምክንያት ገጠርና ከተማ ያሉ ከአዲስ አበባና ሌሎች ከተማ ያሉ ዜጎች አለአግባብ ከሚኖሩበት ቀዬ ማፈናቀል በተለይም ዘርን መሰረት በማድረግ ከጉራፈራዳና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ያሉ ነዋሪዎች እና  በልማት ስም ለውጭ ዜጎች መሬት እየተሰጠ እንደ ጋምቤላ ያሉ ዜጎቻችን  መፈናቀላቸው ህገወጥ ተግባር ነው በሚል በማውገዝ የድርጊቱ ፈፃሚዎችን ለፍርድ ማቅረብ እንደተዘጋጀና ለዚህም እንቅስቃሴያችንን የሚደግፉ ኢትዮጵውያን  ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ጠይቋል፡፡   

ፓርቲው ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ ለማድረግ የተለያዩ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን የቀየሰ ሲሆን በዋነኝነትም በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች ህዝባዊ የአዳራሽ ስብሰባዎችን፣የአደባባይ ስብሰባዎችንና የተቃውሞ ሰላማዊ ሰለፍ ማድረግን እንደሚያካትት ተጠቅሷል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ 6 ህዝባዊ ስብሰባዎችን፣ በክልሎች ለመጀመሪያ ዙር ብቻ 10 ስብሰባዎች ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታውቋ፡፡

እንደ ፓርቲው ገለፃ ከሆነ የህዝባዊ ንቅናቄ ዓላማው፡-

1.      የፀረ-ሽብር ህጉ የኢትዮጵያውያንን በርካታ መብቶች የሚገፍ በመሆኑና ከህገ መንግስቱ ጋር የሚፃረር በመሆኑ በሚሊዮኖች የሚቆጠር የተቃውሞ ድምፅ በማሰባሰብ በአስቸኳይ እዲሰረዝ ጥያቄ እናቀርባለን፡፡ የድጋፍ ፊርማ(ፒቲሽን) እናስፈርማለን ፡፡ ይህንንም በሰላማዊ ሰልፍ እንጠይቃለን፡፡ ከዛም የሚሊዮኖችን ድምፅ በመያዝ ወደ ክስ እንሄዳለን፡፡

2.     በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው በገጠርና በከተማ የዜጎች መፈናቀልና የመሬት ቅርምት እንዲቆምና መፍትሄ እንዲያገኝ እንጠይቃለን፡፡

3.     የስራ አጥነትና የኑሮ ውድነት እንዲቀረፍ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንጠይቃለን፡፡

4.     የንግዱ ማኀበረሰብ ውስጥ ፍትሃዊ ውድድር እንዲኖር ፣ ማጥላላትና ማዋከብ እንዲቆም፤ ገዥው ፓርቲ ህግ አውጭ እና ነጋዴ የሚሆንበት ስርዓት እንዲያበቃና የግሉ ሴክተር በልማት ውስጥ ከፍተኛ ሚና እንዲኖረው እንጠይቃለን፡፡ ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሳካት ህዝቡ ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ መኀበራት፣ ሚዲያው፣ በውጭ የሚኖሩና ለሀገር ተቆርቋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ የሀገርን ጥቅም ለማስቀደም የሚፈልጉ የኢህአዴግ አባላት እንዲሳተፉ ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡ በመግለጨው ዙሪያም ከጋዜጠኞች በርካታ ጥያቄዎች ቀርበው ከፓርቲው አመራሮች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: