ጋዜጠኞች እና ብሎገሮች ቶርቸር እንደተፈፀመባቸው ተገለፀ

 

ዛሬ ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ እና ማህሌት ፋንታሁን ከሰዓት በዋለው የአራዳ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡ በፍቃዱ ኃይሉ የውስጥ እግሮ ተደብድቦ ቶርቸር መደረጉን እና አቤል ዋበላም ከፍተኛ ተደጋጋሚ ድብደባ እንደተፈፀመበት ለፍርድ ቤቱ ተከተፈቀደላቸው ቤተሰቦች እና ከተከላካይ ጠበቃቸው አቶ አምሃ መረዳት ተችሏል፡፡ በስፍራው ልክ እንደ ትናንቱ በርካታ ጋዜጠኖች፣ ቤተሰቦች፣ ወዳጆች እና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ቤተሰብ በስተቀር ጋዜጠናም ሆነ ዲፕሎማት እንዲሁም ጓደኞቻቸው ችሎቱን እንዲታዘቡ አልተፈቀደም ነበር፡፡ናግረዋል፡፡ ማህሌት ፋንታሁን በችሎት ላይ ከማልቀስ በቀር ቃላት መናገር እንዳልቻለች በችሎቱ
ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ የተፈፀመውን ቶርቸር ለማስተባበል መሞከሩን እና እነ በፍቃዱ ኃይሉና አቤል ዋበላን ውሸታቸውን ነው፣ እነኚህ የድርጊቱ ዋና አቀናባሪ ናቸው ሲል መናገሩን ከችሎት ታዳሚ ቤተሰብ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ፖሊስ የያዘበትን ምክንያት ሲያስረዳ ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ከምርጫው በፊት አመፅና ሽብር ለመፈፀም 5 ጊዜ ውጭ ሀገር ስልጠና ወስደዋል፣የመገናኛ ብዙኃን መሳሪያ ኮምፒዩተር ገዝተዋል ማለቱን ጠበቃቸው አቶ አምሃ ለመገናኛ ብዙኃን ገልፀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ፖሊስ አሸባሪ ያላቸውን እና ስልጠና የሰጡትን ድርጅቶች ስም እንዲጠቅስ ሲጠየቅ አልጠቅስም፣ አሁን ከጠቀስኩኝ ተባባሪዎቻቸው ያመልጡኛል ሲል ለፍርድ ቤቱ መናገሩን መረዳት ተችሏል፡፡zz
ከዛሬ ጀምሮም የቅርብ ጥቂት ቤተሰብ ብቻ ማዕከላዊ ሄዶ እንዲጎበኛቸው የተፈቀደ መሆኑን በመግለፅ ለእሁድ ግንቦት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የትናንትናው የነ ተስፋዓለም ወልደየስ፣አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬ፣ ዘለዓለም ክብረት፣ ናትናኤል ፈለቀ እና አጥናፍ ብርሃን ችሎት ለቅዳሜ ግንቦት 9 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት መቀጠሩ ይታወሳል፡፡

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: