በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ–የሰበር ውሳኔዎች ዳሰሳ
1. መግቢያ
በአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ዋነኛ ከሚባሉት የአሰሪ ግዴታዎች ውስጥ አንዱ ከስራው ጋር በተያያዘ የሰራተኛውን ደህንነትና ጤንነት ለመጠበቅና ከአደጋ ለመከላከል የሚያስፈልጉትን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ ይገኝበታል፡፡ ግዴታው በአዋጁ አንቀጽ 12(4) ላይ በጥቅሉ የተቀመጠ ሲሆን በአንቀጽ 92 ላይ ደግሞ ግዴታዎቹ በዝርዝር ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ከሙያ ደህንነት፤ ጤንነትና የስራ አካባቢ ጋር በተያያዘ ግዴታ የተጣለው በአሰሪው ላይ ብቻ ሳይሆን በሰራተኛውም ላይ ጭምር ነው፡፡ (አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 13(4) (5) እና አንቀጽ 93)
ሰራተኛው ሆነ አሰሪው በህግ የተጣለባቸውን ግዴታ ቢወጡም ያልተጠበቀ አደጋ መድረሱ አይቀሬ ነው፡፡ በስራ ላይ በሚደርስ አደጋ ሰራተኛው ጉዳት ሲደርስበት የአሰሪና ሰራተኛ ህጉ ጉዳት የደረሰበት ሰራተኛ እንደ ጉዳቱ መጠን እንዲካስ ከሞተም በስሩ የነበሩ ጥገኞች ክፍያ እንዲከፈላቸው በአሰሪው ላይ ግዴታ ይጥላል፡፡
ህጉ በፍርድ ቤቶች ተፈጻሚ ሲደረግ በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ትርጉምና የተፈጻሚነቱ ወሰን፤ የአሰሪው ኃላፊነት፤ የአካል ጉዳት ምንነትና መጠን፤ የጉዳት መጠን ደረጃ እና የካሳ ስሌት በተመለከተ የህግ ትርጉም የሚሹ ጥያቄዎች ይነሳሉ፡፡ ይህ ዳሰሳም የሰበር ችሎት በስራ ላይ የሚደርስ…
View original post 2,979 more words