በባህርዳር በተደረገ የተቃውሞ ሰልፍ የሰው ህይወት ሲጠፋ፤ በአዲስ አበባም ተቃውሞ ተደርጓል

bahr rዛሬ አርብ ታህሣሥ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ባህርዳር ከተማ  ቀበሌ 04 እየተባለ የሚጠራው አካባቢ የሚገኘውን የጥምቀት ባህር ታቦት ማደሪያ መንግስት ለባለሀብት ይሰጣል መባሉን ተከትሎ ህዝቡ ለተቃውሞ አደባባይ ላይ ቢወጣም፤ የመንግስት ፖሊሶች በሰላማዊ ሰለፈኞቹ ላይ በከፈቱት ተኩስ እስካሁን 3 ዜጎች መገደላቸው ሲነገር፣ አዛውንት መነኩሴን ጨምሮ በርካቶች ከመንግስት በተተኮሰ ጥይት መቁሰላቸውን ምንጮች ከስፍራው አስታውቀዋል፡፡ ለተቃውሞ የወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከመነሻው እየዘመሩ ወደ ጥምቀተ ባህር ታቦት ማረፊያ ሲሄዱ የመንግስት ፖሊሶች ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፉን ለማስቆም በሚል በወሰዱት የተኩስ ኃይል እርምጃ አማረ ያዜ የተባለ ወጣት ወዲያው ሲሞት፤ ሌሎች 2 ሰዎችም ሆስፒታል ደርሰው መሞታቸው ተጠቁሟል፡፡  እንደ ባህርዳር ሆስፒታል ምንጮች ጥቆማ ከሆነ የሟቾች ቁጥር ከ3 ወደ 5 እንዳሻቀበ የተገለፀ ሲሆን፤ ከ8 ያላነሱ ቆስለው የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደነበር አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል አስተዳደር የቤተ ክርስቲያን ንብረት የሆነውን የታቦት ማደሪያ ከፊሉን ለመንገድ ማስፋፊያ ቀሪውን ለባለሃብትና  ለጥቃቅንና አነስተኛ ሱቆች መስሪያ እንዲነጠቅ ማዘዙን ተከትሎ በቤተ ክርስቲያኗ በተደረገ ጥሪ የተቃውሞ ሰልፉ መካሄዱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ ይሁን እንጂ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉን ለማስቆም ፖሊስ በወሰደው ሰልፍ በወጣው ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡ በመጨረሻም የአማራ ክል መስተዳደርና የባህርዳር ከተማ መስተዳደር በጋራ በተሸከርካሪ መኪና በመንቀሳቀስና ባርዳር በሚገኘው በአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት በተለይም በሬዲዮ በጥምቀተ ባህር ታቦት ማረፊያ ስፍራው ሊካሄድ የታሰበው የመንግድ ማስፋፊያ ቀርቷል ሲል ማወጁ ተጠቁሟል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፌደራል መንግስት በበኩሉ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቴቪ) ባሰተላለፈው ዜና በተፈጠረው ችግር አንድ ሰው ብቻ መሞቱን ሲያምን የሌሎች ሟቾችንና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን በተመለከተ ያለው ነገር የለም፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ገለፀ ከሆነ የሟቾችና ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው እንደሚጨምርና በሰልፉ ላይ ከነበሩት መካከል ከ30 የማያንሱ ሰዎች በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ስፍራ ለእስር መወሰዳቸውን እማኞች ለአዲስሚዲያ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ የፌደራል መንግስት በበኩሉ ቀደም ሲል በ2፡00 ሰዓት የዜና እወጃው ላይ ካስተላለፈው ዜና በተቃራኒ ስራው ሊከናወን የነበረው ከኋይማኖቱ አባቶች ጋር በተደረገ መግባባትና ስምምነት እንደሆነ እና የጥምቀተ ባህር ታቦት ማረፊያን እንደማይነካ ከየትኛው ደብርና ገዳም እንደሆኑ ያልተገለፁ የተወሰኑ ቀሳውስትን ምስል በማሳየት ስራው ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ በዜና እወጃው በሰልፉ የተገኙትንም ሆነ ጉዳት የደረሰባቸውንም ሲወነጅል ተሰምቷል፡፡

munirk mosque pበተያያዘ ዜና በአዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው ኑር (ቤኒ) መስኪድ ህዝበ ሙስሊሙ ድንገት በመንግስት ላይ ተቃውሞ ማሰማቱ ታውቋል፡፡ ለዓመታት የቆየው ህዝበ ሙስሊሙ የመንግስት በኃይማኖት ጣልቃ ገብነት በሰላማዊ መንገድ በተከታታይ ያሰማ የነበረውን ተቃውሞ ለተወሰነ ጊዜ ረገብ ያለ ቢመስልም ዛሬ አርብ ታህሣሥ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. የተለመደ ሰላማዊ ተቃውሞውን ማሰማት ቀጥሏል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ መንግስት በኋይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም ከጥር 1 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው ሰላማዊ ተቃውሞ ምላሽ ባለመገኘቱ ዛሬም ድንገት ሰላማዊ ተቃውሞ መቀጠሉ ታውቋል፡፡ መንግስት ከሙስሊሙ ማኀበረሰብ ተወካዮቻቸው ጋር ለተወሰነ ጊዜ ሲደራደር ቆይቶ በመጨረሻ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቹን በሙሉ አስሮ ክስ መመስረቱንና እስካሁንም እልባት እንዳልተገኘለት አይዘነጋም፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: