አያት የመኖሪያ ቤቶች ስራ ድርጅት በሊዝ ወስዶ መሠረቱ ወጥቶ ያለቀ ቦታ ለኢሊሌ ሆቴል ተወሰነ

ታምሩ ጽጌ

መሠረቱን ለማውጣት 3.7 ሚሊዮን ብር በላይ እንደወጣበት ተገልጿል

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ ከኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል ወረድ ብሎ የሚገኘውን፣ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አያት አክሲዮን ማኅበር በሊዝ የወሰደውና መሠረቱ ወጥቶ ያለቀ ቦታ፣ ፊት ለፊቱ ለሚገኘው ኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል በፍርድ ቤት ውሳኔ ተሰጠ፡፡

 

አዲስ አበባ፣ ካዛንችስ  ከአያት ተነጥቆ ለኤሊሊ ሆቴል የተሰጠው ቦታ

አዲስ አበባ፣ ካዛንችስ ከአያት ተነጥቆ ለኤሊሊ ሆቴል የተሰጠው ቦታ

ከ20 በላይ ክሶች ተመሥርቶባቸውና ጥፋተኛ ተብለው 11 ዓመታት የእስርና የገንዘብ ቅጣት ተወስኖባቸው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አያሌው ተሰማ ከፍተኛ ባለድርሻ የሆኑበት አያት አክሲዮን ማኅበር፣ ቦታውን በሊዝ የወሰደው ከአራት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ ስፋቱም 1,696 ካሬ ሜትር ነው፡፡ አክሲዮን ማኅበሩ ቦታውን በሊዝ የወሰደው ባለ16 ፎቅ ለመኖሪያና ለቅይጥ የንግድ ሥራ ሕንፃ ለመገንባት ነበር፡፡

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቦታውን በሊዝ ያስተላለፈው ለልማት መሆኑን በመግለጽ፣ አያት አክሲዮን ማኅበር ምንም ዓይነት ግንባታ አላካሄደም በማለት በሊዝ አዋጁ የተፈቀደው የመጠበቂያ ጊዜ እንዳለፈ አስታውቆ ካርታውን ማምከኑም ተጠቁሟል፡፡

የኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት አቶ ገምሹ በየነ ቦታው ከሆቴላቸው ፊት ለፊት በቅርበት ላይ መሆኑን በመግለጽ፣ መሰጠት ያለበት ለመኪና ማቆሚያ (ፓርኪንግ) ለእሳቸው መሆኑን ለክፍለ ከተማው በማመልከታቸው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱም ተገልጿል፡፡ የሆቴሉን ባለቤት አቶ ገምሹንና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደርን በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት የከሰሰው አያት አክሲዮን ማኅበር፣ ለመሠረት ማውጫ ከ3.7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንዳወጣበትና ካርታው ከመምከኑ በፊት ሊነገረው ሲገባ፣ በድብቅ ማምከኑ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ሲከራከር ከርሟል፡፡

ጉዳዩን ሲመረምር የከረመው ፍርድ ቤቱ ማኅበሩ ቦታውን በተነጠቀ ወይም ካርታው በመከነ በ15 ቀናት ውስጥ ለአስተዳደሩ የቦታ አመላለስ ይግባኝ ሰሚ ጉባዔ ማቅረብ እንደነበረበት አስታውቋል፡፡ ያንን ሳያደርግ ወደ ፍርድ ቤት መምጣቱ  (ክስ መመሥረቱ)  ሕጉን ያከበረ አካሄድ አለመሆኑን በመጠቆም፣ 1,696 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ለኢሊሌ ኢንተርናሽናል ሆቴል መሰጠቱ ተገቢ መሆኑን በውሳኔው አስታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ሪፖርተር ጋዜጣ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: