እነ ሀብታሙ አያሌው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ጠየቁ

• አቶ ዳንኤል ሺበሽ በእስር ቤት በደል እየተፈጸመበት መሆኑን ተናግሯል

Political prisonersበፌደራል አቃቤ ህግ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩና በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የቀረበባቸውን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኖላቸው ሳለ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እየተከታተሉ የሚገኙት እነ ሀብታሙ አያሌው የይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሱላቸው ጠይቀዋል፡፡
በዚህ መዝገብ ይግባኝ የተጠየቀባቸውና ሰብሳቢ ዳኛው፣ ዳኛ ዳኜ መላኩ ከችሎት እንዲነሱ የጠየቁት ተከሳሾች አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሽ እና አቶ አብርሃም ሰለሞን ናቸው፡፡
የይግባኝ መልስ ሰጭዎቹ ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት እንዲነሱላቸው ለመጠየቃቸው ምክንያታቸውን ዘርዝረው በጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በዋናነት ዳኛው ‹‹…ችሎቱን እየመሩበት ካለው አግባብ አንጻርም ሆነ በህግ ከሚጠበቅባቸው ገለልተኝነት አንጻር እርሳቸው እንደ አንድ ዳኛም ሆነ እንደ ሰብሳቢ በሚሳተፉበት ችሎት ትክክለኛ ፍትህ እናገኛለን ብለን ስለማናምን›› የሚል ነው፡፡
እነ ሀብታሙ አያሌው ነሀሴ 15 ቀን 2007 ዓ.ም የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት በጻፈው እግድ ምክንያት እስካሁን በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡
በሌላ በኩል ቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኘውና በዚሁ መዝገብ የተካተተው የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ በእስር በሚገኝበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በደል እየተፈጸመበት እንደሆነ ለችሎቱ ገልጾዋል፡፡ አቶ ዳንኤል ለፍርድ ቤት ክርክር ያዘጋጀው ወረቀት ተቀምቶ እንደተቀዳደደበትና በአስተዳደሩ ከፍተኛ ዛቻም እየተፈጸመበት መሆኑን ለችሎቱ ተናግሯል፡፡ ‹‹እዚህ ቤት አስክሬንህ ነው የሚወጣው›› እያሉ ይዝቱብኛል ያለው አቶ ዳንኤል፣ ‹‹ከሌላው እስረኛ እኩል የማልታየው ለምንድነው? እኔስ ዜጋ አይደለሁምን?›› ሲል ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ መልስ ሰጭዎቹ ባቀረቡት የሰብሳቢው ዳኛ ይነሳልን አቤቱታ ላይ ብይን ለመስጠት ለታህሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ዘገባው የነገረ ኢትዮጵያ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: