በኦሮሚያ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፤ በመንግሥት የኃይል እርምጃ የተገደሉ ዜጎች ቁጥርም ከ140 በላይ ደርሷል

በኦሮሚያ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ አሁንም በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ ነው፡፡ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዝግተዋል፡፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተገደሉት ዜጎች ቁጥር ከ140 በላይ መድረሱን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት የኃይል እርምጃ ከሰላማዊ ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ከተሳተፉት እና በቤታቸው እንዲሁም በመንገድ ላይ ሲጓዙ የተገደሉትን 140 ዜጎችን ጨምሮ ከ350 በላይ ሰዎች ሲቆስሉ ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በእስር ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

በተለይ የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በጅምላ እየወሰዱት ባለው እስር በድጋሚ የታሰሩት የኦፌኮ/መድረክ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ልጅ የሆነው እና በአዳማ ዩኒቨርስቲ የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ የሆነው ናዖል በቀለ ገርባን ጨምሮ በርካታ ተማሪዎች ከሚማሩበት የትምህርት ተቋም ተይዘው መታሰራቸውም ተሰምቷል፡፡

oromoprotestsህዝባዊ ተቃውሞው አሁንም በተለያዩ ከተሞች በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ በወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምስራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ፣ በአርሲ ፣ በምስራቅ ሸዋ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ ነው፡፡ በመንግሥት የሚገደሉ፣ የሚታሰሩና የሚጎዱ ዜጎችም ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
የኦፌኮ/መድረክ ዋና ፀሐፊ አቶ በቀለ ነጋዓ እስካሁን በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከደረሰባቸው ተደጋጋሚ ማስፈራሪያና ዛቻ በኋላ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ የተንቀሳቃሽ ስልካቸው ተነጥቆ ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርጎ እስካሁንም በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ህዝባዊው ተቃውሞ ባለፈው ህዳር 2008 ዓ.ም. አዲሱን የአዲስ አበባ እና የኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ትግበራን በመቃወም መጀመሩ ይታወሳል፡፡

መንግሥት በበኩሉ ለተቃውሞ የወጡትን ፀረ-ህዝብ፣ ፀረ-ሰላም፣ አሸባሪዎች ብሎ መወንጀሉን እና ህዝባዊው ተቃውሞውን በቁጥጥር ስር አውየዋለሁ በሚል ተደጋጋሚ መግለጫ ቢሰጥም፤ ተቃውሞው በያዝነው ሳምንት በተለያዩ የሀገሪቱ ኦሮሚያ ክልሎች ተጠናክሮ መቀጠሉ የታወቀ ሲሆን፤ በተለይ በሐረርጌ አካባቢ ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ እና ሐረር የሚወስዱ ዋና መንገዶች በተቃውሞው ተዘግተው እንደነበር ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: