• የጋዜጣው ጽሑፎች፣ «መንፈሳዊ ኮሌጆቹ በአጠቃላይ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው» አይሉም
• በጋዜጣው አጻጻፍ አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት ዝግጁዎች ነን
• ጉዳዮቹን እንድናስረዳና የተፈጠረውንም ችግር ለመረዳት የውይይት መድረክ ይዘጋጅልን
• በተለያየ መንገድ እንደጠየቅነው፣ በአካል የመወያያ ዕድል ማጣታችን በእጅጉ ያሳዝነናል
• ለሚታረም ነገር እርምት መውሰድና ስናጠፋም ይቅርታ መጠየቅ የአገልግሎታችን መርሕ ነው
* * *
• ሰዎች እንደመኾናችንና ልንሳሳት ስለምንችል፣ በማንኛውም ደረጃ ተወያይተን የሚታረም ነገር ካለ አስፈላጊውን እርምት መውሰድ እና በትክክል ጥፋት እንዳጠፋንም ስንረዳ ይቅርታ መጠየቅ አንዱና ዋነኛው የአገልግሎታችን መርሕ ነው፡
• በሀገራችን የተከሠቱትን ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት ኹሉም አካል በየዘርፉ በሚረባረብበት በዚኽ ወቅት፣ ትልቅ ሓላፊነት ያለባት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባትና ልጆች እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎችን በመጻጻፍ መጠመዳችን በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡
• ሕግ አውጥቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ የሰጠን የቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በማኅበሩ አገልግሎቶች ላይ አኹንም እየተፈጠሩ ያሉት ዕንቅፋቶች እንዲታዩልንና አስፈላጊው እርምት እንዲደረግልን በታላቅ ትሕትናና አክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዚኽ በታች ይመልከቱ)
ምንጭ፡- ሐራ ዘተዋሕዶ ፣ https://haratewahido.wordpress.com/2016/02/29