(አዲስ ሚዲያ) ወጣት አስቴር ስዩም የታአሰረችው ከሰኔ 25 ቀን 2007 ዓ ም ጀምሮ ትኖርበት ከነበረው ጎንደር ከእስር በተጨማሪ በርካታ ዜጎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን መቃወም ተከትሎ በደህንነት ኃይሎች ታፍነው አዲስ አበባ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ለወራት ከፍተኛ ስቃይና እንግልት ከደረሰባችው ሴቶችና ወጣቶች መካከል አንዷ ናት።
አስቴር ስዩም
የቀረበባትም ክስ ህዝባዊ አመፅ ማነሳሳት ሙከራ በሚል የፌደራል አቃቤ ህግ ክስ እንደነበር ያገኘው መረጃ አመልክቷል።
አስቴር ታፍና በመወሰድ ስትታሰር የ3 ወር ህፃን ልጇን ለወላጅ እናቷ ትታ የነበረ ቢሆንም፥ በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ታስራ እያለ ወላጅ እናቷ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል።
ይሁን እንጂ፤ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፥ የአድስ አበባ ልደታ ምድብ ችሎች ከ 23 ወራት እስርና የፍርድ ሂደት በኋላ ግንቦት 14 ቀን 2009 ዓ ም የ 4 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶባታል።