የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሀገር ውስጥ የከተሞች ጉብኝት ንግግሮች ከወዲሁ ተቃውሞን አስነስቷል

(ዳጉ ሚዲያ) አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ። በቅርቡ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በመተካት የገዥው ኢህአድግ ሊቀመንበር እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙት ዶ/ር አብይ አህመድ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞችን በመጎብኘት ንግግር አድርገዋል።

Dr Abiy Ahmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን መንበር በተረከቡ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ በኦጋዴን ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጅግጅግ፥ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ፥ በትግራይ ክልል መቀሌ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት በፓርቲያቸው ኢህአድግ እና በተለያዩ ክልል ባሉ የፓርቲያቸው አጋር ፓርቲዎች ከተወጣጡ አካላት ጋር ንግግር አድርገዋል።

በንግግር ጥበብ በአንደበተ ርትዑነታቸው በርካታ አድናቂዎችን ያፈሩትና በገሪቱ ብዙ ለውጥ ያመጣሉ በሚል ተስፋ የተጣለባቸው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በበዓለ ሲመታቸው ወቅት ሀገሪቱ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ እንደሚሰሩና የነበሩ አለመግባባቶች በሰላም መፍትሄ እንዲያገኙ እንደሚሰሩ ቃል መግባታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ በሀገር ውስጥ ያሉ የተወሰኑ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፥ የሲአኢክ ማኅበራት ተወካዮች ፥ የተወሰኑ የሀገር ሽማግሌዎች፥ ታዋቂ ግለሰቦች እና የኃይማኖት መሪዎችን በብተመንግሥት በጥራት የእራት ግብዣ ማድረጋቸውም ታውቋል። ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ከተረከቡ 20 ቀናት ቢሆናቸውም ከንግግር ባለፈ ቃል ከገቧቸው ነገሮች ውስጥ አንዳችም ተግባራዊ ያደረጉት ነገር እንደሌለ በማስታወስ በደጋፊዎቻቸው ሳይቀር እየተተቹ ይገኛሉ።

በትግራይ ክልል መቀሌ መነበራቸው ጉብኝት ከተሳታፊዎች ስለወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ በተያያዝ ለተነሳላቸው ጥያቄ ጉዳዩን የልማት በተለይም የውሃ፥ የትምህርት ቤቴ እና የጤና ጉዳይ እንጂ ዳያስፖራው በማኅበራዊ ሚዲያው እንደሚለው አይደለም፤ ለዚህም ዳያስፖራው ሀገሩ ገብቶ የህዝቡን ሁኔታ ቢያውቅ የበለጠ ይረዳ ነበር የሚል እደምታ ያለው ንግግራቸው የአማራ ተወላጆችን እና የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ደጋፊዎችን አስቆጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሀገሪቱን በትረ ሥልጣን በተረከቡ ማግስት ባደረጓቸው የተለያዩ ከተሞች ጉብኝት ለታዳሚው ህዝብ በተለያየ የአካባቢው ቋንቋዎች ንግግር ማቅረባቸው በበርካቶች ዘንድ አድናቆትና ድጋፍ የተቸራቸው ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ መጠቀም የነበረባቸው በሕገ መንግሥቱ የሰፈረውን የፌደራሉን ቋንቋ ነበር በሚል ም ትችትን አስተናግደዋል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: