በፌደራል አቃቤ ህግ በሽብር ወንጀል ተከሰው ለበርካታ ወራት ታስረው የነበሩት የዋልደባ መነኮሳት ከእስር ተፈቱ። መነኮሳቱ ከዋልደባ ገዳም ታፍነው ለበርካታ ወራት ታስረው ጉዳያቸው በፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሲታይ ቆአይቶ በመጨረሻም ክሳቸው ተቋርጦ ተፈተዋል።
መነኮሳቱ ልደታ ፍርድ ቤት ሳሉ
መነኮሳቱ በአዲስ አበባ በሚገኘው ቃሊቲ ፌደራል ወህኒ ቤት ባሉ የጥበቃና የደህንነት አባላት ተደጋጋሚ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈፀምባቸው እንደነበር አብቱታዎቻቸውን ለፍርድ ቤት ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።
መነኮሳቱ አባ ገብረኢየሱስ ኪዳነ ማርያም፥ አባ ገብረሥላሴ ወልደኃይማኖት፥ መርጌታ ዲበኩሉ እንዲሁም አቶ ለገሰ ወልደሐና፥ አቶ ሀብታሙ እንየው ጨምሮ 114 የፖለቲካ እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ከታሰሩበት ወህኒ ቤት ተለቀዋል።
በመጨረሻም፤ መነኮሳቱ ከእስር በመፈታታቸውን ፈጣሪን በማመስገን አሁንም በርካታ ዜጎች ፍርድ ቤት እንኳ ሳይቀርቡ ለዓመታት በውህኒ ቤት ያሉ እንዳሉ እና ሀገሪቱ ኢትዮጵያ እና ኃይማኖታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እስር ላይ እንዳሉ በማስታወስ ሁሉም ከእስር ነፃ ካልወጡ ራሳቸውን ከእስር እንደተፉ እንደማይቆጥሩ ተነግረዋል።