Category Archives: Social and Culture

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥፋተኛ መሆኑን አመነ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን  ምንያህል ተሾመ  ሰኔ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.  ከቦትስዋና ብሄራዊ  ቡድን ጋር በተደረገው ጨዋታ መሰለፉ ስህተት እንደሆነ  አመነ፡፡ ፌዴሬሽኑ ብሄራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ  አቻው ጋር ከመጫወቱ በፊት ችግር ስለመፈጠሩ ከፊፋ ደብዳቤ ደርሶት እንደነበርም ገልጿል፡፡

 

efifa
የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለችግሩ ተጠያቂ ያላቸውን ግለሰቦች ዝርዝርም ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረት የብሄራዊ ቡድኑ ቡድን  መሪ አቶ ብርሀኑ ከበደ ፣ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ፣ ረዳት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ፣ የቡድኑ ተጨዋች ምንያህል ተሾመ  እና የፌዴሬሽኑ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች ጥፋተኛ ተብለዋል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በጥፋተኞቹ ላይ በቅርቡ  ተገቢውን  ቅጣት በመውሰድ የቅጣት ውሳኔውን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ፌዴሬሽኑ በተፈጠረው ችግር ከፍተኛ ሀዘን እንደተሰማው ገልፆ መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የቡድኑ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው በተፈጠረው  ስህተት የተሰማቸውን  ሀዘን  ገልፀው ፥ ከማዕከላዊ  አፍሪካ  ሪፐብሊክ ጋር ለሚካሄደው ጨዋታ ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ጨዋታውም  አሸንፈን ወደ አለም  ዋንጫ  እንደምንሳተፍ   እርግጠኛ ነኝ ብለዋል ፡፡

በፊፋ ህግ መሰረት ተገቢ ያልሆነ  ተጨዋችን  ማሰለፍ  በጨዋታው  የተገኘውን  ነጥብ  እና  ተጨማሪ  የገንዘብ  ቅጣት እንደሚያስጥል ይታወቃል፡፡

የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ንብረት እያወዛገበ ነው

1ሚ. ብር አበድሬአቸዋለሁ የሚል ድርጅት ክስ ሊመሰርት ነው የአዋሣው ቤታቸው ተሸጦ ስም መዛወሩ እያነጋገረ ነው

Afewerk

እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ንብረት እያወዛገበ ነው፡፡ አርቲስቱ በሕይወት ሳሉ አንድ ሚሊዮን ብር አበድሬአቸዋለሁ የሚል ድርጅት ለክስ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱን ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ሎሬት አፈወርቅ በህይወት ሳሉ የስዕል ሥራዎቻቸውን፣ ቪላ አልፋንና ሙሉ ንብረታቸውን ለመንግስት ማውረሳቸውን ተከትሎ፣ መንግስት ንብረቱን ለመረከብ እንቅስቃሴ ጀምሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡ የእኚሁን ታላቅ አርቲስት ንብረት ለማጣራትና ለመመዝገብም ከፍርድ ቤት፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከሙያ ባልደረቦች የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ ምዝገባና ቆጠራ ቢጀመርም ፍፃሜ ሣያገኝ ተቋርጧል፡፡ ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ በህይወት ሣሉ የአክሲዮን ባለ መብት ለመሆን አንድ ሚሊዮን ብር ወስደዋል በሚል የአርቲስቱን ስዕሎች ይሸጥ በነበረ አንድ የማስታወቂያ ድርጅት ክስ ሊመሰረት መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

ጉዳዩ በፍርድ ቤት እልባት እንዲያገኝ ለኮልፌ ምድብ ችሎት ተመርቶ እየታየ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮች፤ ለጊዜው የንብረት ምዝገባና ቆጠራው መቋረጡን ገልፀዋል፡፡ በአዋሣ ከተማ የሚገኘውና በሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ስም የተመዘገበው ቤት በቀድሞ ባለቤታቸው አማካኝነት መሸጡን የጠቆሙት ምንጮች፤ የቤቱ ስም የተዛወረበት አሠራር ሕጋዊነት አነጋጋሪ እየሆነ መምጣቱን ጠቁመዋል፡፡ በሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ስም በለንደንና በስኮትላንድ ባንኮች ያለ ገንዘብ እንዲመለስ ጥረት እየተደረገ ሲሆን በተለያዩ አገራት ያሉ ስዕሎችና ንብረቶችን ለማስመለስም እየተሞከረ ነው ተብሏል፡፡ የአርቲስቱ ንብረት ካለባቸው አገራት መካከልም ንብረቱንና ገንዘባቸውን ለመመለስ ፈቃደኛ የሆኑና በመመለስ ሂደት ላይ የሚገኙ እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ ቪላ አልፋ፤ በኮሚቴዎቹ ሲከፈት በሺዎች የሚቆጠር ፓውንድ በካዝናቸው ውስጥ መገኘቱንና ይህም በንብረት ዝርዝር ላይ ተመዝግቦ መያዙን ምንጮች ገልፀዋል፡፡ በፍርድ ቤት ጉዳይ የተቋረጠው የሎሬት አፈወርቅ ንብረት ቆጠራና ርክክብ መዘግየት በንብረቱ ላይ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል የጠቆሙት ምንጮች፤ እጅግ ውድ ዋጋ ያላቸው

ስዕሎቻቸውና የአርቲስቱ የመኖሪያ ቤትና የስዕል ስቱዲዮ የሆነው ቪላ አልፋም የመበላሸት አደጋ አንዣቦበታል ብለዋል፡፡ የሎሬት አፈወርቅ ተክሌ የቀብር ሥፍራ ምንም አይነት የማስታወሻ ሐውልት ሣይሰራበት መቅረቱን የጠቀሱት ምንጮች፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የቀብራቸው ሥፍራ ሊጠፋ ይችላል የሚል ሥጋት መፈጠሩን ገልፀዋል፡፡

Written by መታሰቢያ ካሣዬ- http://www.addisadmassnews.com/

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?

”ጎዳና ቤቴ’

ሰኔ 25/2012 እአአቆጣጠር  በቢቢሲ ድህረ ገፅ ላይ በወጣ አንድ ዘገባ መሰረት ኢትዮጵያ በአመት 5ሺህ በላይ ሕፃናት በማደጎነት ወደ አሜሪካ  ብቻ እንደሚሄዱ  እና አሜሪካ ከዓለም ላይ በማደጎነት ከምትወስደው ሕፃናት ኢትዮጵያውያን ሕፃናት ከ አምስቱ አንዱ እንደሆኑይገልፃል።(http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474)

አዲስ አበባ ብቻ ዛሬ ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ መግብያ ያጡ ”ጎዳና ቤቴ” ብለው አንቅልፍ በጣላቸው ቦታ ክልውስ ብለው የሚተኙ ሕፃናት ይኖሩባታል።ይህ የሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ግዴለሽነት የመነጨ እንጂ ከድህነታችን ብቻ የሚመስለው ካለ ለመሳሳቱ እማኝ ላቅርብ።
ሕፃናት አሳዳጊ የሚያጡት ባብዛኛው የርስበርስ ጦርነት ሲኖር ወይንም ሰላም በተናጋበት ጊዜ ነው።ኢትዮጵያ ግን ጎዳና የወጡት ሕፃናቶቿ የበዙት በአንፃሩም ቢሆን ጦርነቱ ከቆመ ጊዜ ጀምሮ ነው ለምን?
በ 1969 ዓም በዚያድባሬ ሱማሌ ወረራ ሳቢያ ብዙ ሕፃናት አባት እናታቸውን አጡ።ሀገሪቱ በወቅቱ ገንዘብ የላትም።ምዕራባውያን ፊታቸውን አዙረውባት ነበር።ግን ሕፃናት ጎዳና አልተጣሉም ይልቁንም ኃላፊነት የተሰማቸው ኮለኔል መንግስቱ በ 16 ወራት ውስጥ የሕፃናት አምባ እንዲገነባ አድርገው በአንድ ጊዜ ከአምስት ሺህ ሕፃናት በላይ የሚይዝ ትልቅ የሕፃናት ማሳደግያ በአፍሪካ በግዙፍነቱ (በውቅቱ) እና በአቅሙ ቀዳሚ  ሆኖ ተገንብቷል። ኢህአዲግ መንግስት ከሆነበት ጊዜ  ጀምሮ ሲያዳክመው ቆይቶ በ 1990 ዓም ተዘጋ። ኢህአዲግ ወያኔ የነበረውን አስፋፍቶ ሕፃናትን ከጎዳና ኑሮ ከማዳን ይልቅ ሕፃናትን በማደጎነት እየሸጠ በአንድ ሕፃን በትንሹ 25ሺህ ዶላር መሰብሰብ እና ወደኪሱ  ማስገባቱን መረጠ።

ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?

ዛሬ ኮለኔል መንግስቱ እንደጀመሩት ቢቀጥል ኖሮ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሕፃናት በተማሩበት እና ከጎዳና ኑሮ በዳኑበት ነበር። ሃቁ ይህ ነው።አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ የተሰቀለው ቢል ቦርድ እና ኢቲቪ በአቶ መለስ የሞቱ ሰሞን ከዜና አንባቢው ጀርባ አቶ በለስ ጣታቸውን ወደ ሕፃናት ሲዘረጉ ያሳያል።ግን  እንዴት ነው አቶ መለስ የኢትዮጵያ ሕፃናት አባት የሚባሉት? በምን መስፈርት? ሕፃናቱን ጎዳና ወድቀው እሳቸው በሚያልፉበት መንገድ በወታደሮቻቸው ስለገፏቸው ነው?ወይንስ የሕፃናት አምባን ስለዘጉላቸው? ነው ወይንስ በአስር ሺዎች በማያውቁት ባእዳን እጅ እንዲያድጉ ስለሸጧቸው። ‘መሸጥ’ የሚለው ቃል ለቀረበው ዕቃ ወይም ሰው አልያም ሕፃናት ገንዘብ ከፍሎ ሕፃኑን መውሰድ የሚለውን ትርጉም እስከያዘ ድረስ መሸጥ ከሚለው ቃል የትሻለ ሊገኝ አይችልም።

ቅዳሜ ጧት

ከአምስት አመት በፊት በ 2001ዓም አንድ ቅዳሜ ጧት ወደ ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም 45 ሰዎችን አሳፍሮ አንድ መለስተኛ አውቶቡስ መመናንን ይዞ መንገድ ላይ ነበር።በመንገድ ላይ በእድሜ ጎልማሳ ካህን ስለገዳሙ ታሪክ ይናገራሉ።በአንክሮ በመገረም ነበር የምንሰማው።እውነተኛ ታሪኩ ይህ ነበር።

555833_4741247050817_2127754364_n

” አቡነጎርጎርዮስ የዝዋይ ገዳም መስራች አንድቀን የመንፈስ ልጆቻቸውን እያስተማሩ ኮለኔል  መንግስቱ ከአዋሳ ሲመጡ ጎራ ይላሉ።ወደ ገዳሙ ውስጥ ሳይገቡ ገና አጥሩን ሲመለከቱ በረጅሙ ታጥሮ ይመለከቱ እና ‘ይሄ መነኩሴ ይህን ይህል ቦታ አጥሮ አገሩ ታድያ ምን ተረፈ’ ይሉ እና አንዱን ወታደር አቡነ ጎርጎርዮስን እንዲጠራቸው ይልኩታል። አቡነ ጎርጎርዮስ መልክቱ እንደደረሳቸው ‘አሁን ትምህርት ላይ ነኝ ደግሞስ ፈላጊ ይመጣል እንጂ ተፈላጊ እንዴት ይሄዳል?’ ብለህ ንገረው ብለው መልሰው ይልካሉ።ኮለኔል መንግስቱ እንዲህ አይነት ድፍረት በመስማታቸው ምንም ሳይሉ ወደ አዲስ አበባ ይመለሳሉ። በቀጣዩ ቀናት አቡነ ጎርጎርዮስ ኮለኔል መንግስቱን ቅሬታቸውን ለመንገር ይመጣሉ።ቅሬታቸው ሌላ ነበር።እንደገቡ አቡነ ጎርጎርዮስ በቁጣ ”ለመሆኑ ሕፃናት አምባ የምታሳድጋቸው ልጆች አምላካቸውን ካላወቁ አውሬ እንደሚሆኑ ታውቃለህ?” ይሉታል ይደነግጣል። ”ምን ይደረግ?” ይላቸዋል።”ለእኔ ፍቀድልኝ እኔ የማደርገውን አውቃለሁ ” ይሉታል። ከድጋፍ ደብዳቤ ጋር ይልካቸዋል።

አቡነ ጎርጎርዮስ በህፃናት አምባ ውስጥ የቅዱስ ሚካኤል ታቦት አስይዘው በግቢው ውስጥ ለሕፃናቱ ቤተክርስቲያን ሰሩላቸው።ብዙ በስነምግባራቸው የታነፁ ሕፃናትን አፈሩ። በቀን በሚልዮን ብር ለጦርነት ታወጣ የነበረች ሀገር እንዲህ ልጆቿን ታሳድግ ነበር። ዛሬ የጎዳና ተዳዳሪ ሲበዛ መንግስት ኃላፊነት አይወስድም።ሕፃናቱን ለመሸጥ ግን ቢሮዎችን በየቦታው ባእዳን እንዲከፍቱ አርጎ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ አደረጋቸው። ቢቢሲ ከላይ በጠቀስኩት ቀን ላይ ባወጣው ዘገባ ላይ እንዲህ ይላል።
”International adoption is big business in Ethiopia and the country accounts for almost one in five international adoptions in the US, but how ethical is the process?” http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-18506474
”በኢትዮጵያ የማደጎ ሕፃናትን ወደውጭ መላክ የንግድ ሥራ ሆኗል።ይህም ወደአሜሪካ ከመላው አለም ከሚገቡት ውስጥ ከአምስቱ አንዱን እጅ ይይዛሉ።ነገር ግን ይህ እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?” በማለት ይጠይቃል። እውነት እንዴት ሞራላዊ ሂደት ሊሆን ይችላል?
ግን ከኮለኔል መንግስቱ እና ከአቶ መለስ ለኢትዮጵያ ሕፃናት አባት በመሆን ፋውንዴሽን ሊመሰረትለት የሚገባው ማነው?
ይህንን በ ኮለኔል  መንግስቱ የተመሰረተውን ታሪካዊ የሕፃናት አምባ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፊልም ይመልከቱ እና ኃላፊነት የሚሰማው መንግስት ስጠን በሉ።

ምንጭ ፡- ከጉዳያችን ብሎግ የተወሰደ

ኸረ ዛሬም በአጃቢዎች እየተጠበቁ ነው !

ብስራት  ወልደሚካኤል

afrosonb@gmail.com

አቶ መለስ ዜናዊ በህይወት እያሉ የጥበቃ አጃቢዎችን ብዛት ላየ የምር የሚሞቱ አይመስልም ነበር፡፡ ግን የማይሞት የለ እንዲሉ አቶ መለስ ስንቱን ኢትዮጵያዊ በግፍ ጨካኝ አመራራቸው ሲያስጨንቁ 21 ዓመታትን ካሳለፉ በኋላ ነሐሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም. መሞታቸው በአምላኪዎቻቸው ይፋ ሆነ፡፡ ይሁን እንጂ አምላኪዎቻቸው ነሐሴ ሞቱ ቢሉንም እሳቸው የሞቱት ሐምሌ 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ኢትዮጵያዊያንን ካስጨነቁ በኋላ በቤልጂየም ብራሰልስ ሴይንት ሉክ ሆስፒታል በሞትና በህይወት መካከል  ከተጨነቁ በኋላ ፓርቲያቸው ይቆዩልን ቢሉም ሳይሰናበቷቸው በጨበጣ ያለፈቃዳቸው የላይኛው ጥሪ በልጦ ላይመለሱ ሄደዋል፡፡ ያኔ ግን ትዝ ይላችኋል? ነሐሴ 15 ቀን 2004ዓ.ም. አቶ በረከት ስምዖን  የአቶ መለስን መሞት በጠዋቱ ሲያረዱን  “ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ባጋጠማቸው ኢንፌክሽን ትናንት ሐምሌ 14 ቀን 2004ዓ.ም.ከምሽቱ 4 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል” አሉ፡፡ ግን አቶ በረከት  የሰውየውን መሞት ለማርዳት የፈጠኑ አልመሰሏችሁም? በድናጋጤ እንዳንሞት እንኳ አላዘኑልንም፤ ያው ኢህአዴግ በተፈጥሮው “ግልፅ, ዴሞክራትና ዘመናዊ አስተዳደርም” አይደል? ለዛ ነው ቶሎ የነገሩን ፤ቢዘገየም ብራቮ! አቶ በረከት ብያለሁ፡፡

የአምባገነኑን ጨካኝ ለኢህአዴግዎች ቅዱስ የሆኑት መሪ ሞታቸውን ዓለም ይወቅልን፣ ነፍሳትም ያንቡ፣ ህዝቡም ይሰናበታቸው፣.…ተብሎ እምባ ማይታክታት ሀገር ህዝቡ ከነጭፍሮቻቸው በፈፀሙት የግፍ አገዛዛቸው 21 ዓመታትን ማልቀሱ ሳያንሰው ሞታቸው ከተነገረ ጀምሮ  13 ቀናት ምድሯን በጥቁር ልብስ ገበያ ካደሩ በኋላ ምክንያቱ ሳይታወቅ አስከሬኑ ለህዝብ ሳይታይ ባማረው የውጭ ሳጥን ነሐሴ 27 ቀን 2005ዓ.ም ግብዓተ መሬታቸው  አዲስ አበባ በሚገኘው መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ግቢ ተፈፅሟል፤ ወዳጆቻቸው እንዳሉን ከሆነ፡፡ ምክንያቱም ደጉ ለሀገሪቱ ህዝብ አላስ…የሆኑት አምባገነን መሪያችንን አስከሬን እንደነ ክቡር  አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ፣ የዓለም ሎሬት አፈወርቅ ተክሌና አቡነ ጳውሎስ አስከሬኑ ለህዝብ አልታየማ! ባለማየታችንም ቢሆን ቅር አይለንም፣ አንኮነንም…”ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” አይደል የሚለው ቃሉ? ደግሞስ እንኳን የእሳቸውን መሞት ቀርቶ የሀገራችንን ዕድገትስ በነገሩን ብቻ ያልኖርንበትን ሳናይ  11 በመቶ አድገናል ሲሉን እያመንን አይደል?….፤ታዲያ እሳቸው ከኢትዮጵያ በምን ያንሳሉ?…ምክንያቱም በህይወት እያሉ እራሳቸውን ብቻ ተቋምም፣ሀገርም ፣ህዝብ አርገው ይቆጠሩ ነበርና፡፡

አሁን ግን ግብዓተ መሬታቸው የተፈፀመበት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን በወጣቶች ስፖርትና መዝናኛ(ወወክማ) አቅጣጫ ባለው መካነ መቃብራቸው ቦታ ግዙፍ የማያልቁ ትላልቅ ሻማዎች እየበሩ(እሳቸው ግን ተፍተዋል) በሁለት የጦር መሳሪያ በታጠቁ መከላከያ ሰራዊት ዘወትር ይጠበቃል፡፡ እንዴት ነው ነገሩ? ሰውዬው ሞተውም ይፈራሉ እንዴ? ወይ አምባገነን ለካ ሞቶም አያርፍ…..!

ሌላው ያስገረመኝ ጉዳይ ቤተክርስቲያን ሊሳለምና ፀሎቱን ሊያደርስ የሚሄድ ምዕመን ድንገት ዓይኑን አዲስ ወደ ሆነበት መካነ መቃብር አቅጣጫ መልከት ቢያደርግ አስከሬኑ ያረፈበት አጠገብ በተጠንቀቅ የተቀመጡት የመከላከያ ሰራዊቶቹ  ግልምጫና ፍጥጫ ምን እሚሉት ነው? ደግሞስ ለሙት የሚደረገው ጥበቃ እና እኒያ ግዙፍ አራቱ ሻማዎች በጀት ከማን ይሆን የሚሸፈነው? መቼም ጉድ እማይሰማ የለ! ከሀገሪቱ በጀት ነው እንዳይባል፣ አያደርጉትም አይባልማ! እንዲህ ከሆነማ በቁማቸው ሀገሪቷንና ህዝቡን የጋጡት የኢህአዴግ ቱባ ቱባ ባለስልጣናት ሲሞቱ እንዲህ የሀገር በጀት የሚባክን ከሆነ ምን ቀረን…?

ግድ የለም ጎበዝ!…ከእንግዲህ ሞተውም በዛ ክፉ መንፈሳቸው ሀገር ማተራመስና ማራቆት ስለማያቆሙ አትሙቱብን፣ በቁማችሁ ጋጡና ጨርሱን ብለን እንፀልይላቸው ይሆን ወይስ…..?  ኦ…ኦ…የረሳሁት ትዝ አለኝ!…ግን መከላከያ ሰራዊቱ የሞተ አስከሬን እንዲጠብቁ የተደረጉት የአቶ መለስ አምላኪ ኢህአዴጋዊያን  አውጠተው የሙዚየሙን ስራ ያስተጓጉላሉ ተብሎስ  ይሆን? የሀገሪቱ ካዝና ይመስል ምናልባት ሼም ስለማያውቁ  ሊሆን ይችላል፤ አለበለዚያ ሰውዬው  በምድር ለሰሩት ግፍ ወደላይኛው ቅጣት እንዳይሄዱ/እንዳያርጉ ታስቦስ ይሆን? ኸረ መላ በሉን ጎበዝ! ሞተውና ተቀብረውም ስፍራው በመከላከያ ጦር መጠበቁ ለምን ይሆን?

በቅርብ ቀን የኢህአዴግን ፍፃሜ ምንነት በግልፅ የሚያሳየን “የኢህአዴግ ፍፃሜ” የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ ለአንባቢያን እየመጣ ነው፡፡ መቼም በኢቴቪ የሰለቸንን የኢህአዴግ ፕሮፖጋንዳ ምስጢርንም ከዚሁ መፅሐፍ ስለሚያገኙ እንዲያነቡት ተጋብዘዋል፡፡

733766_225902407550725_1016857317_n