Tag Archives: Ethiopia

ማስፈራሪያና ዛቻ ያልተበረዘ ንፁህ መረጃን ለህዝብ ከማድረስ አይገታኝም !!

ከበትረ ያዕቆብ

mycountryethiopia@gmail.com

OLYMPUS DIGITAL CAMERAዉድ የሀገሬ ልጆች ከሁሉም በማስቀደም እንደምን ናችሁ ? ደህና ናችሁ ? እንዴት ናችሁ ? ስል የጠበቀ ሰላምታየን ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ መቼም እዚች ላይ ምነዉ ሰላምታ አበዛህሳ እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ምክንያቱም “አሸባሪ ፣ ፀረ ሰላም ፣ አክራሪ”… ወዘተ የሚል ተለጣፊ ስም ለሀገር ወዳድና ለመብታቸዉ መከበር ድምፃቸዉን ለሚያሰሙ ሁሉ በጅምላ እየተሰጠ ዜጎች በሀሰት በሚወነጀሉበት ሀገር ፤ በእያንዳንዷ ቀን እንደ መልካም ተግባር መሰል ዜጎችን ጠልፎ ለመጣል የተንኮል ወጥመድ ሲጠመድ በሚዋልበት ሀገር ፤ በየስራ ቦታዉ ፣ በየመዝናኛ ስፍራዎች ፣ በየመንገዱ… ሲያነፈንፉ የሚዉሉ የወሬ ‹‹ተኩላዎች›› እንደ አሸን በፈሉበት ወቅት ፣ ንፁህ ዜጎች በግዳጅ ያልፈፀሙትን ኃጢያት እንዲናዘዙ በሚገደዱበት ሀገር ፤ በልቶ ማደር በከበደበት ጊዜ አጥብቆ ደህንነትን መጠየቁ ተገቢ ነዉና፡፡ እንደዉም ከዛም በዘለለ ብዙ ቢባል እንኳ የሚበዛ አይመስለኝም፡፡ መቼም እዚህ ላይ ለማለት የፈለኩት ለሁሉም ሰዉ ግልፅ ይመስለኛል፡፡ የሆነ ሆኖ ለሰላምታ ያህል ይህን ካልኩ ወደ ፍሬ ሀሳቤ ልለፍ፡፡

እንደሚታወቀዉ በአለማችን ለጋዜጠኞች አደገኛ ከሚባሉት አገራት መካከል አንዷ አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ እንደዉም ግንባር ቀደሟ፡፡ እርግጥ ከላይ ከጠቀስኩት በመነሳት ለምን ለጋዜጠኞች ብቻ ትላለህ ፤ ጠቅለል አድርገህ ለዜጎቻቸዉ አደገኛ ከሚባሉት አገራት መካከል አገራችን ኢትዮጵያ ግንባር ቀደሟ ናት አትልም? ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ያን ያልኩት በዋናነት በፅሑፌ ላነሳዉ ወደ ፈለግኩት ርዕሰ ጉዳይ በቀጥታ ለመንደርደር ያመቸኛል በሚል እንጅ ትክክል ናችሁ፡፡ እናም እንደሚታወቀዉ በሀገራችን ጋዜጠኞች ለብዙ ችግርና ፈተና ይዳረጋሉ፡፡ ለምሳሌ ከሚደርስባቸዉ መጠነ ሰፊ የሚባል ማስፈራሪያ ፣ ዛቻና ወከባ ባሻገር በእብሪተኛና ኃላፊነት በጎደላቸው የደህንነት ሰዎች ሰብዓዊነት በጎደለዉ ሁኔታ ይደበደባሉ ፣ ያለ ምክንያት ለሰዉ ልጅ ቀርቶ ለእንስሳት እንኳን ወደማይመቹ ‘እስር ቤቶች’ ይወረወራሉ ፣ ሲልም ከዚያ የከፋ ነገር ይፈፀምባቸዋል፡፡ እዚህ ላይ ሙያዊ ኃላፊነታቸዉን መወጣታቸዉ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በእነ እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ እና ርዕዮት አለሙ ላይ የተፈፀመባቸዉ ያለዉ ዘግናኝ ግፍ እንዲሁም በእነ ተመስገን ደሳለኝ ላይ እየደረሰ ያለዉ መከራ ለምሳሌነት ተጠቃሽ ነዉ፡፡ እንግዲህ እኔም ይህችን አጭር ፅሑፍ ቢጤ ለመፃፍ ምክንያት የሆነኝ ከዚህ ከሀገራችን መንግስት ጋዜጠኞችን የማሳደድ አባዜ ጋር በተያያዘ በእኔም ላይ በደህንነት አባሎች እየተፈፀመብኝ ያለ ወንጀል ሲሆን ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያዉቀዉ መልካም ነዉ በሚል እሳቤ አንዳንድ ነገሮችን ለመጠቆም ወድጃለሁ፡፡

ዉድ የሀገሬ ልጆች እንደሚታወቀዉ ከዚህ በፊት በደረሱብኝ የተለያዩ ዛቻዎችና ማስፈራሪያዎች ምክንያት ለደህንነቴ በመስጋት ከምሰራበት መንግስታዊ ካልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ስራዬን ለመልቀቅና መኖሪያዬን ከባህር ዳር ከተማ ወደ አዲስ አበባ ለመቀየር ተገድጄ ነበር፡፡ ይህንንም ያደረግኩት ከባህር ዳር ይልቅ አዲስ አበባ አንፃራዊ ሰላም ያለበትና ለደህንነቴም ቢሆን የተሻለ ነዉ በሚል ተስፋ ነዉ፡፡ እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በዋናነት መሰረቱን ጣሊያን ሀገር ላደረገ www.assaman.info  ለተባለ ድህረ-ገፅ የምሰራ ስሆን ፤ በተጨማሪም በፈቃደኝነት ሀገርን የማገልገል አላማ በማንገብ  www.thedailyjournalist.comበተባለ ድህረ-ገፅ እና እንደከዚህ ቀደሙ የግሌ በሆነዉ www.ethiopiahot.wordpress.com(personal Blog) ላይ እየሰራሁ እገኛለሁ፡፡ ከዚህም ባሻገር ፅሑፎቸን እንደ http://ecadforum.comላሉ የተለያዩ ኢትዮጵያዊ ድህረ ገፆች በመላክ እንዲወጡ አደርጋለሁ፡፡

ይሁንና ምንም እንኳን እዉነቱ የምሰራዉ ስራ ለሀገርና ለወገን የሚበጅ ቢሆንም ሰሞኑን እየደረሱብኝ ያሉት ማስፈራሪያዎችና ዛቻዎች ከበፊቶቹ እየተለዩና እየከበዱ የመጡ ሲሆን ፤ ከእስራት ወደ ግድያም ተሸጋግሯል፡፡ የምንደዉለዉ ከማዕከላዊ ነዉ የሚሉት እነዚህ የደህንነት ሰዎች በፅሑፎቼ ላይ ተገቢ አስተያየት ከመስጠት እና እንዲስተካከል ከመጠየቅ ይልቅ በአምባገነን ስሜት አፋቸዉን ሞልተዉ መፃፍ አቁም ስንልህ ባለማቆምህ “ልናስወግድህ” ነዉ በማለት እየዛቱብኝ ይገኛሉ፡፡ የዛቱትንም በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ እየገለፁ ይገኛል፡፡ 

ለምሳሌ በጥር 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ በ7፡51 ሰዓት ላይ በተደረገልኝ የስልክ ጥሪ፡- “ደጋግመን እንድታቆም ነግረንህ ነበር፡፡ አንተ ግን እንኳን ልታቆም እንደዉም ብሶብሃል፤ባለፉት ግዚያት በተደጋጋሚ ይከሰስ ተብሎ አስፈላጊ ዶክመንቶችን በመሰብሰብ አንዳንድ ዝግጅት ስናደርግ ነበር፡፡ በተለይም ከኦጋዴን ጋር በተያያዘ ፅፈህ በለቀቅከዉ ፅሑፍ እና ከዚያ ወዲህ በለቀቅካቸዉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን በቅርቡ ቶርቸር ምናምን በሚል ሌላ ፅሑፍ ለቅቀሀል፡፡ ስለሆነም አሁን አንተን ማስወገድ የሚለዉን የተሻለ አማራጭ ሁኖ አግንተነዋል፡፡ በማንኛዉም ዓይነት ዘዴ አንተን ማስወገድ፡፡” የሚል ከበድ ያለ ዛቻ ሰንዝረዉብኛል፡፡

በድጋሚ በጥር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ከቀኑ በ10፡05 ሰዓት ላይ በተደረገልኝ ሌላ የስልክ ጥሪ ደግሞ፡- “ባለፈዉ የነገርኩህን አቅልለህ ወይም እንደ ቀልድ እንዳላየኸዉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡… ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር የመጨቃጨቂያ ጊዜ የለንም፡፡  …የስራህን ዋጋ በቅርቡ ታገኛለህ…፤ ተዘጋጅ!!” በማለት ዝተዉብኛል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ዛቻዎችና ማስፈራሪያዎች በተጨማሪ እነዚህ የደህንነት ሰዎች የተለመደዉን “ሽብርተኛ” የሚል የሐሰት ካባ በሙያ ጓደኞቼ ላይ እንደደረቡት ሁሉ በእኔ ላይም ለመደረብ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ፡፡ በተደጋጋሚ “እያንዳንዷን ስራህን እናዉቃለን ፣ ለማን እንደምትሰራም እንዲሁ ፣ ስለአንተ ከበቂ በላይ ማስረጃ አለን…”  እያሉ ለሐሰት ዉንጀላ መንገድ እየጠረጉ ይገኛል፡፡ በተለይም በጥር 20 ቀን 2005 ዓ.ም. በተደረገልኝ የስልክ ጥሪ ላይ ከንግግራቸዉ በግልፅ እንደተረዳሁት የኢህአዴግ መንግስት “አሸባሪ” ሲል ከፈረጀዉ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጭ ግንባር(ኦብነግ) ጋር ምንም ሚያገናኘን ነገር በሌለበት ሁኔታ ግንኙነት ያለ ለማስመሰል እየሞከሩ ነዉ፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ የግንባሩ በሆነዉ ድህረ-ገፅ ላይ የወጡትን ፅሑፎቼን ለግንኙነቱ እንደ አንድ ማሳያ እንደሆኑ በተዘዋዋሪ እየጠቀሱ ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ ግልፅ ማድረግ የምፈልገዉ እነዚህ ፅሑፎች እኔ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጭ ግንባርን ለመርዳት በማሰብ የፃፉኳቸዉ ወይንም እኔ በቀጥታ ለግንባሩ  የላኳቸዉ አለመሆናቸውን ነዉ፡፡ ይልቁንም የግንባሩ ጋዜጠኞች ከተለያዩ ድህረ-ገፆች ላይ ራሳቸዉ እንደማንኛውም የዓለማችን ጋዜጠኛ የወሰዷቸዉ ናቸዉ፡፡ ሆኖም ግን በእኔ ስለተፃፉና ስሜ ስለተጠቀሰባቸዉ ብቻ ያንን ሊሉ ችለዋል፡፡ ይህም ደግሞ ድህረ-ገፆችና የዜና አዉታሮች መረጃን እንዴት እንደሚቀባበሉ ጠፍቷቸዉ ያደረጉት ነዉ የሚል እምነት የለኝም ፣ እንዴትስ ድህረ-ገፆችን በማናለብኝነት ሲዘጉ ፣ ሲከፍቱ ፣ ኢሜሎችን ያለ ይለፍ ቃል (Password) ሲጎረጉሩ ለሚዉሉት የኢህአዴግ ‹‹ተኩላዎች›› ይህን መረዳት ያዳግታቸዋል?

ዉድ የሀገሬ ልጆች! እኔ ለማንም ኢትዮጵያዊ መጥፎ የምመኝ ፣ የሀገርን ደህንነት ለርካሽ ጥቅም ስል አሳልፌ የምሰጥ ፣ ሽብር ፈጣሪ… አይደለሁም፡፡ እኔ ሀገሬን ፣ ወገኔን የማፈቅር ፣ ለሀገሬና ወገኔ ለሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም ፣ ፍቅርና ብልፅግናን ሌት ተቀን የምመኝና የምሰራ አንድ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነኝ፡፡ እኔ አቅሜ በቻለዉ መጠን በሙያዬ ሀገሬንና ወገኔን ለማገልገል ሙሉ በሙሉ ፍቃደኛ የሆንኩና ለዚያም የምንቀሳቀስ ተራ ሰዉ ነኝ፡፡ እነርሱ ሊያስመስሉ እንደሚሞክሩት አይነት ወንጀለኛ ሳልሆን መብቱን በአግባቡ ለመጠቀም የሚታትር ንፁህ ዜጋ ነኝ፡፡ ይህን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በግልፅ እንዲረዳልኝ እፈልጋለሁ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እነዚህ ኃላፊነት የጎደላቸው የደህንነት ሰዎችም ሆኑ አለቆቻቸዉ አንድ ሊያዉቁት የሚገባ ቁም ነገር አለ እላለሁ፡፡ ይህም እኔንና መሰል ምስኪን ጋዜጠኞችን አሳዶ በመደብደብ ፣ በማሰር ወይም በመግደል የመንግስትን ጉድፍ ከአለም ህዝብ አይን መሸሸግ ከቶም አይቻልም፡፡ እንኳን እነርሱ እንደሚያስቡት ቀርቶ ጊዜያዊ መፍትሄ ሊሆንም አይችልም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ መሰል እርምጃቸዉ የሚያመልኩትን ፓርቲያቸዉንም ሆነ የገነቡትን አምባገነናዊ አገዛዝ የባሰ መጥፎ ገፅታን እያላበሰዉና በሀገር ዉስጥም ሆነ በዉጭ ተቃዉሞን እያስከተለበት ይሄዳል፡፡ ይሄም ዞሮ ዞሮ የሚፈሩትን ዉድቀት ያስከትላል፡፡ እዚህ ላይ ምናልባት እነ እስክንድር ነጋን በማሰራቸዉ እየደረሰባቸዉ ያለዉ የፖለቲካ ክስረት እንደ ምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ደግሞም ዱላዉና እስሩ የበለጠ እልህን ይፈጥር ይሆናል እንጅ እኔንም ሆነ የሙያ አጋሮቼን ከምንወደዉ ሙያችን ሊያቆራርጠን ፍፁም አይቻለዉም፡፡

ዉድ የሀገሬ ልጆች! ሀገር እንድታድግ ወይንም በማይጨበጥ ተስፋ ኢህአዴግ አስመዘግበዋለሁ የሚለዉ አይነት የኢኮኖሚ ብልፅግና ታስመዘግብ ዘንድ ሁሉም የሀገሪቱ ዜጋ በየተሰማራበት የሙያ ዘርፉ የሙያዉን ስነ ምግባር አክብሮ በትጋት ሊሰራ ይገባል፡፡ ጋዜጠኛዉ ፣ ዶክተሩ ፣ ኢንጅነሩ ፣ ነጋዴዉ ፣ መምህሩ ፣ ፖለቲከኛዉ… ሁሉም፡፡ ይህ የግሌ አመለካከት ሳይሆን የአለም ህዝብ በጋራ የተስማማበት እዉነት ነዉ፡፡ ከዚህ የእዉነት ሀ፣ ሁ በመነሳትም ባሳለፍኩት የስራ ጊዜያቶች በምወደዉ የጋዜጠኝነት ሙያዬ ለሀገሬ ይበጃል ያልኩትን በታማኝነት ለማድረግ ሞክሬያለሁ፡፡ አሁንም እየሞከርኩ እገኛለሁ፡፡ ለወደፊቱም ሙያዬ ያልተበረዘ ንፁህ መረጃን ለህዝበ ማድረስ እንደመሆኑ ያንን ከማድረግ ምንም አይነት ማስፈራሪያም ሆነ ዛቻ እንደማያቆመኝ በእርግጠኝነት ለመናገር እወዳለሁ፤ ይህንንም እናንተ ዉድ የሀገሬ ልጆች በግልፅ እንድታዉቁልኝ እፈልጋለሁ፡፡

 

Opposition Political Parties Showing Reservation to the Ethiopian National Transitional Council (ENTC)

By Betre Yacob.

Ethiopian National Transitional Council (ENTC)Opposition political parties in Ethiopia are said to have been showing reservation to the Ethiopian National Transitional Council (ENTC), which has been working to overthrow the Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) tyrannical regime that has been abusing, oppressing and exploiting its own people.

One ENTC leadership told this writer in an interview that although opposition political parties working in Ethiopia expressed their support to the Council (ENTC) — most of them have so far shown reservation to work together.

“When we formed ENTC, we had anticipated the joining of the other political groups under this umbrella. Hence the structure of the organization was designed in a bi-cameral way where organizations will have one wing with their voices and votes, and the public will be on the other end. To that effect, written invitations were sent to all the organized groups that are struggling for change in Ethiopia. Unfortunately, this did not work out as the opposition parties had some reservations even though they expressed support to the council”, he said.

The leadership, who said that the opposition political parties needed time to feel comfortable to rally behind the idea and join this new organization, said that —recognizing the problem —the general assembly of the council had passed a resolution in July 2012— to mobilize the public and, in the mean time, work closely with the other political parties and civic organizations.

“Accordingly, we are working together with other political parties in defining the roadmap and target around the alternative that ENTC believes yields success. Along with several other political parties and civic organizations, we have formed the “Joint Coordinating Committee of Ethiopian Democratic Forces” to help strengthen the cooperation. This committee is comprised of subcommittees and task forces which help develop the working relationships between the organizations”, he said.

The leadership also said that studying the past history of Ethiopian politics and assessing current political situations in Ethiopia, ENTC believed that along with the struggle for freedom— it was not too early to start thinking and planning of what was beyond.

“We believe that creation of an all-inclusive transitional government will help us have a framework and readiness that is required if the regime falls. In addition to that, having this institution beforehand will force the disparate political groups to work under one umbrella strengthening the struggle, hence two birds with one stone. Currently ENTC is calling for the formation of such an institution”, he explained.

Different political analysts argue that the Ethiopian National Transitional Council (ENTC) has been the first ever and wise development in the Ethiopian opposition politics. They are optimistic that the council will strengthen the Ethiopian struggle for freedom by bringing opposition political parties —which have been so fragmented.

The Ethiopian National Transitional Council (ENTC) was officially established in Dallas, USA on July 3, 2012, by Ethiopians from all over the world. It has been given the objective to overthrow the EPRDF regime and facilitate a peaceful transition of power to opposition political parties through participatory, fair, and democratic election.

Since its establishment, the council have done so many successful activities. For instance, it has managed to organize and mobilize Ethiopians that were part of the silent majority at the grassroots level in different local councils / chapters from all over the world including some in Africa. In addition, it has been doing meaningful works to influence western governments, which are the backbone of the tyrant regime in Ethiopia, to stand for the demand of the Ethiopian people.