የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች የመንግስትን ማጭበርበር አጋለጡ
ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ዛሬ ጥቅምት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. ከCPJ ፣ ከዶሃ ዓለም አቀፉ የሚዲያ ነፃነት ማዕከል እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ተወካዮች ጋር በአዲስ አበባ ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል ተገናኝተው ተወያዩ፡፡ ጋዜጠኞቹ ለ3፡30 ሰዓት ያህል ስለኢትዮጵያ ሚዲያ አፈና፣ ስለጋዜጠኛች መከራ፣ እስርና ስቃይ እንዲሁም ስደት ከነነባራዊው ሁኔታ በዝርዝር ከነ ምክንያቱ ሰፊ ምክክር ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ትናንት ጥቅምት 29 ቀን 2006ዓ.ም በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የተደረገው የአፍሪካ ሚዲያ ፎረም ላይ ነፃ ጋዜጠኞች እንዳልተጋበዙ እና የመንግስት ደጋፊዎች እንዲሳተፉ መደረጉን እንዲሁም ከነፃ ሚዲያ ከ3 ያልበለጡ በእንግሊዘኛ የሚዘጋጅ ሚዲያ አዘጋጆች በሌላ አካል እንዲሳተፉ መደረጉን፣ መንግስት ሚዲያውን ከማፈኑ በተጨማሪ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ፣ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውን ጨምሮ 6 ጋዜጠኖች ከጋዜጠኝነት ስራ ጋር በተያያዘ መታሰራቸው እና በተለያየ ጊዜም የተለያዩ ጋዜጠኞች እየታሰሩ እንደሚፈቱ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም ዙሪያ በአፍሪካ ሚዲያ ፎረም ላይ ስለተጋበዙ ስለኢትዮጵያ ጋዜጠኞች እና ሚዲያ አፈና የተሳሳተ ዘገባ እንዳያቀርቡ እውነታውን ከ15 ያላነሱ ጋዜጠኞች አብራርተዋል፡፡ በዚህም ጋዜጠኖቹ የመንግስትን ማጭበርበር በማጋለጣቸው፤ ተወካዮቹ እውነታውን ለዓለሙ ማኀበረሰብ እነምደሚያቀርቡ እና ይህንንም በይበልጥ ለለጋስ ሀገሮች እንደሚያሳውቁ በማረጋገጥ ውይይቱ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡
ሰበር ሰሚ ችሎት የነ አቶ በቀለ ገርባን ይግባኝን እንደማያይ አስታወቀ -እነ አንዱዓለም አራጌም የፊታችን ሰኞ ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኦፌኮ-መድረክ ምክትል ሊቀመንበር እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ላይ እና የኦፌኮ ሌላው አመመራር ወጣት ኦልባና ሌሊሳ የጠየቁትን ይግባኝ ዛሬ ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. በዋለው ችሎት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የህግ ስህተት የለውም በሚል ሰበር ሰሚ ችሎቱ ይግባኙን ውድቅ አድርጎታል፡፡ አቶ በቀለ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት በፌደራሉ አቃቤ ህግ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል 8 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ሲሆን ፤ ይህን በመቃወምፈደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቀው ነበር፡፡
ጠቅላይ ፍርድ ቤቱም በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተወሰነውን የ8 ዓመት እስራት ወደ 3 ዓመት ከ7 ወር ዝቅ ማድረጉይታወቃል፡፡ አቶ ኦልባና ሌሊሳም በከፍተኛው ፍርድ ቤት 13 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸውን በይግባኝ ጠቅላይፍርድ ቤቱ ወደ 11 ዝቅ እንዲል አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ እነ አቶ በቀለ ገርባ የተከሰስነው በሐሰት የፈጠራወንጀል እንጂ ምንም የፈፀምነው ወንጀል ስለሌለ፤ አቃቤ ህግም በከሰሰን ወንጀል ያቀረበው ማስረጃ እርስ በርሱየሚጣረስ በመሆኑ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በነፃ ሊያሰናብተን ይገባል ሲሉ ይግባኝ ቢሉም ፤ሰበር ሰሚ ችሎቱ በዛሬውጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም. ውሎው የይግባኝ ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል፡፡
በተያያዘ ዜና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱዓለም አራጌ ፣ሌላው የፓርቲው ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንን፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ ክንፈሚካኤል ደበበ እናሌሎች የአንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰነባቸውንየጥፋተኝነት ውሳኔ በመቃወም ለሰበር ሰሚ ችሎት ይግባኝ ብለዋል፡፡ በዚሁ መሰረት የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 8 ሰዓት 6 ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቀነ ቀጠሮ መሰጠቱንጠበቃው አቶ አበበ ጉታ አስታውቀዋል፡፡
ይህም ለነ አቶ አንዱዓለም ቀጠሮ የመጀመሪያው የሰበር ሰሚ ችሎት ቀነ ቀጠሮ መሆኑ ታውቋል፡፡ አቶ አንዱዓለምአራጌ በከፍተኛው እና በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕድሜ ልከል ፅኑ እስራት ሲፈረድበት ጋዜጠና እስክንድ ነጋ ደግሞ 18 ፅኑ እስራት ፍርድ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መፅናቱ ሲታወቅ የሌሎችም እንዲሁ መሆኑም አይዘነጋም፡፡
ስለ ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ በጥቂቱ
የዶክተር ቅጣው እጅጉ አጭር የሕይወት ታሪክዶክተር ቅጣው እጅጉ የካቲት 16 ቀን 1940 (እ.ኢ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ
ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኃላበባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅየከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
ዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ፣በሄሮሺማ ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እናየአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።
ዶክተር ቅጣው በናሳ (NASA) በሲስተም መሃንዲስነትና በጠፈር ሳይንቲስትነት የሰሩ
ሲሆን ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና
ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና ሮኬቶች ፈጥረዋል። ዶክተር ቅጣው በዚህ ከፈጣሪ በተቸሩት ታላቅ ችሎታና እውቅት ለዚህች ለምንኖርባት ዓለምና ሕዝብ ታላቅ አስተዋፅዎ አበርክትዋል። ከነዚህም ጥቂቱን ለመጥቀስ ለናሳ(NASA) ሁለት የኤሮ-ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር (Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ
ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን
ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም(Global Positioning Satellite System)
ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ በአማካሪነት አገልገለዋል።
በተጨማሪም ለሀገራቸው በነበራቸው ታላቅ ፍቅር ‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ግንባር’ የተባለውን ድርጅት በመመስረት ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ለኢትዮጵያ ሰላም ፣ ብልፅግናና አንድነት ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉ የትግል ሰው ነበሩ። በእውነትም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ዓለም አንድ ትልቅ ሰው አጣች ቢባል ማጋነን አይሆንም። ዶክተር ቅጣው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ስቴላ እጅጉ ጋር በመልካምና በደስታ ጋብቻ ተጣምረው ይኖሩ ነበር። ዶክተር ቅጣው፣ ቢንያም ያሬድ እና አቢጋኤል የተባሉ የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት አባት ነበሩ።
ዶክተር ቅጣው እጅጉ ወደ ኦስትን ቴክሳስ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ መጥተው ድንገት
በደርሰባቸው ሕመም ምክንያት በታማኝነትና በመሰጠት ሲያገለገሉትና ዘወትር ሊያዩት
ወደሚናፍቁት ጌታቸው እየሱስ ክርስቶስ በጃንዋሪ 12 ቀን 2006 በ58 አመታቸው ተሰብስበዋል።
ዶክተር ቅጣው እጅጉ በመልካም ባህሪያቸው የተወደዱ፣ በትህትናቸው የተመሰገኑ፣ በስራቸው የተደነቁ፣ በራዕያቸው ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ፣ የብዙዎቻችን ተስፋና አርዓያ እንዲሁም የሀገር ኩራት የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ። ዶክተር ቅጣውባለቤታቸውንና ልጆቻቸውን አፍቃሪ፣ ዘመድ ወዳጅ አክባሪ እና ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ፈሪ ነበሩ።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የመጀመሪያው ማጣሪያ ጨዋታ በናይጄሪያ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለብራዚሉ ዓለም ዋንጫ 2014 ማጣሪያ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዛሬ ጥቅምት 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ከናይጄሪያ አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ 2 ለ 1 ተሸነፈ፡፡ በውጤቱም ኢትዮጵያ 1፡ 2 ናይጄሪያ በመሆን ተጠናቀቋል፡፡ በጨዋታውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ከፍተኛ ብልጭ የበላይነቱን ቢያረጋግጥም፤የኢትዮጵያ የፊት አጥቂ ሳላዲን ሰይድ ያገባት ጎል በዳኛው ተሽራለች፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን የበረኛው ክልል አካባቢ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ባለቀ ሰዓት ናይጄሪያ ልታሸንፍ ችላለች፡፡
ሁለቱም ቡድኖች ጎሉን ያስቆጠሩት በሁለተኛ አጋማሽ ሰዓት ሲሆን ለኢትዮጵያ በ56ኛው ደቂቃ የመሪነት ጎሉን በግራ አቅጣጫ ያስቆጠረው በኃይሉ አሰፋ (ቱሳ) ነው፡፡ ናይጄሪያ ደግሞ አንዱን በጨዋታ ስታገባ ሁለተኛውን ጎል ግን በተሰጣት ፍፁም ቅጣት ምት ነበር፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ስታዲየም በተመልካቾች የብሔራዊ ቡድኑን መለያ በመልበስ እጅግ አሸብርቀው ለሜዳው ደምቀት ሰጥተውታል፡፡ ቀጣዩ የደርሶ መልስ በናይጄሪያ በሚደረገው ጨዋታ ለዓለም ዋንጫ የመጨረሻው ውጤት ይታወቃል፡፡
የአለም ሻምፒዮኖቹ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ለአለም ኮከብ አትሌትነት እጩ ሆኑ
የአለም ኮከብ እጩዎቹ ጥሩነሽ፣ መሐምድ እና መሰረት

የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ባለሞያዎች ቡድን እ.አ.አ በ2013 ዓ.ም የአትሌቲክስ ውድድር አመት አትሌቶች በሩጫ፣ ውርወራ እና ዝላይ ውድድሮች ያስመዘገቧቸውን ውጤቶች እና ሌሎች መስፈርቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ባደረገው የኮከብ አትሌቶች እጩዎች ምርጫ ኢትዮጵያዊያኖቹ የረጅም ርቀት ሩጫ ድንቆች ጥሩነሽ ዲባባ እና መሰረት ደፋር፣ እንዲሁም የወቅቱ የ800 ሜትር ሩጫ ኮከብ መሀመድ አማንን ጨምሮ በወንዶች 10፣ በሴቶች 10 አትሌቶችን እጩ አድርጎ አቅርቧል።
በሞስኮ አስተናጋጅነት በተካሄደው 14ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 10 ሺህ ሜትሩን 30፡43.35 በሆነ ጊዜ በማጠናቀቅ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ በርቀቱ ሶስተኛዋ በአጠቃላይ ደግሞ አምስተኛዋ የሆነው የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ጥሩነሽ ዲባባ በ10 ሺህ ሜትር ርቀት ባደረገቻቸው 11 ተከታታይ ውድድሮች አንድም ውድድር አለመሸነፏ እና በ2013 ዓ.ም በተለያዩ ርቀቶች ባደረገቻቸው ውድድሮች ጠንካራ ተፎካካሪነቷን በተደጋጋሚ ለማሳየት መቻሏ ለእጩነት አብቅቷታል።
የ 2007 ዓ.ም የአለም ኮከብ መሰረት
ሌላዋ ለአለም ኮከብነቱ እጩ የሆነችው ኢትዮጵያዊ አትሌት መሰረት ደፋር በሞስኮው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማጣሪያውን በቀላሉ ካለፈች በኋላ በፍጻሜው ውድድር ወቅት በተለመደው አስደናቂ የአጨራረስ ብቃቷ በመታጀብ 5 ሺህ ሜትሩን 14:50.19 በሆነ ጊዜ አጠናቃ ለሁለተኛ ጊዜ በርቀቱ የአለም ሻምፒዮን ከመሆኗ በተጨማሪ አመቱ ጥንካራ ተፎካካሪዋ ጥሩነሽ ዲባባን በዳይመንድ ሊግ ያሸነፈችበት እና በተደጋጋሚ አስደናቂ ብቃቷን ያሳየችበት ሆኖ ነው የተጠናቀቀው።
እ.አ.አ በ 2007 ዓ.ም መሰረት ደፋር እጅግ በጣም ውጤታማ አመትን በማሳለፏ በአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) የአመቱ ኮከብ ሴት አትሌት ተብላ በመመረጥ ይሄንን ክብር ያገኘች በታሪክ ሁለተኛዋ ሴት አፍሪካዊት አትሌት ለመሆን ከመቻሏ በተጨማሪ ሶስተኛዋ ኢትዮጵያዊትም ለመሆን መቻሏ ይታወሳል። ከመሰረት በፊት ታላላቆቹ ሀይሌ ገብረስላሴ (1998 ዓ.ም) እና ቀነኒሳ በቀለ (2004 እና 2005 ዓ.ም) የአመቱ የአለም ኮከብ አትሌቶች ተብለው ተሸልመዋል።
በወንዶቹ በኩል ለኮከብ አትሌትነት ዘንድሮ እጩ ሆነው ከቀረቡት አስር አትሌቶች መካከል ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መሀመድ አማን 2013 ዓ.ም እጅግ በጣም ስኬታማው አመት ነበር። በሞስኮው 14ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድንቅ የአጨራረስ ብቃት 800 ሜትሩን በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ ሶስተኛው ፈጣን ሰአት ሆኖ በተመዘገበ 1:43.31 በሆነ ጊዜ አጠናቆ ለኢትዮጵያ በታላላቅ ሻምፒዮናዎች ከ5 ሺህ ሜትር በታች በሆነ ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘ በታሪክ የመጀመሪያው አትሌት የሆነው መሀመድ አማን በርቀቱ የዳይመንድ ሊግ ሻምፒዮን በመሆን በፍጹም የበላይነት ነበር የዘንድሮውን የውድድር አመት ያጠናቀቀው።
እ.አ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2013 ጀምሮ እስከ ፊታችን ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ *የአለም አትሌቲክስ ቤተሰብ* በኢሜል መልእክቶች በሚያደርገው የድምጽ አሰጣጥ ሂደት ከፍተኛ ድምጽ የሚያገኙ ሶስት ወንድ እና ሶስት ሴት አትሌቶች ወደፍጻሜው የሚያልፉ ሲሆን፣ ከዛ በኋላ የአለም አቀፉ አትሌቲክ ፋውንዴሽን ምክርቤት የአለም ኮከብ በመሆን የሚያሸንፉት ወንድ እና ሴት አትሌቶችን መርጦ አሸናፊዎቹ እ.አ.አ ህዳር 16 ቀን 2013 ዓ.ም ሞናኮ ውስጥ በሚካሄድ ስነ-ስርአት በይፋ ይታወቃሉ።
የዘንድሮውን የአለም ኮከብ አትሌትነት ክብር ጃማይካዊያኖቹ የአጭር ርቀት ውድድር ኮከቦች ዩሴን ቦልት እና ሼሊ-አን ፍሬዘር-ፕራይስ ይወስዱታል ተብሎ ይጠበቃል።
ዩሴን ቦልት እና አሜሪካዊቷ አሊሰን ፊልክስ የ2012 ዓ.ም የወንዶች እና ሴቶች የአለም ኮከብ አትሌቶች ተብለው መመረጣቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡- ፍስሃ ተገኝ “ቶታል 433 “ ስፖርት