Tag Archives: Ethiopian-Yeman

በየመን ጦርነት 45 ኢትዮጵያዊያን ሲገደሉ ከ60 በላይ ቆስለዋል

ግሩም ተ/ኃይማኖት

ሰሞኑን ያለማቋረጥ የመን ላይ እየተወሰደ ባለው የአየር ጥቃት ምክንያት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በከፍተኛ ችግርና ጭንቀት ውስጥ ናቸው፡፡ ዛሬ በተደረገ የአየር ድብደባ ምክንያት ካምፕ ውስጥ የነበሩ 45 ኢትዮጵያዊን ሲገደሉ ከ60 በላይ ቆስለዋል፡፡

Yeman war

በIOM ካምፕ ላይ በስህተት የተወሰደ እርምጃ ነው በተባለው በዚህ ጥቃት፤የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ የነበሩት የምስራቅ አፍሪካ ስደተኞች ናቸው የሞቱት የሚል መግለጫ IOM ቢያወጣም፤ በዛ ካምፕ ውስጥ የሚጠቀሙት ኢትዮጵያዊን መሆናቸው ግን የታወቀ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ሄጄ ካምፑን እንዳየሁት እኔም የማውቀው በጅቡቲ በኩል ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ብቻ እንደሚያርፉበት ነው፡፡ የሞቱትን ነፍስ ይማር!!!! የተቀሩት ኢትዮጵያዊያንስ እጣ ፋንታ ምን ይሆን?

%d bloggers like this: