የአንድነት ፓርቲን ለመጪዎቹ አመታት የሚመራ ሊቀመንበር 3 ዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀመሩ
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ለመጪዎቹ 3 ዓመታት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ተክ በመተካት ፓርቲውን በሊቀመንበርነት የሚመራ 3 ዕጩዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ መቀጠላቸው ተገለፀ፡፡ ፓርቲው በተለይም የፓርቲውን ዓላማና ግብ በአጭር ጊዜ ከማሳካት አንፃር ትግሉን ይመራል፣ መጪውን 2007 ዓ.ም. ምርጫንም በድል ለማጠናቀቅ ይረዳ በሚል ከወዲሁ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመጥራት አዲስ የፓርቲውን ሊቀመንበር እና የብሔራዊ ምክር ቤት አባላትን ሊያስመርጥ ነው፡፡ ለዚህም መጪዎቹን ዓመታት አንድነት ይመራል በሚል በዕጩነት የቀረቡት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኬሚካል ኢንጂነሩ ረዳት ፕሮፌሰር ግዛቸው ሽፈራው፣ በፓርላማ ብቸኛው የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካይ እና የልማት አማካሪ አቶ ግርማ ሰይፉ እና መንግስታዊ ያልሆነ በአፍሪካ የንግድ ግብይት ጥናት ድርጅት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተክሌ በቀለ ናቸው፡፡
ኢንጂነር ግዛቸው በሙያቸው በኬሚካል ምህንድስና ማስተርስ ድግሪ ያላቸው ሲሆን፤ በፖለቲካ ህይወታቸው በመኢአድ እና በኋላም በቅንጅት ፤አሁን ደግሞ በአንድነት/መድረክ ከተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርነት ጀምሮ አሁን ደግሞ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በመሆን ልምድ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ አቶ ግርማ ሰይፉ ደግሞ በኢኮኖሚ ፖሊሲ ትንተና የማስተርስ ድግሪ ያላቸው ሲሆን፤ በፖለቲካ ህይወታቸው በቀድሞ ኢዴሊ በኋላም በቅንጅት፤ አሁን ደግሞ የአንድነት/መድረክ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና ስራ አስፈፃሚ እና የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በመሆን ልምድ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡
ሶስተኛው እጩ ደግሞ የአንድነት ፓርቲ የጀርባ አጥንት በመሆን ሰፊ ስራ እየሰሩ ያሉት አቶ ተክሌ በቀለ በሙያቸው በማኀበራዊ ግብይት የማስተርስ ድግሪ ያላቸው ሲሆን፤ በፖለቲካ ህይወታቸው በቀድሞ ኢዴፓ በኋላም በቅንጅት አሁን ደግሞ በአንድነት/መድረክ ከሰሜን ቀጠና አደራጅነት ጀምሮ በአሁን ወቅት የማዕከላዊው ፋይናንስ ሃላፊ እና ስራ አስፈፃሚ አባል እንዲሁም የብሔራዊ ምክር ቤት አባል በመሆን ሰፊ የፖለቲካ ልምድ እንዳላቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ፓርቲው በያዝነው የፊታችን ታህሳስ 2006 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ በሚያካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የፓርቲውን ሊቀመንበር ጨምሮ በፓርቲው ከፍተኛ ስልጣን ላለው ብሔራዊ ምክር ቤት አባላትን እንደሚያስመርጥ ይታወቃል፡፡ በተለይ ዕጩ ሊቀመንበሮቹ በአሁን ወቅት በይፋ የምረጡኝ ቅስቀሳ መጀመራቸውን የፓርቲው ልሳን ያስታወቀ ሲሆን፤ በመካከላቸው ያለው ፉክክርም እጅግ ፈታኝ እና አጓጊ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
Our World lost the Greatest Icon
Our World lost African the greatest icon, in December 5, 2013. Who is Nelson Mandella has died yesterday midnight aged 95. He was prisoner at very cold island of Roben for 27 years. He struggle Racism the so called appartide in South Africa until to free in 1993. Then He was a president of new bright South Africa 1994-1999.
Madella is a father of justice, peace, love and a good symbol for all over the world. And also he was a bridge for giveness. His work and role is not only for South Africa but also worldwide. His fruit will be above statue. Now who likes Mandella in Africa as well as the world? He is just gift of God Rather than his positive role for the people. Today our world especially Africa needs another Mandella for the nation otherwise they might be back as earlier. Really today our World lost its icon.
የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ፍርድ በአየር ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ
የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመጨረሻ ፍረድ ብይን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም ያለምንም ችሎት በአየር ላይ ለሌላ ጊዜ መቀጠሩ ታወቀ፡፡ ቀደም ሲል ጉዳዩ ልደታ ከሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዝግ ችሎት እየታየ የነበረ ሲሆን፤ በብዙዎች ግምት የመጨረሻ የብይን ፍርዱ ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ በሁለቱም ፍርድ ቤት ችሎት አለመሰየሙ ታውቋል፡፡
ይሁን እንጂ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ጉዳዩን እንዳይከታተሉ በዝግ ችሎት ሲያደርግ የቆየው አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው ፍርድ ቤት ዛሬ በመዝገብ ቤት በኩል ለአንዱ ተከላካይ ጠበቃ የመጨረሻ ይሆናል የተባለውን የፍርድ ብይን ለታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ያለ ምንም ችሎት በአየር ላይ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ተከላካይ ጠበቆችም ከፍርድ ቤት አሰራር ውጭ ያለምንም ችሎት ቀነቀጠሮ መሰጠቱ እንዳስገረማቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በወለጋ ሻምቡ ወህኒ ቤት አንድ ወታደር ሁለት አለቆቹን ገደለ
ትናንት ህዳር 24 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ውስጥ በሚገኘው ሆሮጉድሩ ወረዳ ሻምቡ ወህኒ ቤት አንድ ወታደር ሁለት አለቆቹን በመሳሪያ ገድሎ እጁን ሰጠ፡፡
ገዳዩ አለቆቹ በተደጋጋሚ በእስረኞች ላይ እና በሌሎች የበታች ሰራተኞች ላይ ጸደጋጋሚ በደል ሲፈፅሙ ይቃወም የነበረ ሲሆን ትናንት ግን እስካሁን በውል ባልታወቀ ምክንያት ሁለቱነብ አለቆቹን መግደሉን ምንጮቻችን ከስፍራው አስታውቀዋል፡፡ የወረዳው ፖሊሶች ዝርዝር መረጃውን እንዲሰጡን ተደጋጋሚ ጥረት ብናደርግም አልተሳካም፡፡
በአፍሪካ ትልቁ የንግድ ማዕከል በሆነው መርካቶ በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረቶች ወደሙ
በአዲስ አበባ የሚገኘው የአፍሪካ ትልቁ የንግድ ማዕከል መርካቶ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በኋላ በመርካቶ ልዩ ቦታው ከምዕራብ ሆቴል ወደ በርበሬ በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሐረር ሜትሮ ሆቴል ዓለም ሽንሽን እና ጌጣጌጥ በሚሸጡባቸው ሱቆች እና በተለምዶ ጆንያ ተራ እየተባለ በሚጠራው ቦታ በተነሳ የድንገተኛ ችሳት ቃጠሎ እስካሁን ግምቱ ያልታወቀ ንብረት አውድሟል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር እሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ድርጅት እሳቱን ለማጥፋት በቶሎ ባለመድረሱ ብዙ መትረፍ የሚገባቸው ንብረቶች ሊወድሙ መቻላቸው የታወቀ ሲሆን፤ ድርጅቱ በበኩሉ ወደ መርካቶ መሄጃ መንገዶች በመቆፋፈራቸው ለመዘግየቱ እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡ በአካባቢው ያሉ እማኞች በበኩላቸው ድርጅተሩ በከተማው መቼም ቢሆን በአፋጣን ደርሶ ውድመትን አድኖ አያውቅም፤ ብዙ ንብረት ማትረፍ ሲቻል ብዙ ጊዜ ሆን ብሎ በሚመስል መልኩ ይዘገያል የሚል ትችትን አቅርበዋል፡፡



