Daily Archives: October 16th, 2013

ስለ ዶክተር ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ በጥቂቱ

የዶክተር ቅጣው እጅጉ አጭር የሕይወት ታሪክዶክተር ቅጣው እጅጉ የካቲት 16 ቀን 1940 (እ.ኢ.አ) ከአባታቸው ከአቶ እጅጉ ሃይሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ በላይነህ በከፋ
ጠቅላይ ግዛት በቦንጋ ከተማ ተወለዱ። የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቦንጋ፣ በዋከና በጅማ ከተማ ካጠናቀቁ በኃላበባህር ዳር በሚገኘው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅየከፍተኛ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
kitዶክተር ቅጣው ወደ ጃፓን አገር በመሄድ በኦሳካዪኒቨርስቲ በቋንቋና የጃፓን ኢኮኖሚ፣በሄሮሺማ ዩንቨርስቲ የኢንደስትሪ እናየአውቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ አጥንተው ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በኋላም አሜሪካን ሀገር ስኮላር ሺፕ አግኝተው በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን ማስትሬታቸውን በመጨረሻም ለትምህርት ባላቸው ከፍተኛ ፍላጎት በኤሮ-ስፔስ ምህንድስና ዶክትሬታቸውን ተቀብለዋል።

ዶክተር ቅጣው በናሳ (NASA) በሲስተም መሃንዲስነትና በጠፈር ሳይንቲስትነት የሰሩ
ሲሆን ከሌሎች መሃንዲሶችና ሳይንትስቶች ጋር በመተባበር ለእኛ አለም (Planet Earth) እና
ለተቀሩት ፕላኔቶች የምርምር ሳይንስ (Planetary Science Research and Exploration) የሚረዱ የጠፈር መንኮራኩሮችና ሮኬቶች ፈጥረዋል።  ዶክተር ቅጣው በዚህ ከፈጣሪ በተቸሩት ታላቅ ችሎታና እውቅት ለዚህች ለምንኖርባት ዓለምና ሕዝብ ታላቅ አስተዋፅዎ አበርክትዋል። ከነዚህም ጥቂቱን ለመጥቀስ ለናሳ(NASA) ሁለት የኤሮ-ስፔስ መወርወሪያ ሜካኒዝም ለቦይንግ ኩባንያ ሲሙሌተር (Flight Dynamic Simulator) እና አድቫንስድ
ወይንም ኔክስት ጀነሬሽን (Advance or Next Generation) በመባል የሚታወቁትን
ግሎባል ፖዚሽን ሳተላይት ሲስተም(Global Positioning Satellite System)
ከፈለሰፉት ውስጥ አንደኛው ሰው እሳቸው ነበሩ ዶክተር ቅጣው Trans Tech International በመባል የሚታወቀውን ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ድርጅት በመመስረት የተለያዩ ሀገሮች የቴክኖሎጂ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ በአማካሪነት አገልገለዋል።
cabበተጨማሪም ለሀገራቸው በነበራቸው ታላቅ ፍቅር ‘የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ግንባር’ የተባለውን ድርጅት በመመስረት ገንዘባቸውንና ጉልበታቸውን ሳይቆጥቡ ለኢትዮጵያ ሰላም ፣ ብልፅግናና አንድነት ትልቅ መስዋዕትነት የከፈሉ የትግል ሰው ነበሩ። በእውነትም ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ዓለም አንድ ትልቅ ሰው አጣች ቢባል ማጋነን አይሆንም። ዶክተር ቅጣው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ ስቴላ እጅጉ ጋር በመልካምና በደስታ ጋብቻ ተጣምረው ይኖሩ ነበር። ዶክተር ቅጣው፣ ቢንያም ያሬድ እና አቢጋኤል የተባሉ የሁለት ወንዶችና የአንድ ሴት አባት ነበሩ።

ዶክተር ቅጣው እጅጉ ወደ ኦስትን ቴክሳስ ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ መጥተው ድንገት
በደርሰባቸው ሕመም ምክንያት በታማኝነትና በመሰጠት ሲያገለገሉትና ዘወትር ሊያዩት
ወደሚናፍቁት ጌታቸው እየሱስ ክርስቶስ በጃንዋሪ 12 ቀን 2006 በ58 አመታቸው ተሰብስበዋል።

kitawዶክተር ቅጣው እጅጉ በመልካም ባህሪያቸው የተወደዱ፣ በትህትናቸው የተመሰገኑ፣ በስራቸው የተደነቁ፣ በራዕያቸው ብዙ ተከታዮችን ያፈሩ፣ የብዙዎቻችን ተስፋና አርዓያ እንዲሁም የሀገር ኩራት የሆኑ ታላቅ ሰው ነበሩ። ዶክተር ቅጣውባለቤታቸውንና ልጆቻቸውን አፍቃሪ፣ ዘመድ ወዳጅ አክባሪ እና ከሁሉም በላይ እግዚአብሔርን ፈሪ ነበሩ።

ፖሊስ በቦምብ ፍንዳታ ህይወታቸው ያለፈው ሶማሊያውያን አሸባሪዎች ናቸው ሲል መናገሩ ተጠቆመ

ጥቅምት3 ቀን 2006 .. በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ሩዋንዳ ማዞሪያና ቦሌ ሚካኤል መግቢያ አካባቢ በቦንብ ፍንዳታ ህይወታቸው ያለፈው ሁለት ሶማሊያውያን ሽብርተኞች መሆናቸውን ማረጋገጡን፤ የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ማስታወቁን ሪፖርተር በጥቅምት 6 ቀን 2006 .. እትሙ ዘግቧል ፡፡ የአንድግለሰብሰርቪስቤትተከራይተውከነበሩትሶማሊያውያንመካከልአንደኛው20 ቀናትበላይየቆየሲሆን፤ሌላኛውፍንዳታውከመድረሱበፊትከሁለትሰዓታትበፊትየደረሰመሆኑንግብረኃይሉማረጋገጡንአስረድቷል፡

ሽብርተኛ የተባሉት ሶማሊያውያን ካፈነዱት ቦምብ በተጨማሪ መጠናቸው ያልተገለፁ ቦምቦችና አንድ ሽጉጥ ከሁለት ካርታ ጥይት ጋር መገኘቱን፣ የፈንጅ ማቀጣጠያና የአደጋ መከላከያ ጃኬቶች ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ማሊያና ቀበቶዎች መገኘታቸውም ተጠቁሟል፡፡ እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ከሆነ ከሶማሊያውያኑ ጋር ቀጥታ ግንኙነት አላቸው የተባሉ 3 ተጠርጣሪዎችና የቤቱ አከራይ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑንም ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

የአደጋውን መንስኤና አጠቃላይ ስለነበረው ሁኔታ ፖሊስ መረጃ እያሰባሰበ በመሆኑ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ይህደጎ ስዩም ለሪፖርተር የገለፁ ቢሆንም፤ የፌደራል ፖሊስ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል ግለሰቦቹ ሽብርተኛ መሆናቸውን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደጠቆሙት ከሆነ የፍንዳታው ቅንብር ኢህአዴግ ቀደም ሲል ልክ ጨዋታው ሲያልቅ በተለይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ካሸነፈ ስታዲየም አካባቢ በማፈንዳት የድርጊቱ ፈፃሚዎች የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉ ተቃዋሚዎች እና የኃይማኖት አክራሪዎች ናቸው ለማለት አቅዶት የነበረውን ሆን ብሎ ግቡ ሳይሳካ ሲቀር በበሌላ ቦታ ማፈንዳቱን የከዚህ ቀደም የኢህአዴግን ድርጊት እያመሳከሩ ያስታወሱ አልታጡም ፡፡

በተለይም በፍንዳታው ዓለም አቀፉ ማኀበረሰብ የታሰሩ የህሊና እና የፖለቲካ እስረኞች ላይ መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንዲደግፉና እንዲፈጡ የሚጠይቀውን ጫና በመግታት እውቅና ለማግኘት ታቅዶ እንደነበር ከኢህአዴግ ውስጥ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፡- ቃሌ የውይይት መድረክ

 

 

 

የመጅሊስ እና የዑለማዎች ምክር ቤት የይፍረሱ ክስ ለሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርብ ተገለፀ

የኢትዮጵያ እስልምና እና የዑለማዎች ምክር ቤት ይፍረሱ በሚል የቀረበው አቤቱታ ውድቅ ከተደረገ በኋላ ፤ በድጋሚ ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚቀርብ ኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ባወጣው እትሙ አስነብቧል፡፡

muslimsየታሰሩት የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ እንደተናገሩት፤ የተጀመረው ክስ ለመስከረም 27 ቀን 2006 ዓ.ም. ድጋሚ ያስቀርባል አያስቀርብም የሚለውን ለማየት እንደነበር ተናግረው ፤ ጉዳዩ ተብራርቶ በመቅረቡ ለማክሰኞ ጥቅምት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚሰየም ጋዜጣው ቢዘግብም የማክሰኞ ችሎት ውሎውን በመለከተ ግን ያለው ነገር የለም፡፡

እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ፤ ዑለማዎች ምክር ቤት በራሱ በእስልምና ጠቅላይ ጉባዔዎች ስር ያለ በመሆኑ እና የነዚህ የበላይ ደግሞ መጅሊሱ በመሆኑ ዑለማዎች ምክር ቤት የማስመረጥ መብት የለውም የሚለው የክሱ አንዱ ጭብጥ መሆኑን ጠበቃ ተማም መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ እንደጠበቃ ተማም ገለፃ፤ ዑለማዎች ምክር ቤት ምርጫ ያካሄደው የራሱ የሆነ ህጋዊ ሰውነት ሳይኖረው ነው፡፡ ምርጫውን የማካሄድ ስልጣን የዑለማዎች ምክር ቤት ሊሆን አይችልም፡፡

በአዲስ አበባ የዳቦ እጥረት ተከሰተ

በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ በበቂ ሁኔታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተገለፀ፡፡የከተማው ነዋሪዎች በየዳቦ ቤቱ ዳቦ ለመግዛት ሲሄዱ ዳቦ አለመኖሩ እየተነገራቸው በተደጋጋሚ እየተመለሱ መሆኑንና ችግሩም እስካሁን እንዳልተቀረፈ ሰንደቅ ጋዜጣ በጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. እትሙ ዘግቧል፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ አንዳንድ ዳቦ መሸጫ ሱቅ የሥራ ኃላፊዎችና ባለቤቶች በተገኘው መረጃ መሰረት በዳቦ መሸጫ መንግሥት ከተመነው ዋጋ አንፃር ሲታይ አንድን ዳቦ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው የትርፍ መጠን አነስተኛ በመሆኑ ዘርፉ አበረታች አለመሆኑ ተገልፁዓል፡፡bbb
እጥረቱን በተመለከተ ጋዜጣው ያነጋገራቸው በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ሰይድ፤ የዳቦ ዋጋ ትርፍን በተመለከተ መንግስት ተመኑን ሲያስቀምጥ ያሉትን ወጪዎች ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የተፈጠረውንም የዳቦ እጥረት በተመለከተ ስንዴ በእህል ንግድ በኩል ተገዝቶሀገር ውስጥ ሲገባ መንገድ ላይ በተፈጠረው መዘግየት የተፈጠረ መሆኑን ኃላፊው አመለክተዋል፡፡ ያም ሆኖ እህል ንግድ ከመጠባበቂያ ክምችቱ በማውጣት ለአዲስ አበባም ሆነ ለክልል የዱቄት ፋብሪካዎች እንደተቀመጠላቸው ኮታ እንዲያከፋፍል መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል በ 2003 ዓ.ም. በበርካታ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ከጣለ በኋላ በስተመጨረሻ የሌሎች ተመን ሲነሳ የስኳር፣ የዘይትና የስንዴ ምርቶችን የማከፋፈል ስራ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሎ እስከ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ይሁን እስካሁን በስርጭቱ ረገድ በስኳር ላይ ተደጋጋሚ ችግር እየታየ ሲሆን አሁን ደግሞ በዳቦ ስንዴ ላይ ችግሩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

“ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መሞታቸው ተነግሮናል” አቶ ስብሃት ነጋ

በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ወቅት ያበሩት የነበረው የጦር አውሮፕላን ተከስክሶና ቆስለው በሻዕብያ እጅ ለሁለተኛ ጊዜ የወደቁት ጀግናው ኢትዮጵያዊ ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ በኤርትራ እስር ቤቶች በስቃይ ቆይተዋል፡፡

colonel bezabehጦርነቱ አብቅቶ ሁለቱ አገሮች የጦር ምርኮኞቻቸውን ሲቀያየሩ የኢትዮጵያ መንግስት በኮሎኔሉ ጉዳይ ገፍቶ መሄድ ባለመቻሉ በዛብህ ወደ አገራቸው ሳይመለሱ በኤርትራ እስር ቤት መቅረታቸውን የመንግስት ተቃዋሚዎች ይናገራሉ፡፡
የኮሎኔሉ ቤተሰቦች ደህንነታቸውን ይሰሙ የነበሩት ከአለም አቀፍ ቀይ መስቀል ሰራተኞች የነበረ ቢሆንም ግንኙነቱ መቋረጡን ለአብራሪው ቤተሰቦች ቅርበት ያላቸውና የኮሎኔሉ ወንድም ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለላይፍ መጽሔት ሰጥተውት በነበረ ቃለ ምልልስ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የኮሎኔሉ ቤተሰቦች በተለያዮ ጊዜያት ወደ መንግስት አቤት በማለት አብራሪውን በዲፕሎማሲ ጥረት ከእስር እንዲያስፈቱ ሲወተውቱ ቢቆዮም መኖር አለመኖራቸውን እንኳን የሚያረጋግጥላቸው እስከማጣት መድረሳቸው ጉዳዮን ለፈጣሪ ከመስጠት የዘለለ አማራጭ እንዳይኖራቸው አድርጓል፡:

የኢትዮጵያ የሰላምና ልማት ኢንስቲትዮትን የሚመሩት የቀድሞው የህወሃት ነባር ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ አሜሪካን አገር ጎራ ባሉበት አጋጣሚ ከገዛ ፓልቶክ ሩም ተሳታፊ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ‹‹ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ መሞታቸው ተነግሮናል፡፡አሁን እየጠየቅን የምንገኘው ከሞቱም ሬሳቸውን እንዲያሳዮንና የአሟሟታቸውን ምክንያት እንዲነግሩን ነው፡፡››በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡የፓልቶኩ አቅራቢም በኮሎኔሉ ሞት የተሰማትን ሀዘን በፓልቶኩ ስም ገልጻለች፡:

የስብሃትን ንግግር ተከትሎ የኮሎኔሉ ቤተሰቦች በስብሃት የተነገረውን ከዚህ ቀደም መስማታቸውን ለማረጋገጥ ሞክረናል፡፡ የኮሎኔሉ ቤተሰቦች በዛብህ ሞተዋል ተብለው በይፋ አለመረዳታቸውን ባደረግነው የማጣራት ሙከራ ለማወቅ ችለናል፡፡ ስብሃት ነጋ በኤርትራ 27 የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን የጦር ምርኮኞች እንደሚገኙ በቃለ ምልልሳቸው አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፡- ዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅ

%d bloggers like this: