Tag Archives: eTHIOPIAN udj PARTY

በእስር ላይ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተፈቱ

girma1ዛሬ መስከረም 17 ቀን 2006 ዓ.ም. የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንዲሁም በፓርላማ ብቸኛው የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካይና የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት 26 የአንድነት አባላት ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ተፈተዋል፡፡ በፖሊስ ተይዘው ወደጣቢያ የተወሰዱት የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አስራት ጣሴ፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ለመሆን በእጩነት የቀረቡትና የፋይናንስ ኃላፊ አቶ ተክሌ በቀለ፣ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስዩም መንገሻ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ሌሎች አመራሮችም ነበሩበት፡፡

አመራሮቹ የፊታችን እሁድ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ቀበና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊትለፊት ከሚገኘው የፓርቲው ዋና ጽህፈት ቤት አንድነት ፓርቲ ከ33 ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በመሆን ለጠሩት የተቃውሞ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በተለይ በአራዳ ክፍለ ከተማ በቅስቀሳ ላይ እያሉ መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ቢሰጥም የከተማው ፖሊስ ለቅስቀሳ የሚሰማሩ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎችን በተደጋጋሚ ያለምንም በቂ ምክንያትና ክስ እያሰረ መፍታቱ አዲስ አይደለም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራሮቹንና አባላቱን ለምን እና በምን የህግ አግባብ ለሰዓታት እንዳሰረ ብንጠይቅም ታዘንነው ከማለት ውጭ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

ለሰዓታት ታስረው የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተፈቱ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዛሬ ረቡዕ መስከረም 15 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሽሮ ሜዳ ፖሊስ ማዘዣ እና የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለሰዓታት ከታሰሩ በኋላ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ መፈታታቸው ታውቋል፡፡ ስለ ፖሊስ ጣቢያው የሰዓታት ቆይታ ሲጠየቁ፤ ዶ/ር ነጋሶ ተደንቀው “ክስ ስላልመሰረቱ ታስሬያለሁ ለማለት እቸገራለሁ፤ ግን አስገራሚ ነው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡Dr.negaso

ከቅስቀሳ ስራ ላይ በቄራ አካባቢ በእስር ላይ የሚገኙት የፓርቲው ወጣቶች ግን እስካሁን ስለመፈታታቸው የታወቀ ነገር የለም፡፡ በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ለመስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.መ. አንድነት ለጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ፖሊስ የፓርቲው አባላት ሲቀሰቅሱ ለምን እንደሚያስር ምላሽ እንዲሰጠን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ምላሻቸውን ለማግኘት አልቻልንም፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ታሰሩ

የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት እና የአሁኑ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት) ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ታሰሩ፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የታሰሩት ዛሬ መስከረም 15 ቀን 2006ዓ.ም.  አንድነት ፓርቲ አባላት በጉለሌ ክፍለ ከተማ መስከረም 19 ቀን 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለተጠራው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በሽሬ ሜዳ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሳሉ መታሰራቸውን ተከትሎ የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ያዘዝኩት እኔ ስለሆንኩ ልጆቹን ልቀቁ፤ ከፈለጋችሁ እኔን ማሰር ትችላላችሁ በማለታቸው የጣቢያው  ፖሊሶችme ዶ/ሩ ነጋሶን ማሰራቸው ተረጋግጣል፡፡Dr. Negaso

በአሁን ሰዓት የማዘዣው ፖሊሶች ዶ/ር ናጋሶን ከያዙበት ሽሬሜዳ ወደ ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ በፖሊስ መኪና እና በበርካታ ፖሊሶች ታጅበው ተወስደዋል፡፡ እስካሁንም ዶ/ሩ ነጋሶን በፖሊስ መመሪያው የማዘዣው ፖሊሶች ከማድረስ ውጭ ያነጋገራቸው  ፖሊስ የለም፡፡ በቅስቀሳ ላይ እያሉ የታሰሩትና ዶ/ር ነጋሶ ሊያስፈቱ ሄደው በምትካቸው በመታሰራቸው የተለቀቁት የአንድነት ፓርቲ አባላትም ቅስቀሳቸውን የቀጠሉ ሲሆን ሌሎች አባላትም እሁድ መስከረም 19 ቀን 2006ዓ.ም. በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ዘግይቶ በደረሰን የተያያዘ ዜና በዚሁ በአዲስ አበባ በቅስቀሳ ላይ ያሉት የአንድነት አባላት 16 አባላት ታስረዋል፡፡ በዚህ ጉዳይም ሌሎች የአንድነት ፓርቲ ከፍተኘኛ ስራ አስፈፃሚ አመራሮች የታሰሩ አባላቱን ለማስፈታት ወደየ አካባቢው አቅንቷል፡፡

%d bloggers like this: