በአዲስ አበባ የዳቦ እጥረት ተከሰተ

በአዲስ አበባ ከተማ ዳቦ በበቂ ሁኔታ እየቀረበ እንዳልሆነ ተገለፀ፡፡የከተማው ነዋሪዎች በየዳቦ ቤቱ ዳቦ ለመግዛት ሲሄዱ ዳቦ አለመኖሩ እየተነገራቸው በተደጋጋሚ እየተመለሱ መሆኑንና ችግሩም እስካሁን እንዳልተቀረፈ ሰንደቅ ጋዜጣ በጥቅምት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. እትሙ ዘግቧል፡፡ እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ አንዳንድ ዳቦ መሸጫ ሱቅ የሥራ ኃላፊዎችና ባለቤቶች በተገኘው መረጃ መሰረት በዳቦ መሸጫ መንግሥት ከተመነው ዋጋ አንፃር ሲታይ አንድን ዳቦ ለገበያ በማቅረብ የሚገኘው የትርፍ መጠን አነስተኛ በመሆኑ ዘርፉ አበረታች አለመሆኑ ተገልፁዓል፡፡bbb
እጥረቱን በተመለከተ ጋዜጣው ያነጋገራቸው በንግድ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱራህማን ሰይድ፤ የዳቦ ዋጋ ትርፍን በተመለከተ መንግስት ተመኑን ሲያስቀምጥ ያሉትን ወጪዎች ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የተፈጠረውንም የዳቦ እጥረት በተመለከተ ስንዴ በእህል ንግድ በኩል ተገዝቶሀገር ውስጥ ሲገባ መንገድ ላይ በተፈጠረው መዘግየት የተፈጠረ መሆኑን ኃላፊው አመለክተዋል፡፡ ያም ሆኖ እህል ንግድ ከመጠባበቂያ ክምችቱ በማውጣት ለአዲስ አበባም ሆነ ለክልል የዱቄት ፋብሪካዎች እንደተቀመጠላቸው ኮታ እንዲያከፋፍል መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሚል በ 2003 ዓ.ም. በበርካታ የፍጆታ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ተመን ከጣለ በኋላ በስተመጨረሻ የሌሎች ተመን ሲነሳ የስኳር፣ የዘይትና የስንዴ ምርቶችን የማከፋፈል ስራ ሙሉ ለሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ውሎ እስከ ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ይሁን እስካሁን በስርጭቱ ረገድ በስኳር ላይ ተደጋጋሚ ችግር እየታየ ሲሆን አሁን ደግሞ በዳቦ ስንዴ ላይ ችግሩ እየተንፀባረቀ መሆኑን ሰንደቅ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: