ሰበር ዜና፤ የኢትዮጵያ መንግሥት ሶስት ጋዜጠኞችን እና ሁለት የዞን 9 ብሎገሮችን ከእስር መልቀቁን አስታወቀ
ከሚያዚያ አጋማሽ 2007 ዓ.ም. በፌደራሉ አቃቤ ህግ በ”ሽብርተኝነት” ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ እየታየ ከነበረው የዞን 9 ብሎገሮች እና ጋዜጠኞች መካከል፤ ሶስቱን ጋዜጠኞች እና ሁለቱን ብሎገሮች ክሳቸው በፍትህ ሚኒስቴር ውድቅ ተደርጎ መፈታታቸውን የገዥው መንግሥት ደጋፊ የሆነው ሬዲዮ ፋናን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡
ዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእስር የተፈቱት ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ፣ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ እና ኤዶም ካሳዬ፤ የዞን 9 ብሎገሮች መካከል ዘለዓለም ክብረት እና ማህሌት ፋንታሁን እንደሆኑ ታውቋል፡፡
እንደሬዲዮ ፋና ዘገባ ከሆኑ ቀሪዎቹ የዞን 9 ብሎገሮች መካከል በእስር ላይ የሚገኙት በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና በሌለችበት ክስ የተመሰረተባት ሶሊያና ሽመልስ የክስ ጉዳዩን እንደሚቀጥል የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ማስታወቁን ጨምሮ ዘግቧል፡፡
ጋዜጠኞቹ እና ብሎገሮች ቀደም ሲል በፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ በ”ሽብር ወንጀል” ተከሰው ጉዳያቸው በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ለሐምሌ 13 ቀን 2007 ዓ.ም. ለብይን ተቀጥሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡
የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በተመሰረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ተባሉ
ከ35 ወራት የፍርድ ሂደት ቆይታ በኋላ ዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእስር ላይ ባሉት የኢትዮጵያ ሙስሊሙ ማኀበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሜቴ አባላት በሆኑት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግን እና የመከላከያ ምስክሮችን ቃል በንባብ አሰምቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ በ18 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ሰጥቷል።
ከ1ኛ እስከ 9ኛ ያሉት ተከሳሾች በተከሰሱባቸው በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ላይ በተዘረዘሩት መቀስቀስ፣ ማነሳሳት እና ማሴር በሚሉ ወንጀሎች ጥፋተኛ ተብለዋል።

ቀሪዎቹ ተከሳሾች በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ላይ በተጠቀሰው በመሳተፍ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል።
ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሀምሌ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ሰጥቷል።
ተከሳሾቹ እና አቃቤ ህግ ከሀምሌ 27 ቀደም ብለውም የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡም አዟል።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ጠዋት ከከሳሽና ከተከሳሽ በኩል በተካሄዱ ክርክሮች አምስት ጭብጦችን መመርመሩ ነው የተመለከተው።
ከአምስቱ ጭብጦች መካከል መንግስት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል አልገባም? የሃይማኖቱ ተከሳሾችን ከፋፍሏል አልከፋፈለም? እና የመጅሊሱ ምርጫ ከህገ መንግስቱ ጋር ተጋጭቷል? አልተጋጨም? የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው።
ችሎቱ እነዚህን ጭብጦች ሲመረምር በተለያዩ ሃገራት ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የሚራመዱ አሰራሮችን ማየቱን በችሎት መግለፁ ተጠቁሟል፡፡
ከዚህ ሰፊ ሃተታ በኋላ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አለመግባቱን፣ ተከታዮችን አለመከፋፈሉንና የመጅሊሱ ምርጫ ከህገ መንግስቱ ጋር ሳይቃረን በሃይማኖታዊ ስርአት መካሄዱን ከምስክሮችና ከማስረጃ ቃል በማገናዘብ አረጋግጫለሁ ማለቱን ተከትሎ ነው ከሰዓት በኋላ ፍርድ መስጠቱን ኤቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡
Obama’s visit diplomatic triumph or misplaced priority?
The upcoming official visit by United States President Barack Obama has sparked fierce debate between thrilled diplomats and concerned activists in the US.
Former diplomats say that Obama’s visit, a first for a sitting American president, is welcome news that recognizes the two countries’ ever-increasing ties. Meanwhile, human rights activists say the visit could be seen as an endorsement of the Ethiopian government’s alleged restriction of press and political freedoms.
The US State Department, in its annual Human Rights Report issued on June 25, grouped Ethiopia together with a small list of countries including China and Eritrea, accused of contravening human rights. Rights groups say that despite such reports, the US priorities its security cooperation with Ethiopia while turning a blind eye to rights abuse.
Ahistoric visit
Former presidents Jimmy Carter, Bill Clinton and George Bush have all visited Ethiopia, but only after leaving office. The 44th US President…
View original post 657 more words
“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት
የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል! መልዕክታቸውም እነሆ፤…
“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)
ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን ያህል እናንተም የተጎዳችሁ መሆናችሁን በተለያዩ ሀገሮች በተደረጉ ሰልፎች ፤ የዉይይት መድረኮች ላይ በንዴት፤ በቁጭት እና በእልኸኝነት በእንባ ስትራጩ በመሃላችሁ ተገኝቼ ያየኻችሁ ሲሆን፤ ይህም በጣም በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል። አንዳርጋቸውም በወያኔ የጨለማ እስር ቤት እየከፈለ ያለውን መከራና መስዋትነት የትም እንዳልወደቀና እንዳልቀረ በማሰብ እጽናናለሁ።
ዛሬ አንዳርጋቸው ፅጌ በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ“፤ “የኢትዮጵያ ልዩ አፈር“፤ “የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ” ወዘተ…. የሚሉ መገለጫዎችን እና መጠሪያዎችን የተጎናፅፈው ታናሽ ወንድሜ አንዳርጋቸው ፅጌ በእኔ እይታ ደግሞ የቤተሰባችን ልዩ ልጅ ነው።
አንዳርጋቸው የቤተሰባችን የመጀመረያ ወንድ ልጅ ስለነበረ ብርቅዬ መሆን የጀመረው የካቲት 1 ቀን 1947 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሆስፒታል ከእናታችን ከወ/ሮ አልታዬ ተሰማ ሮቢ እና ከአባታችን ከአቶ ፅጌ ሀብተማርያም ጨሜሳ ከተወለደ ቀን ጀምሮ ነው።
አንዳርጋቸው ለወላጅ አባታችን እና እናታችን፤ ለአያቶቻችን እና ለቅድመ አያቶቶቻችን ፤ ለእህቶቻን እና ለወንድሞቻችን ፤ ለዘመድ አዝማድ፤ ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ በአጠቃላይ በአካባቢው ለነበሩት ዘመድ እና ወዳጅ ሁሉ ትልቅ እና ትንሽ ፤ ሐብታም እና ደሃ ፤ ወንድ እና ሴት ሳይል እንዲሁም በትምህርት ቤት አክብሮት እና ትህትና ሲያሳይ የኖረ ነው። የአንዳርጋቸው ሌላው ትልቁ እና አስገራሚው ስጦታዉ ወደር የማይገኝለት ትዕግስቱ ነው።
በቅርበት ከነበርው አካባቢው ሰፋ ባለው ክልል ወስጥም ቢሆን አንዳርጋቸው ስለ ሀገሩ እና ስለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር እና ደህንነት የነበርው የተቆርቋሪነት ስሜት ገና የአንደኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከነበረበት ዘመን የጀመረ ነበር። ለዚህም ነው ዛሬ “ለአንቺነው ነው ሀገሬ ” የሚል ግጥም ለገጠመላት የልጅነት ፍቅረኛው “ኢትዮጵያ” ሲል ልጆቹን ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ጥሎ የሀገርን ጥቅም እየነገደ የቡድን ምቾትን እና ሀብትን በማካበት ላይ የሚገኘውን የዘረኛ ባንዳ ወያኔ መንግስት በቁርጠኝነት ለመታገል የተነሳው።
አንዳርጋቸው አገሩን በበጎውም በክፉም ዘመን የሚያውቃት የ1960ቹ ትውልድ አካል በመሆኑ ነው፡ በዚህም በዚያም የተነሳ ይችን አገር ለማዳን የመጨርሻው ትውልድ እንደመሆኑ ይህንን አደራ ለመሸከም ታሪክ የጣለበትን ሀላፌነት ከዚህ የመነጨ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ ስለሆነም አንዳርጋቸው ቁጭ ብሎ ከመፀፀት በላይ እራሱን ለዚች አገር የመስዋት ጠቦት አድርጎ ማቅረቡና ታፍኖ ያለው ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን ተረድቶ በልቡ ማሀደር ላይ በክብር የጻፈው በመሆኑ ማንም ምድራዊ ሀይል ምንም አይነት ጥላሸት በመቀባት ሊቀይርው እንደማይችል ባለፉት 10 ወራት የታየው አብሮነት ትልቅ ምስክር ነው።
እነሆ! ይህ ጉዞው ዛሬ በወረበላው የየመን መንግስት ሹማምንት ተባባሪነት በጠላቶቹ እጅ እንዲወድቅ አድርጎታል። አንዳርጋቸው በጠላቶቹ እጅ ከወደቀ አስርኛ ወራቶች በላይ ቢቆጠሩም እስከ ዛሬ ድርስ ከአረመኔዉ ወያኔ አፋኞች ውጭ እና ከፈጣረው በስተቀር የት ስፍራ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ የሚያውቅ ሰው የለም።
አንዳርጋቸው በዚህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ መዉደቁ ልቤ ውስጥ የተቀመጠ የእሳት ረመጥ ሆኖ በየቀኑ እያቃጠለኝ ቢገኝም፤ በሀገሬ ኢትዮጵያ ፤ ከአሜረካ እስከ ካንዳ ፤ከጃፓን እስክ ደቡብ ኮረያ፤ ከአዎሮፓ እስከ ደቡብ አፍሪካ፤ ከአውስትራሊያ እሰከ እስራኤል እንዲሁም በተለያዩ የአርብ አገራት ባለው የአለማችን ስፋት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን ወገኖቼ ” እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ !” ፡ “ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን” ብለው በመነሳት የወያኔን እና የተባባሪዎቹን እብሪት፤ትዕቢት እና ህገወጥነትን ለማጋለጥ እያደረጉ ያለው ትግል ታላቅ መፅናናትን ይሰጠኛል።
አንዳርጋቸው የትናንሽ ልጆች አባት ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ የ 85 ዓመት እድሜ ባለፅጋ የሆኑ አባታችን እዚያው ታፍኖ በተቀመጠበት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራል። ከዚህ በተረፈ በጣም ከሚወዱት እና ከሚያፈቅሩት ከቅርብ ቤተሰቦቹ አልፎ አሁን ግን በአንዳርጋቸው የሀገር ፍቅር ፤ ለነጻነት ፤ ለፍትህ ፤ ለእኩልነት እና ለዴሞክራሲ የሚታገሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባት እና እናቶች ፤ ወድም እና እህቶች ፤ ልጆች አፍርቶ ይገኛል።
ይችን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት ለዚህ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ቤተሰቤ ልባዊ ምስጋናዬን በአንዳርጋቸው ስም ለማቅረብ ነው። በዚህ ክፉ ጊዜ የታየው ቆራጥነት በወያኔ ታፍኖ የተወሰደው ወንድማችንን ሙሉ ነጻነቱን እንዲሁም በወያኔ እስር ቤት እየማቀቁ ላሉት የነጻነት ታጋዮች እንዲሁም መብትና ነጻነቱን ተገፎ በሰፊዉ እስርቤት እየማቀቀ ላለው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን እንደሚቀጥል እና ከግቡ እንደሚያደርስ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።
በመጨርሻም ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ አንዳርጋቸው እና እሱን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮች እና የፖለቲካ መሬዎች ካለፍርድ በየስር ቤቱ በግፍ ታጉረው ላሉ ሁሉ እና ለቤተሰቦቻቸው ጭምር ፈጣሪ አምላካችን ብርታቱን ይስጥልኝ። የመጨርሻውም ፍርድ የሚመጣው ከሱ ከእግዛብሄር ስለሆነ ይችን የምንወዳትን የጋራ ሀገራችንን ለመታደግ በጋራ የጀመርነውን በጋራ እንውጣው ስል በወያኔ ጭለማ እስር ቤት ውስጥ በሚሰቃዩት ወገኖች ስም እማፀናለሁ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ወደ ሳሙኤል አወቀ መኖሪያ ቤት ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ
• ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ለሌላ ለቅሶ በመሄድ ላይ የነበሩ ዜጎች ተደብድበው ተመልሰዋል
የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ደብረማርቆስ ከተማ የተገደለው የሳሙኤል አወቀ ለቅሶ እንዳይደርሱ ታገዱ፡፡ አመራሮቹና አባላቱ ዛሬ ሰኔ 13/2007 ዓ.ም በጠዋት ከአዲስ አበባ ተነስተው የሳሙኤል አወቀ ቤተሰቦች ወደሚገኙበት ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን እያቀኑ በነበረበት ወቅት አባይ ድልድይ ላይ በፌደራል ፖሊስ ታፍነው ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ጎሃ ፂዮን ከተማ ውስጥ እስከ ምሽቱ 2 ተኩል ድረስ ታግተው ውለዋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ወደ ለቅሶ እንዳይሄዱ ያገዱት ከአዲስ አበባ የሄዱና ከቦታው ተዘጋጅተው ሲጠብቁ የነበሩ የፌደራል ፖሊሶች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አመራሮቹና አባላቱ ለፖሊስ ቃል ሲሰጡ ከሳሙኤል አወቀ ጋር የነበራቸውን ግንኙነት፣ በፓርቲው ውስጥ ያላቸውን ኃላፊነት፣ ሳሙኤልን ማን እንደገደለው የሚመለከቱ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡ ለቅሶ እንዳይደርሱ ከተከለከሉትና ታተው የዋሉት
1. ኢ/ር ይልቃል ጌትነት/ የፓርቲው ሊቀመንበር
2. ይድነቃቸው ከበደ/ የፓርቲው የህግ ጉዳይ ኃላፊ
3. ወሮታው ዋሴ /የፓርቲው የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. ሀብታሙ ደመቀ/ የኦዲትና ኢንስፔክሺን አባል
5. ጌታቸው ሺፈራው/ የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ
6. ጋሻው መርሻ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
7. እምላሉ ፍስሃ/ የብሄራዊ ምክር ቤት አባል
8. ሜሮን አለማየሁ/ አባል
9. ጥላሁን አበጀ/ አባል
10. ጠና ይታየው/ አባል
11. እስጢፋኖስ በኩረጽዮን /አባል
12. ኃይለማሪያም ተክለ ጊዮርጊስ/ አባል
13. ጋሻነህ ላቀ/ አባል
14. ግርማ ቢተው አባልና
15. የመኪናው ሾፌር ናቸው
ከምሽቱ 2 ሰዓት ተኩል ከአዲስ አበባ በመንገድ ትራንስፖርት ሰራተኞችና ትራፊክ ፖሊሶች ህጋዊ መሆኑ ተረጋግጦ ያለፈው እንዲሁም ለአራት ቀን ከፓርቲው ጋር ውል የያዘው መኪና እንዳይንቀሳቀስ ተከልክሎ ከፍተኛ አመራሮቹና አባላቱ ከእስር ተለቀዋል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ ልዑካን ይዘዋቸው የነነበሩ ቁሳቁሶች ለምርመራ በሚል በፖሊስ ተይዘዋል፡፡
በተያያዘ ዜና ከአዲስ አበባ ተነስተው ምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤልያስ ወደ ሌላ ለቅሶ ሲሄዱ የነበሩ ዜጎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ከታፈኑ በኋላ ደጀን ላይ ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ ተፈፅሞባቸው በግዳጅ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደርገዋል፡፡ ተመልሰው ወደ ለቅሶው ቢሄዱ እስከ 10 ሺህ ብር ሊቀጡ እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህ ዜጎች በተያዙበት ወቅት ሰማያዊ ፓርቲ ደብረማርቆስና ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርግ እንደሆነ እንደተገለጸላቸው፤ እነሱም የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ ላይ ትገኛላችሁ ተብለው ተጠርጥረው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡



