Tag Archives: Ethiopia

ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ በድጋሚ ታሰረ

“ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋል”

befekadu-hailu

ከተለያዩ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ድርጅቶች ከዞን፱ ጦማሪያን ስብስብ ጋር በመሆን ሽልማቶችን ያገኘው ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ህዳር 02 ቀን 2009ዓ.ም ጠዋት ከቤቱ በፀጥታ ኃይሎች ወደ ፖሊስ ጣብያ ተወስዷል።

ጋዜጠኛ እና ጦማሪ በፈቃዱ ሚያዝያ 17 ቀን በ2006ዓ.ም ከሌሎች የዞን፱ ጦማሪያን እና ሶስት ጋዜጠኖች ጋር በመሆን በሽብር ወንጀል ተጠርጥሮ የተያዘ ሲሆን ከአንድ አመት ከስድስት ወር የእስር ቆይታ በኋላ የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የተከሰሰበትን የሽብር ወንጀል ወደ አመፅ ማነሳሳት ቀይሮ በ20ሺ ብር ዋስ እንዲወጣ ፈቅዶለት ነበር። በፍርድ ቤቱ ውሳኔ ያልተደሰተው አቃቤ ህግ በበፍቃዱ ላይና ሌሎች ፍርድ በቤቱ ነፃ የለቀቃቸው የዞን፱ ጦማሪያን (ሶልያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔና አቤል ዋበላ) ላይ ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን የፊታችን ማክሰኞ ህዳር 06 ቀን 2009 ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቃቤ ህግ በጠየቀው ይጋባኝ ላይ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በፈቃዱ ኃይሉ ከእስር ከተፈታ አንድ አመት በኋላ ዛሬ ጠዋት ላይ በመኖሪያ ቤቱ እያለ “ኮማንድ ፖስቱ ሊያናግርህ ይፈልጋል” በሚል በፀጥታ ሀይሎች ሊወሰድ ችሏል።

ጋዜጠኛ እና ጦማሪ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በፍቃዱ ኃይሉ ከእስር ከተፈታ በኋላ በአጭር ጊዜ ተወዳጅ በሆነችውና ከ10 እትም በኋላ ከገበያ በወጣችው ውይይት መፅሄት ላይ በዋና አዘጋጅነት ይሰራ እንደነበር ይታወቃል።
ምንጭ፡- EHRP.

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ለ3ኛ ጊዜ ለብይን ተቀጠረ

‹ፌስቡክን ጨምሮ በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ግንቦት ሰባት ከተባለው አሸባሪ ቡድን አመራሮች ጋር ግንኙነት አድርገሃል› በሚል የሽብር ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኘው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው ለ3ኛ ጊዜ ለብይን ቀጠሮ ተሰጥቶበታል፡፡

Getachew Shiferaw

ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓ.ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዳኞች ጉዳዩን በጽህፈት ቤት የተመለከቱት ሲሆን፣ ዳኞቹ መዝገቡን መርምሮ ብይን ለመስጠት ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለጽ ለህዳር 28 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥተዋል፡፡

በሌሎች መዝገቦች ከዛሬ ቀደም ቀጠሮ የነበራቸውን ተከሳሾች ሳያቀርብ የቆየው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጋዜጠኛ ጌታቸውን ጨምሮ ሌሎች በዕለቱ ቀጠሮ ያላቸውን ተከሳሾች ፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡

ተከሳሹ ጌታቸው ሺፈራው ጉዳዩ ሲታይ የቆየው 14ኛ ወንጀል ችሎት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ አሁን ላይ ጉዳዩን የሚያየው ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህም ቀደም ሲል በነበረው ችሎት በአንድ ዳኛ ይታይ የነበረው የክስ ጉዳዩ በአሁኑ ችሎት በሦስት ዳኞች የሚታይ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሺፈራው የቀረበበትን ክስ መከላከል ይገባዋል ወይስ መከላከል ሳያስፈልገው በነጻ ይሰናበት የሚለውን ብይን ለመስማት ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሲሰጥ ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነው፡፡ ተከሳሹ ላይ አቃቤ ህግ ከሰነድ ማስረጃዎች ሌላ የሰው ምስክር አላቀረበበትም፡፡

ጌታቸው ታህሳስ 15 ቀን 2008 ዓ.ም ለእስር ከተዳረገበት ዕለት ጀምሮ እስካሁን ጉዳዩን በእስር ቤት ሆኖ እየተከታተለ ይገኛል፡፡
ምንጭ፡- EHRP.

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኖ ተመረጠ

(አዲስ ሚዲያ) የበርካታ ዓለም አቀፍ የሩጫ ውድድር ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ሆኖ ተመረጠ፡፡ ምርጫው የተደረገው ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም. አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ በጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ሲሆን፤ በውድድሩም አቶ ተፈራ ሞላ እና አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡ በመጨረሻም የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በመወከል የተወዳደረው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ከነበሩት አምስት ድምፆች መካከል የዘጠኙን በማገኘት በማሸነፉ ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን እንዲመራ በፕሬዘዳንት ተመርጧል፡፡

haile-gebreselassie

አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ    ( ፎቶ ክሬዲት ቢቢሲ)

ከአትሌት ሻለቃ ኃይሌ በተጨማሪ ለስራ አስፈፃሚነት አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራ፣ አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም በእጩነት ቀርበው ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ለስራ አስፈፃሚነት አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው አትሌት ገብረእግዚአብሔር ገብረማርያም መሆኑ ታውቋል፡፡

ቀደም ሲል ለሀገሪቱ የአትሌቲክ ውጤት መውረድ ከፌዴሬሽኑ በተጨማሪ በጋራ ሲሰራ የነበረው የኢትዮጵያ አትሌቶች ማኀበር አመራር የነበሩት አትሌት መሰረት ደፋር እና አትሌት ስለሺ ስህን በተለይ ከአትሌቶች ተመሳሳይ ቅሬታ ሲቀርብባቸው የነበረ ቢሆንም፤ በአዲስ ስራ አስፈፃሚ ውስጥ በድጋሚ አባል እንዲሆኑ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡

በተለይ ባለፈው በለንደን ኦሎምፒክ እና በቀርቡ በተካሄደው የሪዮ ዲ ጄኔሪዮ ኦሎምፒክ የአትዮጵያ አትልቲክስ ዓለም አቀፍ የኦሎምፒክ ውድድር ባልተለመደ መልኩ እየቀነሰ በመሄዱና ብት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ለውድድር ለምን አልተጋበዙም በሚል የስፖርቱ ደጋፊና አፍቃሪ እንዲሁም አትሌት ኃይሌ እና አትሌት ገብረእግዚአብሔርን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ስመ ጥር አትሌቶች በይፋ ቅሬታ ማሰማታቸው ይታወሳል፡፡

የአትሌት ኃይሌ ለፕሬዘዳንት መመረጥና የአትሌት ገብረእግዚአብሐየር ለስራ አስፈፃሚነት መመረጥ ከስፖርቲ ደጋፊና አፍቃሪ ኢተዮጵያውያን በተጨማሪ ከዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ማኀበርም የእንኳን ደስ ያላችሁ ድጋፍ ተችሯቸዋል፡፡

የጣይቱ ልጆች ፤የኢትዮጵያ ደም መላሾች

dr-admasu-gebeyehu

አድማሱ ገበየሁ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር)
(ጥቅምት 25 ቀን 2009 ዓ.ም)

ጣይቱ አሰኔ በወሎ ክፍለ-ሀገር በቦረና አውራጃ በጫቀታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጅሩ ጉጣ ከተባለው ቀበሌ ተወለደች። ገና ልጅ እንዳለች ባሻ ዘለቀ ላቀውን አገባች። ዘለቀ የተወለደው በወሎ ክፍለ-ሀገር፡ ቦረና አውራጃ፡ ጫቀታ ም/ወረዳ፡ ልዩ ስሙ ገዛዛ አቦ ከተባለው ቀበሌ ነው። ጣይቱና ዘለቀ ሁለቱም የጫቀታ ተወላጆች ሲሆኑ መኖሪያቸው ጅሩ ጉጣ (ከጣይቱ ትውልድ ቦታ) ነበር።
የጣይቱ አሰኔ አባት አሰኔ ወዳጅ (አባ ጨፍልቅ) ይባላሉ። አባ ጨፍልቅ የንጉሥ ሚካኤል ባለሟልና የአንድ ክፍለ ጦር አዛዥ ነበሩ። አባ ጨፍልቅ አድዋ ጦርነት ላይ ሲዋጉ ጥይት አልቆባቸው አንድ ጠላት በአለንጋ መተው ገድለዋል ይባላል። ይህንን በተመለከተ፡
“ሰው ሁሉ የሚገል በጎራዴ ነው፤
ሰው ሁሉ የሚገል በመሣሪያ ነው፤
የእኛ አሰኔ ወዳጅ በአለንጋው ነው።”
የሚል ተገጥሞላቸዋል። አባጨፍልቅ “የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ባሕር ጠረፍ ነው።” ይሉ እንደነበር ይነገራል። አባ ጨፍልቅ በዘወትር ፀሎታቸው “ድንበር አልፎ የገባውን ጠላት (ጣልያና ፈረንሳይን) ሳናባርር ሞትን እንዳትልክብኝ፣ ያዝልኝ።” ይሉ ነበር ይባላል።

ጣይቱ በ1904 ዓ.ም በላይ ዘለቀን ወለደች። ከሁለት ዓመት በኋላም በ1906 ዓ.ም እጅጉ ዘለቀን ወለደች። እጅጉ እንደተወለደ የጣይቱ ባለቤት ባሻ ዘለቀ ከቤተሰብ ተለይቶ ወደ ዳር አገር ዘመተ። ብዙም ሳይቆይ ጣይቱ መሸሻ አደምን አገባች። መሸሻ አደም የተወለደው በወሎ ክፍለ-ሀገር፡ ቦረና አውራጃ፡ በሜታ ም/ወረዳ፡ ልዩ ስሙ ወርቄ አቦ በተባለው ቀበሌ ነው። ጣይቱ ሦስተኛ ልጅ አያሌው መሸሻን በ1908 ዓ.ም ከመሸሻ ወለደች።
ጣይቱ ሁለት ባሎች አከታትላ ብታገባም አብራ ለመኖር ግን አልታደለችም። የበፊተኛው ማለትም ዘለቀ ላቀው ከልጅ ኢያሱ ሠራዊት ጋር ተቀላቀለ። በጥቅምት ወር 1909 ዓ.ም ደግሞ የአያሌው አባት መሸሻ አደም የንጉሥ ሚካኤልን የዘመቻ ጥሪ ተቀብሎ ሰገሌ (ሸዋ ደብረ ብርሃን አጠገብ) በተደረገው ጦርነት ለመሳተፍ ዘመተ። ግን አልተመለሰም በዚያው ቀረ።

ስለ ጣይቱ ልጆች (በላይ፡ እጅጉና አያሌው) ታሪክ መነሻ ለማግኜት ይረዳ ዘንድ ስለ ባሻ ዘለቀ ማወቅ ይጠቅማል። ባሻ ዘለቀን ለመዝመት ያነሳሳው ልጅ ኢያሱ የኢትዮጵያን ወሰን መልሶ እስከ ባሕር ጠረፍ ለማድረስ ብርቱ ምኞት እንደነበረው ከአማቱ (ከጣይቱ አባት ከሀሰኔ ወዳጅ) ይሰማ ስለነበር ነው። ልጅ ኢያሱ ከመንገሡ በፊት ጣልያንና ፈረንሳይን ከአገራችን በማባረር ጠረፋችንን ለማስከበር አስቧል የሚል ወሬ በስፋት ይሰማ ነበር። ይንንም ለማሳካት ልጅ ኢያሱ ከጀርመንና ከቱርክ ጋር ተፈጣጥሟል ተብሎም ተወርቶ ነበር። ባሻ ዘለቀ ላቀው ከልጅ እያሱ ሠራዊት ጋር ተቀላቀለ። ከልጅ ኢያሱ ጋር ሆኖ በአፋር፡ በጅቡቲ መስመር (ሶማሌ)፡ እና በሐረር አካባቢ ሲንቀሳቀስ ቆዬ።

መስከረም 17 ቀን 1909 ዓ.ም የመስቀል ዕለት ባሻ ዘለቀ ከልጅ ኢያሱ ጋር ሐረር ነበር። አኩለ ቀን ሲሆን “የሸዋ ሰው አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ አድርጎ አዲስ መንግሥት አቋቁሟል፤ ወይዘሮ ዘውዲቱን ንግሥት፤ ደጃማች ተፈሪን ደግሞ አልጋ ወራሽ አድርጎ ሾሟል” ተብሎ ተነገረ። ብዙም ሳይቆይ የኢያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል የልጃቸውን ሥልጣን ለማስመለስ ወደ ሸዋ ዘምተዋል የሚል መልእክት ደረሰ። የልጅ ኢያሱም ሠራዊት ከንጉሥ ሚካኤል ሠራዊት ጋር ለመቀላቀል ገሠገሠ። ይሁን እንጂ ንጉሥ ሚካኤል በለስ እንዳልቀናቸውና እንደተማረኩ ተረጋገጠ።

ለባሻ ዘለቀ ሌላ ተጨማሪ መርዶ ደረሰው። “መስከረም 22 ቀን 1909 ዓ.ም. በቤተ መንግሥት ሹም ሽር ሆኖ የሰላሌው ገዢ ደጃዝማች ካሣ ኃይሉ በግዛታቸው በሰላሌና በላስታ ላይ እንሳሮና መራቤቴ፣ ደራ፣ ሚዳ፣ ቦረና ተጨምሮላቸው ራስ ተባሉ።” የሚል መረጃ ደረሰው። ባሻ ዘለቀ ወደ ቦረና ቢመለስ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ ገመተ። ያለው አማራጭ እስከመጨረሻው ከልጅ ኢያሱ አለመለየት ነው ብሎ ወሰነ።

ባሻ ዘለቀ ከልጅ ኢያሱ ጋር በወሎና በትግራይ አካባበቢ ለአምስት ዓመታት ያህል ሲንቀሳቀስ ቆዬ። ልጅ ኢያሱ ተይዞ ኮረማሽ ታሰረ፤ ብዙም ሳይቆይ በኅዳር 29 ቀን 1914 ዓ.ም ወደ ፍቼ ተዛውሮ በሰላሌ ገዢ በራስ ኃይሉ ጠባቂነት እንዲታሰር ተደረገ። ከልጅ ኢያሱ መታሰር በኋላ ባሻ ዘለቀ ወደ ቦረና ሄዶ የዘመድ አዝማድ ከለላ ማግኘትን መረጠ። በጫቀታ ወረዳ ልዩ ስሙ ጣቀት መደሎ ከተባለው ቀበሌ ተቀምጦ እንዳለ አንድ ሰው በእጁ ጠፋበት (ሞተበት)። ከዚያም ሸፈቶ በጎጃም ክፍለ ሀገር በቢቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ ልዩ ስሙ ለምጨን ከተባለው ቀበሌ እንደተቀመጠ ከደብረማርቆስ በታዘዘ ጦር ተገደለ።

በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ አባታቸው ሲሞት ገና የ10 እና የ12 ዓመት ልጆች ነበሩ። እድሜያቸው ከፍ ሲልና አካላቸው ሲጠነክር አባታቸውን በጥቆማ መርቶ ያስገደለውን ግራዝማች ደርሰህ የተባለውን ሰው ገድለው ጫካ ገቡ። የእናታቸው ልጅ ታናሽ ወንዳማቸው አያሌውም በሽፍትነቱ ተቀላቀላቸው።
ሦስቱ ወንድማማቾች በሽፍትነት በአባይ ወንዝ ዳርቻ ባለው በርሃ በመንቀሳቀስ ከየዘመዱ ስንቅ እያሰባሰቡ ጥቂት ዓመታት እንዳሳለፉ የጣልያን ጦር ደብረማርቆስ መግባቱ ተሰማ። እነበላይም የእናትና የአባታቸውን ወገን ሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተመካከሩ። ጣልያን በ1928 ዓመት አገራችንን ሲወር የጣይቱ ልጆች በላይ ዘለቀ 24፡ እጅጉ ዘለቀ 22፡ እና አያሌው መሸሻ 20 ዓመታቸው ነበር። የአክስታቸው ልጅ ሺፈራው ገርባውም 17 ዓመቱ ነበር።

በላይም ዘለቀም እንዲህ ሲል ጠየቀ። “ፋሽስት ጣልያን እየገፋ መጣ። ንጉሡም ከማይጨው ሸሽተው አዲሰ አበባ ከገቡ በኋላ፤ የሚወልዷቸውንና የሚወዷቸውን ይዘው፤ የሚችሉትን ያህል የኢትዮጵያን ገንዘብ ዘርፈው፤ ያልቻሉትን ለዘራፊ አጋልጠው፤ ከነቤተሰቦቻቸው ከድተው ባሕር ማዶ ሄዱ ይባላል። ስለዚህ እኛስ ይህንን የመጣ እንግዳችንን እንዴት ነው የምናስተናግደው አስኪ መላ አምጡ።” ብሎ ጠየቀ። በመጨረሻም ከብዙ ምክክር በኋላ የተሰበሰበው ቤተሰብና ዘመድ ዝማድ በሙሉ ጠላትን ለመፋለም ወሰነ።

እነ በላይ በመቀጠልም በየአካባቢው ላሉት ሽፍቶች መልእክት ላኩ። “ሽፍትነትም ወግ የሚኖረው አገር አማን ሲሆን ነው። ሁላችንንም የሚያጠፋ የከፋ የውጭ ጠላት መጥቶብናል። ሁላችንም አንድ ልብ ሆነን ልንመክተው ይገባል። የሚያድኑን ደመኞቻችን ከጠላት የከፉ አይሆኑም። የእኛው ወገኖች ናቸው። ሽማግሌ እየላክን አገር አማን ሲሆን የጉማ ሥርዓት ፈጽመን (ማንኛውም የሚጣልብን ካሳ ክሰን) ለመታረቅ መቁረጥ አለብን። ደመኞቻችንም እኛም (ሽፍቶቹ) አንድ ላይ ካልሆንን ከምድር በጠመንጃና በመድፍ ከሰማይ በሮቢላ የመጣብንን ጠላት መመከት አንችልም። እንግዳችን በተደጋጋሚ አገራችንን የደፈረው ጠላታችን ጣልያን ነው። ሕፃን፡ ሴት፡ ሽማግሌ የማይለይ አረመኔ ነው። ሃሳባችንን የወደዳችሁ ሁሉ የሚቀጥለው እሁድ … እኛ ዘንድ መጥታችሁ እንመካከር” የሚል ደብዳቤ ከእነ አንባቢው ላኩ። (ሚስጢሩን ጠላት እንዳይደርስበት በማሰብ የመሰብሰቢያ ቦታው ስም የሚነገረው በቃል ብቻ ነበ፡፡)

በስብሳው ቀን በተባለው ቦታ የአካባቢው ሽፍታ ሁሉ ልቅም ብሎ መጣ። በላይም ዘለቀም እንዲህ ሲል ተናገረ። “እኛ የጣይቱ ልጆች፡ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ በሙሉ የአባይን ወንዝ ይዘን፡ የአለቱን ድንጋይ ተንተርሰን፡ አሸዋውን ለብሰን፡ ዋሻውንና ተራራውን ምሽግ አድርገን፡ የመጣውን ጠላት ለመመለስ ወስነናል። ከዚህ ፍንክች አንልም። እናት ሀገራችን ስትደፈር ከማየት ሞታችንን እንመርጣለን። የፈራህ ልቀቀን። ለአገር ለወገንህ ለመሰዋት የምትፈልግ ሁሉ እኛን ተከተለን።” ብሎ በጣይቱ ልጆች፡ ቤተሰብና ዘመድ አዝማድ ስም ቁርጥ ያለ ጥያቄ አቀረበ። ከዚያም ተሰበሰበው ሽፍታ ሁሉ ገባላቸው። ሽፍታው ሁሉ ላይከዳ መሣሪያውን እንዳጎረሰ አጋድሞ ዮሔ ቢሰት ዮሔ አይሳተኝ በማለት እየማለ ቃል ገባላቸው። በወቅቱ እስከ 200 የሚደርስ የሽፍቶች ሠራዊት አሰባሰቡ። በላይ ዘለቀንም የጎበዝ አለቃ አድርገው መረጡት። በኋላም ሌሎች ሽፍቶች ካያለበት እየወጡ ገቡላቸው።

ከበላይ ጋር ሆነው ጣልያንን ለመፋም ቆርጠው የተነሱት ጀግኖች ለጣልያን ካደሩት ባንዶች ጋር ተደጋጋሚ ፍልሚያ አደረጉ። ተደጋጋሚ በለስም ቀናቸው። ባደረጓቸው ጦርነትም ከገደሏቸውና ከማረኳቸው ባንዶች ላይ ብዙ መሣሪያ ገፈፉ። በርካታ ምርኮኞችንም ወደ አርበኛነት ለወጧቸው። ቀስ በቀስም የቦረና፡ የደራ፡ የደብረ ጉራቻ፡ የእንሳሮ፡ ሕዝብ አነ በላይን ተቀላቀለ። አብዛኛው የምሥራቅ ጎጃም ሕዝብም በትግሉ ተቀላቀለ፤ አርበኞችንም አቅፎ ደግፎ ያዘ።

patriot-belay-zeleke

በላይ ዘለቀ በውጊያ ለተማረኩት ባንዳዎች የሚያደርጋቸው ንግግሮች የብዙ ባንዳዎችን አሰላለፍ ለወጠ። ንግግሩም፡- “እናንተ ከጣልያን ታዛችሁ አገራችሁን በመክዳት በተደረገው ጦርነት ከሞት ተርፋችሁ የተማረካችሁ፣ ኢትዮጵያዊ የሆናችሁ ወገኖቻችን ሁሉ፣ አሁን በእኛ በኩል ምረናችኋል። እናት ሀገርህና ወገንህን የምትል ተከተለን፣ ወይም አርሰህ ብላ። ነገር ግን ሁለተኛ ለጠላት ገብተህ ብትገኝ ነገ እኛገኝሃለን።” የሚል ነበር። በዚህ አቀራረብም በየካቲት ወር 1929 ብቻ ደረቤን፡ ቅንቧትን፡ ባሰን፡ ሊበንን፡ ድድሜትን፡ ደጀንን፡ አምበልን፡ በጠቅላላው አስከ ጨሞጋ ያለውን አሣምነው እንዲከተላቸው አድርገዋል። በ1933 ዓ.ም ጦርነቱ ሊያበቃ ሲቃረብ የነበላይ ጦር በ102 ጦር አዛዦች የሚመራ 111, 000 ሠራዊት ነበረው። በሠራዊቱም ውስጥ የማዕረግ ስም የተሰጣቸው አርበኞች 986 ደርሰው ነበር።

በ1930 ዓ.ም የጣልያን ሠራዊት የበላይን ሚስት ሸክሚቱ አለማየሁንና እህቷን ዘውዲቱ አለማየሁን ገድለው ልጁን የሻሽወርቅ በላይን ማርከው ወሰዷት። ለበላይ ዘለቀም ልጁን ማግኘት ከፈለገ ማድረግ ያለበትን የሚያሳውቅ መልእት በጣልያን መንግሥት ስም ላኩለት።

በላይም ለጣልያን መንግሥት መልእክት የሰጠው መልስ እንደሚከተለው ነበር።“ይድረስ ለጣልያን መንግሥት ሰላም ላንተ ይሁን። የላክልኝን እንግዶች እነ ቀኛዝማች እጅጉ ለማን በአክብሮት ተቀብዬ በማስተናገድ ሥፍራ ሥፍራ ሰጥቻቸዋለሁ። ላንተ ግን ትርጁማን (አስተርጓሚ) ብለህ የላከውን እሌላ ቦታ ስትልክ እንዳይቸግርህ መልሼ ልኬልሃለሁ። ልጅህን እመልስልሃለሁ ለምትለው፣ ለአንድ ልጅ ብዬ እናት ሀገሬን ኢትዮያን ከድቼ ከአንተ ጋር አልታረቅም። ከዛሬ ጀምሮ በእኔ በኩል ያለውን ምኞትህን አንሳ። እኔን ፈልገህ ማጥፋት እንጂ አንዲት ልጅ ወስዶ ማስጨነቅና ማጉላለላት ደስ የሚልህ ከሆነ እንደፈለግህ አድርጋት። ሲሆን ለሷም የፈጠራት አምላክ እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ከአንተው እጅ ላመጣት እችል ይሆናል። ጎጃምን በእንደራሴነት ልስጥህ የምትለው አንተ የሰው አገር ሰው ከምትሰጠኝ እኔው ሀገሬን አስተዳድረው የለምዎይ። የቦለቲካ ወሬህን ከምትነዛ የኢትዮጵያ አርበኛ እየቆማመጠ ለአሞራ ከሚሰጥህ፣ በዱር በገደሉ ወድቀህ ከምትቀር በመጣህበት መንገድ አገርህ ግባ!” ይላል።

የሻሽርቅ በላይም በ1930 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣልያ ማርኮ እስከ ሮማ ተወስዳ በደረሰባት እንግልትና ሥቃይ ምክኒያት እግሯ ሽባ ሆነ። ከዚያም ወደ ቢቸና ተመልሳ በጣልያን ካምፕ በከባድ ጥበቃ ስር ሆነች። በግንቦት ወር 1932 ዓ.ም በታሰረች በሁለት ዓመቷ በአባቷ ብርታት ከቢቸና እስር ቤት አመለጠች።

በመስከረም ወር 1933 ዓ.ም ደጃዝማች ከበደ ተሰማ ከንጉሡ የተላከው ደብዳቤ አመጡ። መልእክቱም፡- “ይድረስ ለልጅ በላይ ዘለቀ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን ሥራህንና ጥንክርናህን ሰምቻለሁ። በጣም የሚያስደስትና የሚያኮራ ሥራ በመሥራትህ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል። እኔም በመንገድ ላይ ነኝ። መጣሁ አይዞህ ጠንክር። የእግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆና በዋናው ቤተመንግሥቴ ለመግባት የበቃሁ እንደሆነ ውለታህን በእጥፍ አድርጌ እመልሳለሁ። እስከዚያው ሰው ላክና መሣሪያ ከዚህ ከከሰላ አስወስድ። በተረፈ ጠንክር አይዞህ!” የሚል ነበር።
ጣልያን ተሸንፎ በ1933 ዓ.ም ከአገራችንን ሲወጣ የጣይቱ ልጆች በላይ ዘለቀ 29፡ እጅጉ ዘለቀ 27፡ እና አያሌው መሸሻ 25 ዓመታቸው ነበር። የአክስታቸው ልጅ ሺፈራው ገርባው ደግሞ 22 ዓመቱ ነበር።

በላይ ዘለቀ በደማርቆስ ከተማ ከንጉሡ ጋር በተገናኘ ጊዜ የሚከተለውን ተናግሮ ነበር። “በአምስቱ ዓመት የጠላት ወረራ ዘመን ውስጥ ከጣልያን ፋሽሽት ጋር በሰልፉ ያይዋቸውን ወንድሞቼን ይዤ በምዋጋበት ጊዜ እንደሥራ ችሎታቸውና እንደየአገልግሎታቸው የማዕረግ ስም ሰጥቻለሁ። ስለሆነም ሕዝቡን ለማስተባበርና ጦሩን ለማጠናከር፣ የጠላትንም ቅስም ለመስበርና ለማጥቃት ችያለሁ፤” ሲል ተናገረ።
ንጉሡም የበላይን ንግግር ካዳመጡ በኋላ፤ “አንተ የማዕረግ ስም የሰጠኸውን እኔ ከመጨመር በስተቀር አልቀንስም፤ መርቄልሃለሁ። ለእኔ የትናንትናው ሰልፍህና ሁኔታህ ብቻ ይበቃኛል። ደስታዬ ወሰን የለውም። በዋናው ቤተመንግሥቴ እንደገባሁ ያንተን ውለታ እመልሳለሁ፤” ሲሉ ተናገሩ። ቀጥለውም “አዲስ አበባ አብረኽኝ እንሂድ፤ አድርሰኝ፤” ሲሉ ንጉሡ ተናገሩ።

በላይም “እኔ አሁን አብሬዎት አልሄድም። ያለኝም እረፍት አሁን ነው። በጦር ሜዳም፡ በየበረሃው አጥንታቸው ረግፎና ተከስክሶ፣ ደማቸው ፈሶ፣ ሥጋቸው ለአሞራ ሲሳይ በመሆን ለአገራችን ሲሉ የተሰውትን የወንድሞቼን አጽም ከየረገፈበት ሰብስቤ በሥርዓት አስቀብራለሁ። ስለዚህ ከእርስዎ ዘንድ ወደፊት በጥቅምት ወር እመጣለሁ።” ብሎ ተናገረ። ንጉሡም “ጥሩ ሃሳብ ነው። መልካም ነው። እኔም ሃሳብህን እደግፋለሁ፤” ብለው ተናገሩ።

ጥቅምት ወር 1934 ዓ.ም በላይ፡ እጅጉና አያሌው አዲስ አበባ መጡ። ከዚያም የኢያሱን ልጅ ዮሐንስ ኢያሱን ለማንገሥ አድማችኋል በማለት በክቡር ዘበኛ ወታደሮች ተይዘው ታሰሩ። ጉዳዩ ሲጣራ እነበላይ በሤራው እንደሌሉበት ተረጋገጠ። ከጥቅምት እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ ዘጠኝ ወር ሙሉ ከአዲስ አበባ እንዳይወጡ በግዞት ቆዩ። በመጨረሻም ንጉሡ ቀደም ብለው ደብረማርቆስ ከበላይ ዘለቀ ጋር ሲገናኙ ለሠራዊቱ አዛዦች በበላይ ዘለቀ የተሰጣቸውን ማዕረግ መርቄያለሁ ያሉትን ለወጡት (ካዱ)። በአርበኛ መሪዎች የተሰጠው ማዕረግ ሁሉ ተቀነሰ። አስከነአካቴውም አንዳንዶቹ የተሰጣቸው ማዕረግ ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ። ለበላይ ዘለቀም የደጃዝማችነት ማዕረግ ተሰጠው። ንጉሡ ደብረማርቆስ ሲደርሱ የገቡትን ቃል፡ አዲስ አበባ ሲገቡ መቀየራቸው (መካዳቸው) የጣይቱን ልጆች በጣም አስከፋ፤ አስቆጣ።

የጣይቱ ልጆችም አዲስ አበባ የመጡበት ጉዳይ ባለመሳከቱ እያዘኑ አኩርፈው ወደ ቢቸና ተመለሱ። በኋላም ንጉሡ በላይን አዲስ አበባ እንዲመጣ ቢልኩበት አሁን አይመቸኝም አልመጣም ብሎ ቀረ። እነበላይ የመጣው ቢመጣ ወደ ንጉሡ ላለመሄድ ወስኑ። የቅርብ ዘመድና ወዳጅ ያካተተ ሠራዊት አሰባስበው በተጠንቀቅ ሲጠባበቁ ቆዩ። (እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት በጠላት ጊዜ የነበረው ያ ሁሉ ሠራዊት ከሁለት ዓመት በፊት የነበረው የአርበኞን በ1933 ዓ.ም መበተኑን ነው።

እንደታሰበውም በመጋቢት ወር 1935 ዓ.ም ከንጉሡ የታዘዘ በርካታ ሠራዊት ያለው ጦር እነበላይን ሶማ ደጋ ከተባለው ትልቅ ተራራና አምባ ላይ እንደመሸጉ ከበባቸው። ከንጉሡ ለሠራዊቱ የተሰጠው ትዕዛዝ፡ እነበላይን ከተቻለ ይዘው እንዲያመጡ ካልተቻለ ደግሞ ባሉበት እንዲደመሰሱ ነበር። የነበላይ ሠራዊት አሥር እጥፍ ቁጥር ካለው ከንጉሡ ሠራዊት ጋር ለ15 ቀናት ሌት ከቀን ተዋጋ። እነበላይ ጊዜው በረዘመ መጠን የውሃ ጥም ቢበረታባቸውም የያዙት ቦታ አመቺ በመሆኑ በርትተው ሲከላከሉ ሰነበቱ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከንጉሡ ለበላይ የተላከ ደብዳቤ መጣ። ደብዳቤውም፡ “ይድረስ ለደጃዝማች በላይ ዘለቀ ሰላም ለአንተ ይሁን። በሰደድናቸው ዳኞች በሊጋባ በቀለ፡ በፊታውራሪ ይልማ በሺ፡ እና በአቶ ዳዊት አማካኝነት እንድትመጣ። እኛ በክፉ አናይህም። በክፉ ብናይህ ውድ ልጃንን ልዑል መኮንን ይሁንብን።” የሚል የመሃላ ደብዳቤው ላይ “ሞኣ አንበሳ ዘዕምነ ነገደ ይሁዳ እኛ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ስዩመ እግዚአብሔር” የሚል ማህተም ያለበትን ደብዳቤ ላኩ።

ይሁን እንጂ መተማመን ስለጠፋ ጦርነቱ እንደገና ተቀሰቀሰ። በሁለቱም ወገን ብዙ ሰዎች ሞቱ። እጅጉ ዘለቀ በከባድ ሁኔታ ግራና ቀኝ ታፋውን ተመታ። የጋሜዎች አዛዥ የነበረውም ልጅ ሺፈራው ገርባው ሞተ። በመጨረሻም በላይ የወንድሙን የእጅጉን ሕይዎት ለማትረፍ ሲል እጁን ለመስጠት ወሰነ።
በግንቦት ወር 1935 ዓ.ም አዲስ አበባ ከገቡ በኋላ 12 ሚኒስትሮች ለሦስት ወር ያህል በዋናው ቤተመንግሥት ሲመረመሩ ቆይተው ውሣኔ ተሰጠ። ውሳኔውም፡- አንደኛ፡ በላይ ዘለቀና እጅጉ ዘለቀ ቢቸና ተወስደው እንዲሰቀሉ። ሁለተኛ፡ አያሌው መሸሻና ሌሎች 15 የጦር አዛዦች በእድሜ ይፍታህ እንዲታሰሩ ተወሰነባቸው። ንጉሡም በሚኒስትሮች የተሰጠውን ውሳኔ አፀደቁት፡፡

በፍርዱ መሠረት በላይና እጅጉ ለመሰቀል ወደ ጎጃም ጠቅላይ ግዛት ሲጓዙ እንዳለ አባይ ሲደርሱ የጎጃምና የቦረና ሕዝብ አንጎራጉሯል ማለትን ስለሰሙ እረብሻ እንዳይፈጠር በማለት የአባይ ውሃ ሞልቶ አላሻግረን ብሎ ከለከለን አሰኙ። ከአባይ መልሰው አምጥተው በወሊሶ ከተማ በደጃዝማች በቀለ ወያ እጅ እንዲታሰሩ ላኳቸው። ቀጥሎም በቤተመንግሥት ግቢ ውስጥ እንዲታሠሩ ተደረገ። በታኅሳስ ወር 1937 ዓ.ም ከእስር ቤት ሰብረው ወደ ጎጃም ሲሄዱ ተያዙ። ከዚያም በላይ ዘለቀ በ33 ዓመቱ፣ እጅጉ ዘለቀ ደግሞ በ31 ዓመቱ ጥር 12 ቀን 1937 ዓ.ም አድስ አበባ ውስጥ ተሰቀሉ።

ስለእነ በላይ መሰቀል በርካታ ግጥሞች ተገጠሙ በዘፈንም ተሰምተዋል፤ ከነዚህም አንዱ እንዲህ የሚል ነበር።
“ተሰቀለ ቢሉኝ ሽጉጡ ነው ብዬ፣
ተሰቀለ ቢሉኝ ጠመንጃ ነው ብዬ፣
ተሰቀለ ቢሉኝ ዝናሩ ነው ብዬ፣
ለካስ በላይ ኖሯል ትልቁ ሰውዬ!”
ሌላው ደግሞ፡-
“አሁን ምን ያደርጋል እኔ ባበጃጅ፣
መማርህ ነበረ ላገር የሚበጅ፤”
እንዲሁም፡
ሰው ማለት፣
ሰው የሚሆን ነው፣
ሰው የሌለ ዕለት።

ወራሪ ጠላትን ለአምስት ዓመታት ያለመታከት ሌት ከቀን ወጥረው መግቢያ መውጫ ያሳጡት ጀግኖች የጣይቱ ልጆች በራሳችን መሪዎች እንደዋዛ በአደባባይ ተሰቀሉ። በዚህም ከጣይቱ ልጆች ጋር ሆነው ጣልያኖችንና ባንዳዎችን አሸንፈው አገራችንን ለድል ያበቁት አርበኞች ሁሉ በሁኔታው በጣም ተሸማቀቁ። አርበኝነትም በይፋ በአደባባይ የሚያስፎክር ጀብዱ መሆኑ ቀረ። እነበላይ ከተሰቀሉ በኋላ በርካታ አርበኞች በተሰጣቸው ማዕረግ እንዳይጠሩ ለቤተሰብና ለዘመድ አዝማድ አሳወቁ። በመሆኑም በቦረና ውስጥ በጣልያን ወረራ ጊዜ በተሰጠ የአርበኝነት ማዕረግ የሚጠራ አልነበረም። ከነበላይ ወዲያ ብሎ ሁሉም እርም ብሎ እርግፍ አድርጎ ተወው።

የጣይቱ ልጆች የትውልድ ሐረግ

በላይ ዘለቀ (የአርበኞች ጠቅላይ አዛዥ) ጥር ወር 1937 ዓ.ም በተወለደ በ33 ዓመቱ ተሰቀለ። እጅጉ ዘለቀ (የአርበኞች ምክትል ጠቅላይ አዛዥና የበረንታ ጦር አዛዥ) ጥር ወር 1937 ዓ.ም በተወለደ በ31 ዓመቱ ተሰቀለ። ሺፈራው ገርባው (የጋሜዎች አዛዥ) መጋቢት ወር 1935 በንጉሡ በታዘዘው ጦር ተገደለ። አያሌው መሸሻ (የመትረየስ ተኳሾች አዛዥ) ከ 1934 ዓ.ም ጀምሮ ለሰላሳ ዓመታት ቦንጋ በእስርና በግዞት ቆይቶ በ1964 ዓ.ም ተለቆ፣ በ1983 ዓ.ም አረፈ።

ጣይቱ አሰኔ … አባቷን አሰኔ ወዳጅን፤ ወንድሟን ለገሠ አሰኔን፣ ባሎቿን ዘለቀ ላቀውንና መሸሻ አደምን፣ ልጆቿን በላይ ዘለቀን ፡ እጅጉ ዘለቀን በሞት ተነጠቀች። ከሞት የተረፈው ሦሰተኛውና የመጨረሻው ልጇም አያሌው መሸሻ በእድሜ ልክ አሥራት ተፈርዶበት ወህኒ ቤት ገባ (1964 ዓ.ም ሲፈታም በሕይዎት አልነበረችም።) ጣይ እስከ ሕይወቷ መጨረሻ ድረስ ሁለት ስሜቶች ሲፈራረቁባት ነበር። በአንድ በኩል በቤተሰቦቿ በደረሰው እልቂት ምክኒያት ቀኑ ሲጨልምባትና ሃዘኑም ሲበረታባት ለጉድ የፈጠረኝ ምነው እኔን ቢያስቀድመኝ ትላለች። በሌላ ቡል ደግሞ የቤተሰቦቿ የአርበኝነት ገድል ልቧን በኩራት ይሞላዋል። ጣይቱ ባለፈችበት ሁሉ ከሕዝብ የሚሰጣት ከበሬታ በልጅቿ አኩሪ ታሪክ ምክኒያት በመሆኑ ፈጣሪን ታመሰግነናለች። ሞት ላይቀር! እንደደኔ ማን የታደለ እናት አለ ትላለች ጣይቱ፤ ወዲያው ደግሞ እንደ ሰው ልጅ ሳይዘሉ፡ ሳይጨፍሩ …. ትልና ለቅሶዋን ታቀልጠዋለች።

ጣይቱ ነፍስ ያወቁ ዘመዶቿን ብታጣም የልጅ ልጆቿን ማሳግን ሥራዬ ብላ ተያያዛው ነበር። የልጅ ልጆቿም የአባቶቻቸውን ታሪክ እንዲያውቁ የተቻላትን ያህል ሞክራለች። ስለ ጦርነቱና ስለ ልጆቿ ገድል በራሷ ብዙም ልትነግራቸው አትችልም ነበር። ይሁን እንጂ በተለያዩ ጊዜያት አብረው ዘምተው የነበሩ ዘመድ አዝማድ ወደ ሠፈሯ ሲመጡ ስለ ልጆቿ የአርበኝነት ገድል ለልጅ ልጆቿ እንዲያወጉላት ታደርግ ነበር። በተጨማሪም እሷ በራሷ ለልጅ ልጆቿ ያስተማረቻቸው ቁም ነገር ነበረ። ይኸውም የልጇን የትውልድ ሐረግ ለልጅ ልጆቿ ማሳወቅ ነበር። በመሆኑም የሚከተለውን የጣይቱን ልጆች የትውልድ ሐረግ መረጃ ያገኘሁት ጣይቱ ካሳደገቻቸው ከየሻሽ-ወርቅ በላይ ዘለቀና ከመንግሥቴ አያሌው መሸሻ ነው። እኔም በራሴ በኩል ከአባቴና ከእናቴ ማረጋገጫ የሚሆነኝ መረጃ አግኝቻለሁ።

በጣይቱ አሰኔ በኩል ያለው የትውልድ ሐረግ (ከበዳሳ አንስቶ እስከ ጣይቱ ልጆች) እነደሚከተለው ነው።
(1) በዳሳ፡ (2) ዋጁ፡ (3) ሜታ፡ (4) ገረሱ፡ (5) አቡ፡ (6) ጃርሶ፡ (7) ቢቂሊ፡ (8) ባቦ፡ (9) ድምቶ፡ (10) ወዳጅ (ወዳይ)፡ (11) አሰኔ (እንሰኔ)፡ (12) ጣይቱ፡ (13) በላይ፡ እጅጉና አያሌው፡፡

በዘለቀ ላቀው በኩል ያለው የትውልድ ሐረግ (ከዋዩ አንስቶ እስከ በላይና እጅጉ) እነደሚከተለው ነው።
(1) ዋዩ፡ (2) ጫንጮ፡ (3) ቂልጡ፡ (4) ገልገል፡ (5) ሃጌ፡ (6) ላቀው፡ (7) ዘለቀ፡ (8) በላይና እጅጉ፡
መሸሻ አደም በኩል ያለው የትውልድ ሐረግ (ከበዳሳ አንስቶ እስከ አያሌው) እነደሚከተለው ነው።
(1) በዳሳ፡ (2) ዋጁ፡ (3) ሜታ፡ (4) ገረሱ፡ (5) አቡ፡ (6) ጃርሶ፡ (7) ቢቂሊ፡ (8) ባቦ፡ (9) ዲዶ፡ (10) ጎበና፡ (11) ቦሩ፡ (12) ይመር፡ (13) አደም፡ (14) መሸሻ፡ (15) አያሌ፡፡
የሺፈራው ገርባውም የትውልድ ሐረግ (በእናቱ በአያህሉሽ ዘለቀ በኩል) እንደሚከተለው ነው።
(1) ዋዩ፡ (2) ጫንጮ፡ (3) ቂልጡ፡ (4) ገልገል፡ (5) ሃጌ፡ (6) ላቀው፡ (7) አያህሉሽ ዘለቀ (የዘለቀ ላቀው እህት፡) (8) ሺፈራው፡ (የሽፈራው የትውልድ ቦታ ወሎ ክፍለ-ሀገር፡ ቦረና አውራጃ፡ ወግዲ ወረዳ፡ መነ-ዲጋ ቀበሌ ነው።)
የራሴ የትውልድ ሐረግና የተወለድኩበት አካበባቢ
አስቲ ከአያቴ ከየሺ ሰምቤ (የአባቴ እናት) ስለራሴ የትውልድ ሀረግ የሰማሁትን ልንገራችሁ። አያቴ ከመቶ ዓመት በላይ ኖራለች። በርካታ ዘመዶቻችን እየመጡ የትውልድ ሐረጋቸውን እንድትነግራቸው ይጠይቋት ነበር። ዋነኛ መነሻቸው የቅርብ ዘመዳሞች እንዳይጋቡ ለመከላከል ነው። አያቴም ጥርት አድርጋ ትቆጥርላቸው ነበር። በዚህም ረክተው ይመለሱ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ዘመዶቼ ከገጠር አዲስ አበባ ሲመጡም ለልጆቼ የሚነግሩት የትውልድ ሐረጋችንን ነበር። እንግዲህ ወደራሴው ልመልሳች፡፡
እኔ ራሴ (አድማሱ ገበየሁ) ከጣይቱ አሰኔ ጋር በ10ኛው ወዳጅ በሚባለው እገናኛለሁ፤ ከአንደኛው ማለትም ከበዳሳ ጀምሮ 14ኛ ትውልድ ላይ ነኝ፡፡እንዲሁም ከአያሌው መሸሻ ጋር በ13ኛው አደም በሚባለው እገናኛለሁ፤ ከአንደኛው ማለትም ከበዳሳ ጀምሮ 17ኛ ትውልድ ላይ ነኝ፡፡ በሌሎችም በተቀሩት በሁለቱ አያቶቼ በኩል ትውልድ ሐረጌ (1) በዳሳ፡ (2) ዋጁ፡ (3) ሜታ፡ ከሚባሉት ጋር ይገናኛል።
ይህ የትውልድ ሀረግ የሚያሳየው እኔ (አድማሱ ገበየሁ) በማንኛውም አቅጣጫ (በአራቱም አያቶቹ በኩል) ኦሮሞ መሆኔን ነው።
ዘመዶቼ የሚኖሩበትና እኔም በልጅነቴ ያደግሁበትና የተማርሁበት አካባቢ የሚገኘው በደቡብ ምዕራብ ወሎ ነው።

(1) የተወለድኩት ቦረና ወረዳ ውስጥ ዲቢ የሚባል አካባቢ ነው። መንደራችን መነ ገጃ (ፊንጫ) እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፡ በርካታ ዘመዶቻችን የሚኖሩባቸው ጎረቤቶቻችን ደግሞ መነ-ከተሜ፡ መነ-ደርሶ፡ መነ-ቱፋ፡ መነ-ደግሉ ይባላሉ።እስከ 8ኛ ክፍል የተማርኩት መካነሰላም ከተማ የሚገኘው ቦረና ትምህርት ቤት ነው።
(2) ቦረና ወረዳ ውስጥ በርካታ የገጠር አካባቢዎች አውቃለሁ፤ ተዘዋውሬም ጎብኝቻለሁ። እነሱም፡- ሜታ (ጅሩ መነቡኮ፡ ወቦ፡ መነዶዩ፡ ወርቄ አቦ፡ ተዋ፡ ወርቄ አቡ፡ በታ፡ መነደጋ፡ አይቻል ቦነያ፡ መስካቤ፡) ወግሎ፡ (ዶክስ፡ መስካቤ፡ ቢሊ፡ ሴፋጢራ፡ አቡ አደሬ፡ ዲቢ ጪሪ፡ ዶንቆሮጫካ፡) ደምቢ፡ (ሰምቦ፡ ሶዬ፡ ደራሜ፡ ወርቄ መስቀሌ፡) አያና፡ ይባላሉ።

(3) በወግዲ ወረዳ (ሌንጮ፡ ለሚ፡ ጫቀታ፡ ጎረንጅ፡) አልፎ አልፎም ቢሆን ዘመዶች አሉኝ። በመሐል ሳይንት (ከደንቆሮ ጫካ እስከ ድንሳ፡) እና በለገሂዳ ወረዳ (አስከ ወለቃ ወንዝ፡) ጥቂት ዘመዶች አሉኝ።
በምሥራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ በእነብሴ ሳር ምድር፡እናርጅ እናውጋ፡ እና ሸበል በረንታ ወረዳዎች (በአባይ ወንዝ ዳርቻዎች አከካባቢ) አልፎ አልፎም ቢሆን ዘመዶች አሉኝ።

ከላይ በጠቀስኳቸው አካባቢዎች የሚኖሩት ዘመዶቼ ሁሉ የትውልድ ሀረጋቸው የሚቋጠረው ሜታ በሚባለው ግንድ ነው። እስከ አያቶቼ ትውልድ ድረስ ያሉት መስማትና መናገር የሚችሉት ኦሮምኛ ቋንቋን ነበር። የአባቴ ትውልድ ትንሽ ትንሽ ኦሮምኛ መስማትና መናገር ይችል ነበር። ከእኔ ትውልድ ጀምሮ ኦሮምኛ መስማትና መናገር የሚችል ማግኜት በጣም አስቸጋሪ ነው። የእኔ ትውልድ (ሁላችንም ማለት ይቻላል) መስማትና መናገር የምንችለው አማርኛ ብቻ ነው።

ለአሁኑ ይህን ያህል ካልሁ፣ ወደፊት ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለኝን አስተያየትና አቋም ይዤ እቀርባለሁ።

ጆቤ እንኳን ደህና አልመጣችሁ!!

ኤርሚያስ ለገሰ
ጥቅምት/2016

ermias-legese

ማስታወሻ : ይህ ጽሁፍ ከራሴ ውጭ የምሰራበትን የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥንና ሬዲዮ (ኢሳት)ን ጨምሮ የማንንም አቋም አያንፀባርቅም::

መግቢያ
“የለውጥ ሃይሎች ግልፅና ደፋር ውይይት ለመፍትሔና የጋራ ድል” በሚል አቢይ ርዕስ ተከታታይ መጣጥፍ እየቀረበ ነው። ከዚህ ቀደም “በክፍል አንድ” በተሰራጨው ጽሁፍ ሁለት ቁምነገሮችን ለመዳሰስ ተሞክሯል። የመጀመሪያው፦ ግልጽና ደፋር ውይይት የምናደርግባቸው መሰረታዊ ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለመዘርዘር ተሞክሯል። ዛሬ አገራችን ያለችበት ሁኔታ የሚያሳስበው ዜጋ ባለመኖሩና አገር አደጋ ላይ በወደቀችበት ሁኔታ በመተማመን ላይ የተመሰረተና የጋራ ድል (win- win) በሚያረጋግጥ መልኩ ምክክር መካሄድ እንዳለበት የተገለጠበት ነው። መጣጥፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የስርአት ለውጥ መምጣት አለበት በማለት የሚንቀሳቀሱት ሁሉም የለውጥ ሃይሎች የዛሬና የነገን ኢትዮጵያ እጣ ፋንታ በሚወስኑ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ምን እንደሚያስቡ ለህዝቡ ማቅረብ እንዳለባቸው የሚጠይቅ ነው። ሁለተኛው፦ በተከታታይ ለሚቀርቡት ጽሁፎች መነሻ ከተደረጉ አምስት ታሳቢዎች ውስጥ ሦስተኛው ታሳቢ (“የአዲስ አበባ ነዋሪ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል። ህዝባዊ ማዕበሉን ለማቀጣጠል ዝግጁነቱ ከፍተኛ ነው”) የሚለው ሃሳብ የተስተናገደበት ነው። ለማስታወስ ያህል “በክፍል አንድ” በቀረበው ጽሁፍ የቀረቡት አምስት ታሳቢዎች የሚከተለውን ይላሉ
ታሳቢ አንድ፦ የህዉሃት አገዛዝ ይወድቃል። የሚወድቀው ግን በከባድ መስዋዕትነት ነው። ከተከፈለው ያልተከፈለው መስዋዕትነት ይበልጣል።

ታሳቢ ሁለት፦ የኢትዮጵያ አንድነት እንደተጠበቀ ይቆያል። የለውጥ ሃይሉ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ አይደራደርም።
ታሳቢ ሦስት፦ የአዲስ አበባ ነዋሪ የስርአት ለውጥ ይፈልጋል። ህዝባዊ ማዕበሉን ለማቀጣጠል ዝግጅነቱ ከፍተኛ ነው።
ታሳቢ አራት፦የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም።
ታሳቢ አምስት፦ ከአጭር ጊዜ አኳያ የተገኘው ድል በብስለትና በፅናት ካልተያዘ ሊዳፈን ይችላል።

በመሆኑም በዚህ ጽሁፍ ላይ ለዋናው ሰነድ መነሻ ከሆኑት ውስጥ በ”ታሳቢ አራትነት” (“የለውጥ ሃይሎች ከአጭር ጊዜ አኳያ የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም።) የሚለው ይቀርባል። በመጣጥፍ ሆድ እቃ ውስጥ የትግራይ ኤሊቶች በተለይም የቀድሞ የህዉሃት የጦር መኮንኖች መደ መድረኩ አሁን ለምን እንደመጡ፤ ይዘው የመጡት እጀንዳ ምን እንደሆነ፤ ወደፊት መምጣታቸው የሚያስገኘው ጥቅምና ጉዳት ለውይይት መነሻ በሚሆን መልኩ የቀረበበት ነው። ከዚህም በተጨማሪ ህዉሃትን ከመገርሰስ አኳያ ዋነኛ የትግል ማዕከሎችና ፓሎች የትኛዎቹ እንደሆነ ለማሳየት ይሞክራል።

(“ክፍል አንድ” አግኝታችሁ ማንበብ ያልቻላችሁ ሰዎች በሳተናው(Satenaw)፣ ኢትዮ-ሚዲያ ፎረም(EMF)፣ ዘ-ሃበሻ( Zehabesha) ፣ ecadf forum: ህብር-ሬዲዮ ድረ-ገጾች ላይ ማግኘት ይቻላል።)
***
(ታሳቢ አራት) :
የለውጥ ሃይሉ ከህወሃት የቀድሞ የጦር ጄነራሎችም ሆነ አመራሮች ብዙ መጠበቅ የለበትም።
ላለፉት ሩብ ክፍለ ዘመናት ህዉሃት በብሔር ብሔረሰቦች ዲሞክራሲያዊ መብቶች እየማለና እየተገዛተ ዝህቡን ለማታለል ብሎም ለመለያየት ቢሞክርም ያሰበውን አላማ ሊያሳካ አልቻለም። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው በአገራችን የሰላም እጦት ከጫፍ እስከ ጫፍ እየታየ ነው። የስርአት ለውጥና የነፃነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተለያዩ የትግል ስልቶች ተቀርፀው ወደ ትግባር ተቀይረዋል። እየተደረጉ ያሉት ትግሎች አስተሳስረን ስንመረምር አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ወደ መቃብር የወረደበት ሆኖ እናገኘዋለን። ከዚህ በኋላ ህዉሃት መንግስታዊ የበላይነትን ባገኘበት ሁኔታ የምርጫ ፖለቲካ አጀንዳው ተዘግቷል። የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች እንዳሉት በምርጫ ፖለቲካ መቃብር ላይ ጥቁር አበባ ተቀምጦበታል። መቃብር ፈንቅሎ ትንሳኤ ይፈፀም ይሆን ለወደፊት የምናየው ይሆናል። ተስፋ አለኝ።

ህወሃት መራሹ ድርጅት በየጊዜው የሚሰጠው ድርጅታዊ መግለጫና እሱን ተከትሎ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተስፋ የሚያስቆርጠው የአገሬው ህዝብና የአለም መንግስታትን ብቻ አይደለም። የስርአቱ መስራችና ባለቤት የነበሩ እንዲሁም በተለያየ ከፍተኛ የፖለቲካና ወታደራዊ ስልጣን ላይ የነበሩትን ጭምር ነው። በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ሚዲያዎችን ያጨናነቁት ጄኔራል አበበ እና ጄኔራል ፃድቃን በስርአቱ ምላሽ ላይ ምን ያህል ተስፋ እንደ ቆረጡ መገመት ይቻላል። “የስርአት ችግር ስላለ፣ ኢህአዴግ የተቀባይነት ችግር ስላጋጠመው የስርአት ለውጥ መምጣት አለብት!” ብሎ የተናገረው አንደበታቸውና የከተበው ብዕራቸው ዞር ብለው ሲመለከቱ ማፈራቸው የሚቀር አይደለም። እነ ፃድቃን “ሀገሪቷ የመበታተን አደጋ ሊያጋጥማት ይችላል” ቢሉም የቀድሞ የትግል ጓዶቻቸውና የስልጣኑ ባለቤቶች “ህገ-መንግስታዊና ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ስርአት በጽኑ መሰረት ላይ ተገንብቷል” የሚል ዲስኩር ያሰማሉ።

እነ ጆቤ “ህዝቡ በተስፋ እጦት ውስጥ ገብቷል” ብለው ሲፅፉ በተቃራኒው እነ አባይ ፀሀዬ “የአገራችን ህዝቦች በኢትዮጵያ የፈነጠቀውን የልማትና የዲሞክራሲ ጮራ ተማምነው በለመለመ ተስፋ ወደፊት ይመለከታሉ” የሚል ዘመን ተሻጋሪ ማብራሪያ ይሰጣሉ። እነ ፃድቃን በቀኝ ሆነው የመቶ ፐርሰንት ምርጫ በህዝብ ማላገጥ ነው” በማለት ብዕራቸውን ሲያነሱ በግራ የተሰለፉት እነ በረከት “ኢህአዴግ ስራ በምርጫ ካርድ የተሰጠውን ሃላፊነት አደራ ለመወጣት ቆርጦ ተነስቷል” ይሉናሉ። አራንባና ቆቦ!! እዚህ ላይ በሁለቱ የቀድሞ የጦር አዛዦችና የህዉሃት መራሹ መንግስት ሃይሎች መካከል በሁሉም ጉዳይ ተቃርኖ ውስጥ እንደገቡ የሚያስብ ካለ በደንብ ተሸውዷል። ሁለቱም ሃይሎች የህዉሃትን ብሎም የትግራይ ህዝብ ጥቅም ይነካል ብለው በገመቱት ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አላቸው። ከዚህ አንፃር በቅድሚያ ሊነሳ የሚችለው በቀድሞ በትግራይ አስተዳደር ስር ያልነበሩና ዛሬ የተካለሉት ወልቃይትን የመሳሰሉ ቦታዎች ናቸው። የጦር አዛዦቹም ሆነ የህዉሃት ታጋይ ባለስልጣናት መጀመሪያ ሰሞን የወልቃይትና ተመሳሳይ ቦታዎች ፈጽሞ አንዳይነሱ፤ የሚዲያ ትኩረት እንዳያገኙ አድርገው ነበር። በጽሑፎቻቸውም ሆነ በመግለጫዎቻቸው በየትኛውም ቦታ ከመግለጥ ተቆጥበው ነበር። የቅማንትን ጉዳይ አጉልቶ የገለጠው “ጆቤ” ወልቃይት ላይ ሲደርስ የብዕሩ ቀለም በሚያስፎግር ሁኔታ አልቆበት ነበር። በኦሮሚያ ጥያቄዎች ላይ በምናቡ ከፈጠራቸው የኦሮሞ ልጆች ጋር ማውራቱን ሊነግረን የፈለገው ጄነራል አበበ ጠገዴና ጠለምት ፀለምት(ጨለማ) ሆነውበት ግድግዳ ተስታኮና ተንፏቆ ሲያልፋቸው ተመልክተናል።

ሁኔታዎች እየገፋ ሲመጡና የትግሉ ማዕከሉ “ወልቃይት” መሆኑ ሲረጋገጥ እየተንፏቀቁም ቢሆን የወልቃይትን አጀንዳ ማንሳት ጀመሩ። ለምን ከዚህ በፊት ልታነሡት አልሞከራችሁም ሲባሉ “ይሔ ትልቅ ጉዳይ አይደለም። መደረግም አልነበረበትም” የሚል ምላሽ ሰጡ። ቁምነገሩ እዚህ ጋር ነው። ለእነ ጄነራል ፃድቃን የቅማንት ጉዳይ ትልቅ እንደሆነ አድርገው ሊያገኑት ሲሞክሩ የማያቋርጥ የህዝብ ደም እየፈሰሰበት ያለውን ወልቃይት ንቀው እንደተውት ሊያሳዩ ሞከሩ። እነዚህ ሰዎች ይህን ምላሽ ሲሠጡ ወልቃይት “የትግል ማዕከል” እና “የኢፍትሃዊነት ማሳያ” መሆኑን ጠፍቷቸው አይደለም። ልክ አቶ መለስ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት ካድሬዎች “ለምን ባድመን ለመሰለ ቁራሽ መሬት የ10ሺዎች ደም ይፈሳል?” ብለን ሥንጠይቀው እጁን እየጠበጠበ “ባድመ የትግላችን ማዕከል የሆነችው የኢፍትሐዊነት ማሳያ ስለሆነች ነው” በማለት የንዴት ምላሽ ሰጥቷል። በመሆኑም ባድመ የኤርትራ መንግስት በሃይል ስለወሰዳት መጀመሪያ ወደቀድሞው ቦታዋ ትመለስና ህጋዊ ውሳኔ ይሰጥባት እንደተባለ ሁሉ የወልቃይትም ተመሳሳይ ነው። ወልቃይት “ኢፍትሃዊነት ማሳያ” ስለሆነች መጀመሪያ ወደቀድሞው ታሪካዊ ባለቤቷ ትመለስና ሌሎች የህዝብ ጥያቄዎች ቂም በቀል በማይፈጥሩና የጋራ ድል (Win_Win) በሚያረጋግጡ መልኩ ይፈቱ ማለት የአባት ነው። ይገባልም።

ይህ ካልሆነ ግን ምንአልባት ከባድመው ባልተናነሰ በ100ሺዎች የሚጠጋ ህይወት የሚወድቅበትና ደም መቃባቱ የሚያባራ ሊሆን ይችላል። በመቶ ሺዎች ሊገደሉ ይችላሉ የሚለውም ተራ ማስፈራራት አይደለም። ህዉሃት በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ የቋጠረው የቂም ቋጠሮ ከዚህ በላይ ሊገድል እንደሚችል ፍንጭ የሚሰጥ ነው። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አሰፋ አቢዩ ከሳምንታት በፊት በሰጠው መግለጫ “99 ፐርሰንት ንፁህ ናቸው። እርምጃ የምንወስደው በተቀሩት ላይ ነው” በማለት ይፋ አድርጓል። አሁን ባለው የአማራ ክልል ንቅናቄ ከ5 ሚሊዮን የአማራ ተወላጆች በቀጥተኛ እየተሳተፉ እንደሆነ ዝቅተኛ ግምት ቢወሰድ እንኳን በኮሚሽነር አሰፋ ስሌት መሠረት ከ50 ሺህ በላይ ሠዎች እርምጃ ይወሰድባቸዋል። ህዝባዊ ማዕበሉ እየሰፋ ሲሄድ በአስቸኳይ የስርአት ለውጥ ካልመጣ እርምጃ የሚወሰድበት የአማራ ተወላጅ ሁለትና ሶስት እጥፍ ይሆናል። ለህዉሃት “የትግል ማዕከል” ( Centrifugal Forces) የሆኑትን ቦታዎች አሳልፎ መስጠት መቃብሩን በጥልቀት የመቆፈር ያህል ስለሚመለከተው በጅምላ ከመግደል የሚመለስ አይሆንም።

በእኔ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ማዕበል ከህዉሃት ህልውና አንጻር በርካታ ዋልታዎች (Multi- Polar) ያሉት ቢሆንም፣ የዋልታዎቹ ምሰሶ ወልቃይት ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የኦሮሚያ፣ ጋምቤላ፣ ኮንሶ የተነሱት እምቢተኝነቶች ትላልቅ ዋልታዎች ቢሆኑም ህዉሃት ልቦና ገዝቶ በህይወት መቆየት ከፈለገ ወደ ምሶሶነት ሳያድጉ በተራዘመ ሂደት ሊያዳፍናቸው ይችላል። ለምሳሌ ህዉሃት ኤርትራ ላይ የሚያስበው (Eritrea-Factor፡ ኤርትራ በጦርነት ማሸነፍና አስመራ ላይ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት) ከተሳካና ህዉሃት ኢትዮጵያን መምራት ከተነሳው የኦሮሚያን ጥያቄ እስከ ጫፍ ሊወስደው ይችላል። ይህም በኦሮሞ ጉዳይ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና አክቲቪስቶችን የመከፋፈል እድሉ ሰፊ መሆኑ አይቀርም። ህዉሃት እስከ ጫፍ የሚወስደውን ፍላጎት ለመቀበል አዳዲስ ሃይሎች (Emerging Power-mongers) የሚፈልቁበት ሁኔታ ይፈጠራል። በመሆኑም ህዉሃት በሚቀደው ሀገር የማፍረስ ቦይ የሚፈሱ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሰዎች ይኖራሉ።
***
እንደ እውነቱ ከሆነ ሁለቱ የህዉሃት የቀድሞ ጦር አዛዦች በተለይም ሌ/ጄነራል ፃድቃን ወልቃይትና ሌሎች “የኢፍትሐዊነት ማሳያ” ቦታዎችና “የትግል ማዕከሎች” በተመለከተ ያስቀመጡት ምላሽ ህዝባዊ እምቢተኝነቱን የበለጠ ነዳጅ የሚጨምር ነው። ጄነራል ፃድቃን መጀመሪያ አካባቢ ባቀረባቸው ጽሁፎች በብልጣብልጥነት ሊያልፈው ቢፈልግም ቦታዎች ይበልጥ “የትግሉ ማዕከሎች” መሆናቸውን በህዝባዊ ማዕበሉ ሲመለከት ከድርቅና በተሻገረ አይን አውጣነት ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እርስ በራስ የተምታታ ምላሽ ሰጠ። ይህ የጦር መኮንኑ ምላሽ የአማራ ህዝብ ትግልና መነቃቃት ከደረሰበት ደረጃ ጋር ፍፁም የማይመጥን ነው። የአሁኑ የአማራ ትግል የደረሰበት ደረጃ ፍልሚያው ተጧጡፎ አድማሱን በመስፋት ቅኝቱ ሙሉ ለሙሉ ተቀይሯል። ከአስር አመት በፊት ሃሰን ዑመር አብደላ በመጣጥፋቸው እንደገለጡት ቅኝትና ምቱ ከተቀየረ እስክታውም መቀየር አለበት። በመሃመድ አህመድ የትዝታ ቅኝትና ምት ጥላሁን ገሠሠን “አንቺን ነው! ሰማሽ ወይ” የሚለው አይደነስም። በ “እምበር ተጋዳላይ” አጨፋፈር ስልት የይሁኔ “ሰከን በል” አይጨፈርም። እንደዚህ ከሆነ በአራዳ ቋንቋ ሽወዳ ይሆናል። አሁን ትግሉ በደረሰበት ደረጃ ደግሞ ውሽልሽል ምክንያት ሸውዶ ማለፍ የሚችልበት ወቅት ላይ አይደለንም። አለበለዚያም እውነት መድፈር ካልተቻለና የሚያስፈራ ከሆነ (ኮንስቲትወንሲያቸውን እንደሚያጡ ይገባኛል) ምላሽ አለመስጠት ይቻል ነበር። ፃድቃን ሊጠቀምበት የፈለገው “የሽወዳ ፖለቲካ” ህዝባዊ እምቢተኝነቱን አቀጣጥሎ መስዋዕትነቱን ከመጨመሩ ባሻገር በሌሎች ያቀረባቸው የመፍትሄ ሃሳቦችም ላይ በጥርጣሬ እንዲታይ ያደረገ ነው።

ለማንኛውም ሌ/ጀነራል ፃድቃን ገ/ትንሳይ “የትግሉ ማዕከል” በሆነው ወልቃይት ዙሪያ ለአዲስ አድማሱ ጋዜጣ የሰጠውን መግለጫ በመመልከት ፍርዱን እንስጥ። አዲስ አድማስ ጋዜጣ “በሰሜን ጎንደር አካባቢ ያለው ተቃውሞ በተለይ ከ “ወልቃይት አማራነት” ጋር የተያያዘ ነው። የወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጉዳይ በምን አግባብ ነው መፈታት ያለበት?” ለሚለው ጥያቄ የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል።

“እኔ የወልቃይት ጉዳይ ለአንዳንድ ፖለቲካዊ አላማዎች ሽፋን ነው ብዬ ነው የማምነው። እንዴት ነው የሚፈታው ላልከው እኔ የሚታየኝ ህገ- መንግስቱን መሠረት አድርጎ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ይሔ ትልቅ ጉዳይ መደረግ አልነበረበትም። ህዉሃትና ብአኤን ተመካክረው መፍታት የሚችሉበት ደረጃ ላይ መድረስ ነበረባቸው።…. በህጋዊ መንገድ ስንሄድም ህገ-መንግስቱን መሰረት አድርጎ መፍታት ያስፈልጋል ነገር ግን ክልሎች በሚወሰኑበት ወቅት ከፍተኛ የፖለቲካ ውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ነበርኩ። በወቅቱ ቋንቋና የህዝብ አሰፋፈርን መሰረት አድርገን እንወሰን በሚል ነው የወሰነው። በዚህ መሰረት ደግሞ የተወሰነው ተወስኗል።”
አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቀጥሎ የጠየቀው “በወቅቱ ወልቃይት እንዴት ነው ወደ ትግራይ የተላከው?” በማለት ነበር። ሌ/ጄነራሉ እንዲህ በማለት አስገራሚ፣ አሳዛኝና እርስ በራሱ የሚደባደብ ምላሽ ሰጠ።

“አሁን እየጠየከኝ ያለኸው መረጃ ነው። ይሄን መረጃ አሁን አላስታውሰውም። እንደዚህ ሆኖ ነበር ብዬ ለማለት አልችልም። የተጠቀምንበት አቅጣጫ ግን የፌደራሊዝሙን መነሻ ነው። የህዝቦች ቋንቋና ባህልን መነሻ አድርገን ነው የከለከልነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ እዚያ አካባቢ ያለው አብዛኛው ህዝብ ትግርኛ ተናጋሪ ነው። ባህሉ የትግራይ ነው። በትግራይ ውስጥ ሊካተት የሚችል ህዝብ ነው። የሆነውም በዚህ አግባብ ነው።”
በመሆኑም እነዚህ የህዉሃት ጦር ጄነራሎች “ህዉሃት አደጋ ላይ መውደቁን ሲያዩ ሊታደጉት መጡ” የሚለውን አባባል ለጊዜው እንተወውና የጎደላቸውን ነገር በጨዋ ቋንቋ እንንገራቸው። በእኔ በኩል የጦር ጀነራሎቹ ወደፊት መምጣት ቢያንስ በአራት መሰረታዊ ጉዳዮች እደግፈዋለው።

አንደኛው ያልተገለጠ ማንኛውም አስተሳሰብ ስለማይታወቅ መገለጥ አለበት የሚል የፀና እምነት አለኝ። የሉቃስ ወንጌል (መዕራፍ 6 ቁጥር 45) በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራል።….. ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ውን ያወጣል። መልካም ሰውም ከመልካም መዝገብ መልካም ያወጣል” አንዲል አንደበታቸውና ብዕራቸው የተፋው ቁምነገር ከየትኛው ልብ እንደመነጨ ማወቅ የሚጠቅም እንጂ ጉዳት የሚያደርስ አይደለም።

ሁለተኛው ምክንያት: እነዚህ የህዉሃት የጦር ጄኔራሎች የቀድሞ ድርጅታቸው ምን ያህል ኋላቀር፣ ለለውጥ ዝግጁ ያልሆነ ግትረኛ፣ ፈሪ ድንጉጥ እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይችላሉ የሚል እምነት አለኝ። እንደጠበኩት በጥቂት ቀናት ውስጥ በህዉሃት ስፖንሰርነት የሚንቀሳቀሱት የውጭ ድረ-ገጾቻቸው ዘመቻቸውን በተጠናከረ መንገድ ከፈቱ። የአየር ሃይል አዛዥ የነበረውን አበበ ተ/ሃይማኖት በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወቅት የአውሮፕላን ግዥ ላይ ፈፀመ ያሉትን ሌብነት እየጠቀሱ ወረዱበት። “የፈፀምከውን ሌብነት ዝም ስንልህ የረሳነው መሰለህ እንዴ?” በሚል ማስፈራራቱን ቀጠሉ። ጄኔራል ፃድቃንን ደግሞ “የስልጣን ፍላጎት የቀፈቀፈው ሃሳብ” በማለት አብጠለጠሉት። ይባስ ብለው በኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስም ባወጡት ድርጅታዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ህዝብ በሁሉም የህይወት መለኩ (መንፈሳዊንንም ይጨምራል) ከፍተኛ ለውጥ እንዳመጣ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ጠንካራ መሠረት ላይ እንደተጣለ፣ በዲሞክራሲያዊ ምርጫ (100%) አሽንፈው የመንግስት ስልጣን እንደተቆጣጠሩ፣ ባለሁለት አሀዝ ተከታታይ እድገት አምጥተናል….ወዘተ የሚሉ አስደንጋጭ ቃላትን በመጠቀም የጦር መኮንኖችን ቆሌ ገፈፋ።

ሦስተኛው ምክንያት :የህዉሃት የጦር ጄነራሎች የሚያቀነቅኑት ሃሳብ ምን ያህል የአገራችንን ችግሮች በጥልቀት ይዳሳሳል፤ ምን ያህል ተቀባይነት ይኖረዋል፤ ከመንግስትና የለውጥ ሃይሎች ፍላጎት አንፃር የተቃኘ ነወይ፤ የደበቋቸውና ለህዝብ ይፋ ቢደረግ ራሳቸውንም ሆነ የቀድሞ ድርጅታቸውን ተጠያቂ የሚያደርግ ነገር ይገልጡ ይሆን ወይ?….. ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች ምላሽ ያገኛሉ በሚል ነው። በግሌ የጠበኳትን አግኝቻለሁ። መኮንኖች የስርአቱ ችግር አለ መፍትሄው ስርአታዊ (systemic) መሆን አለበት ብለዋል። እርግጥ መፍትሄው አሁን ባለው የህዉሃት/ኢህአዴግ ህገ-መንግስት ማዕቀፍ ስር መሆን እንዳለበት ያስገነዝባሉ። አሁን ባለው ህገ- መንግስት እንዴት አድርጎ ስርአታዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚቻል እንቆቅልሽ ቢሆንም እንደ ሃሳብ መነሳቱ የሚያበረታታ ነው። በተለይ ህዉሃት አሁን ከዚያው አቋም ሲነፃፀር ምን ያህል የሰማይና ምድር ልዩነት እንዳለ መገንዘብ ይቻላል። ሰሞኑን አቶ በረከት የኤፈርት ኩባንያ ንብረት የሆነው ሬዲዮ ፋና በጠራው ኮንፈረንስ ላይ አይኑን በጨው አጥቦ “18 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን መክረው የተጻፈ ህገ-መንግስት፣ በአለም ላይ ካሉ ጥቂት ምርጥ ህገ- መንግስቶች አንዱ የሆነ” በማለት ዲስኩር ሲያሰማ እንደነበር ለሁሉም ግልጽ ነው። ህገ-መንግስታዊ ፍርድቤት የሌለው፤ ፍርዱን የሚሰጡት እነ አባዱላ፣ ሙክታር አህመድ፣ አባይ ወልዱ፣ ገዱ አንዳርጋቸው…… ወዘተ የሆኑበት ህገ-መንግስት ምርጥነትን ለመናገር በበረከት የአስተሳሰብ ደረጃ ዝቅ ማለት ይጠይቃል።

አራተኛው ምክንያት፡ የህዉሃት የጦር መኮንኖች በአንዳንድ የለውጥ ሃይሎችና በአለም አቀፍ ተቋማትና ሀገሮች ያለው ግንዛቤ በጣም አደገኛ መሆኑ ላይ ነው፡፤ እነዚህ ግለሰቦችና ተቋማት የጦር መኮንኖች የውስጥ አዋቂ አድርገው ስለሚቆጥሩ እንደ ዋነኛ የመፍትሄ አካል አድርገው የሚወስዱበት ሁኔታ በተደጋጋሚ ይታያል። ይህ አረዳድ በጣም አደገኛ ከመሆኑም ባሻገር የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ወደኋላ የሚመልስበት እድል ሰፊ ነው። የም ዕራብ ሐገሮች በተለይም ሰሜን አሜሪካ (ለምሳሌ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት) በተለያዩ ጊዜያቶች ህዉሃት አደጋ ውስጥ ሲወድቅ እነዚህን የጦር መኮንኖች እንደ አማራጭ የሚያማትሩበት ሁኔታ መኖሩ የሚታወቅ ነው። በምርጫ 97 ማግስት (አቶ በረከት ስምኦን ያጫወተኝ ስለሆነ በከፊል እመኑኝ) የቅንጅት አመራሮች ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መ/ቤት ጋር በሚወያዩ ሰዓት ጄኔራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ እንዲያካትቱ ጠይቀዋቸው እንደነበረ በንዴት ውስጥ ሆኖ አውግቶኛል። ይሄ የበረከት አገላለጥ እውነት ይሁን ውሸት ታሪክ የሚገልጠው ቢሆንም ዊክሊክስን ያገላበጠና የአሜሪካ ኤምባሲ ከቀድሞ የህዉሃት አመራሮች ጋር ያደረጉትን ሚስጥራዊ ውይይት ለተመለከተ አሜሪካኖቹ የሚይዙት የተሳሳተ አመለካከት እንደሚኖር መገመት ይቻላል።

አንዳንድ የለውጥ ሃይሎች ነን የሚሉና አለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት የጦር መኮንኖቹን እንደዋና መፍትሄ የሚወስዱ ከሆነ በጣም አደገኛ ሁኔታ የሚፈጥርበት የተለያዩ ምክንያቶች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ የመጀመሪያው የህዉሃት የጦር መኮንኖች ህዉሃት የኢህአዴግ የፖለቲካ አስኳል መሆኑን ሌሎች የኢትዮጵያ ማህበረሰቦችና የውጭ ሃይሎች እንዲያውቁ አይፈልጉም። ጄኔራሎቹ በጠመንጃ፣ በደህንነት፣ በኢኮኖሚና ፖለቲካ የበላይነት የአገሩ ባለቤት የሆነውን የትግራይ ነፃ አውጪ (ህዉሃት) ወደ ጎን ትተው የህይወት እስትንፋስ የሌለውን ኢህአዴግ እንደ መፍትሄ አመንጪና ተጠያቂ አድርገው ያቀርባሉ። ለስሙ ቦታውን የያዙትንና አንዳችም ስልጣን የሌላቸውን ከህዉሃት ውጪ ያሉ ባለስልጣናትን ከፍ ከፍ በማድረግ የተለየ ምስል ለመፍጠር ጥረት ያደርጋሉ። በተለይም የአየር ሃይል አዛዥ የነበረው ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት በሙት መንፈስ የሚመራውን ሃይለማርያም ደሳለኝ ብዕሩን ባነሳ ቁጥር ሲያንቆለጳጵስና ሲያሞካሽ ማየት የተለመደ ሆኗል። “ይድረስ ለክቡር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝየጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ” የሚል ርዕስ በመጠቀም “ለሰራዊቱ ግንባታ የተዘጋጀው መጽሀፍ አግዱልኝ!” በማለት ተማፅኖ ሲያቀርብ ይስተዋላል። ጀቤ ይሄን የሚያደርገው የሃይለማሪያምን “የህዉሃት ትሮይ ፈረስነት” አጥቶት አይደለም። ኢህአዴግ የሚባለው አደረጃጀት ለህዉሃት ጭምብልነት የተፈጠረ መሆኑን ዛሬም የሚመራበት መርሆ በጫካ የተቀረፀና ከዘመኑ ጋር የማይሄድ፤ ሸረሪት የሚሯሯጥበትና ያደረበት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ።
***
ከጄኔራል ፃድቃን አስተያየት ሳልወጣ አድናቆቴን መግለጽ የምፈልግበት አንድ አረፍተ ነገር አለ። ጄኔራሉ በሌሎች የህዉሃት ታጋዮች ባልተለመደ መልኩ አሁን ያለውን ሁኔታ ሲገመግሙ “የትግራይ ህዝብ በተለይም በከተሞች አካባቢ በሌሎች ማህበረሰቦች የመገለል ሁኔታ አጋጥሞታል። መተማመኛውንም የስልጣን የበላይነት አስጠብቆ ማቆየትና በመከላከያና ሌሎች የፀጥታ ሃይሎች ተከልሎ መኖር” እንደሆነ ገልጧል። ይሄንን ግምገማ ሙሉ በሙሉ የምቀበለው ነው። ለረጅም ጊዜያቶች ይሄ ችግር እየመጣ እንደሆነ ደጋግመን ስንለፈልፍ በህዉሃት ጎራ ያሉ ሰዎች “ዘረኞች” የሚል ታፔላ ተለጥፎልን ነበር። ዛሬ የጦር መኮንኑ በግላጭ ሲያወጣው በህዉሃት መንደር የተፈጠረ ብዙም መንጫጫት አይታይም። ታዲያ! ጄኔራል ፃድቃን በዚህ ጉዳይ ላይ ይሄን ያህል ርቀት መጓዝ ከቻለ ከጥያቄው ጋር አብረው ለሚነሱት ሌሎች ጥያቄዎች ምላሽ ቢሰጥበት እኛንም ከስድብና ውርጅብኝ ያድነናል። ጥያቄው የትግራይ ህዝብ በተለይ በከተሞች ውስጥ በሌላው ማህበረሰብ እየተገለለ መሄዱ እውነት ሆኖ ሲያበቃ፤ የመገለሉ መንስ ኤና መሰረታዊ ምክንያት ምንድነው? መገለሉስ ከመቼ ጀምሮ የተፈጠረ ነው? ተጠያቂው ማነው?…. ወዘተ የሚሉ ናቸው። ይህንን ቁልፍ ጉዳይ መመለስ ከተቻለ ወደ ቁልፍ መፍትሄው የምንሄድበት መንገድ አልጋ በአልግስ ይሆናል።

ከዚህኛው ክፍል ከመውጣቴ በፊት ሁለቱን የህዉሃት የጦር ጄኔራሎችም ሆነ እነሱን ተከትለው ሃሳባቸውን በሰፊው ተቀብለው ያራመዱ የአገር ውስጥ ሚዲያዎች የቀጣይ እጣፈንታ ምን ሊሆን ይችላል የሚለውን የራስ ግምት አስቀምጬ መሄድ እፈልጋለሁ። ከልምድ ማየት እንደሚቻለው ህዉሃት በአንድ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ አቋም ወስዶ መግለጫ እስኪያወጣ ድረስ የቀድሞ አባላቱንም ሆነ በግል ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚንቀሳቀሱ (ሸገር 102) ድርጅቶች ትንሽ ለቀቅ ያለ ሃሳብ የሚያራምዱበት በር ገርበብ ይደረግላቸዋል። የዛን ሰሞን አፋችንን ይዘን በመገረም “በሸገር ካፌ” ላይ ወይዘሮ መዓዛ ብሩና ጓድ አብዱ የጄኔራል ፃድቃንን “የስርአት ለውጥ” አስተሳሰብ ተገቢ እንደሆነ በአድናቆት ሲነግሩን ነበር። እርግጥ የደርግ ዘመን ጥያቄና መልስ ላይ “አብዮታዊ” ማብራሪያ ሲሰጥ የምናውቀው ጓድ አብዱ በእያንዳንዱ ንግግሩ ሟቹ መለስ ዜናዊን ሲያንቆለጳጵስ መደመጥ ብዙዎችን አስገርሟል። በጣት ቆጠራ አልፈው ካልሆነ በስተቀር ጓድ አብዱ ከሰባት ጊዜ በላይ ባደርገው የሟች ጥሪ በስላሴ 24 ሰዓት ቁጭ ብለው መቃብር የሚጠብቁ የህዉሃት ዋርድያዎችን ሳያስበረግግ አይቀርም።

***
ወደ ገደለው ጉዳያችን ስንመለስ የህዉሃት የቀድሞ ጄኔራሎችም ሆነ እንደ ሸገር ያሉት የሚዲያ ተቋማት ህዉሃት/ኢህአዴግ መግለጫ ካወጣ በኋላ ቀስ በቀስ ወደ ኋላ መንሸራተታቸው የግድ ይሆናል። ያለ አንዳች ጥርጥር ጄኔራሎቹ ወደ አፎታቸው ይገባሉ። ሸገርና ተመሳሳይ ሚዲያዎች ደግሞ ወደ ሰገባቸው። ይህን ማድረግ ካልቻሉ “የአበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም” የሚለው ብሂል ወደተግባር ተገልብጦ ለመመልከት ሩቅ አይሆንም። ለነገሩ ጆቤና ጓድ አብዶ በአክሮባት የሚታሙ ስላልሆነ ካናዳው ለማምለጥ እንደ አቦሸማኔ መሮጣቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። የትግራይ ኤሊቶች፣ የህዉሃት የቀድሞ የጦር ጄኔራሎችም ሆነ የቀድሞ ታጋይ ባላስልጣናት ከህዉሃት በፍጥነት ተፋተው ለአዲስ የስርአት ለውጥ ዝግጁ የማይሆኑባቸው ሌሎች ተጨማሪ መሰረታዊ ምክንያቶች አሏቸው። ከዚህ ውስጥ የቅድሚያ መስመር የምትይዘው ኤርትራ ናት (Eriteria-Factor)። ህዉሃት ከኢርትራ ጋር የገባበት ጦርነት ፍፃሜ የረጅም ጊዜ የመጠባበቂያ ህልሙን ያጨለመ ነው። ለሁሉም ግልጽ እንደሆነው ከጦርነቱ በፊት ከኤርትራ መንግስት ጋር ለአመታት የተካሄደው ድርድርም ሆነ የጦርነት ውሳኔ የተወሰነው በህውሃት ማዕከላዊ ኮሚቴ ነው። ወደ ጦርነት ከተገባም በኋላ የመሪነቱን ሚና የጨበጡት ህዉሃቶች ናቸው። በጦርነቱ ምክንያት የአገሪቱ ካዝና በተራገፈና ሙጥጥ ባለ ሰዓት መንግስት ከሶስት ቢሊዮን ብር ያላነሰ የተበደረው ከህዉሃት የኢኮኖሚ ኢምፓወ ከሆነው ኤፈርት (ትእምት) ነበር። ለጦርነቱ የሚሆነውን የጦር መሳሪያ (ታንክ፣ ሮኬት፣ ሚሳየል፣ የውጊያ አውሮፕላኖች……) በየአህጉራቱ የተሽከረከሩ የሚገዙት የህዉሃት አመራሮችና የጦር አዛዦች ናቸው።

(በነገራችን ላይ በአውሮፕላን ግዢ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ከነበራቸው የጦር አዛዦች ግንባር ቀደሙን የሚይዘው የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበረው ሜ/ጄኔራል አበበ ተ/ሃይማኖት ነው። አበበ የክፍፍሉ መጀመሪያ ወቅት እንቡር እንቡር ቢልም የአንጃዎቹ መጨረሻ ኩምሽሽ አድርጎታል። “አይተነው ጊዜ ወደሚያደላው” አይነት ባህሪ ያለው አበበ ገልብጦ የመለስን ቡድን ይቅርታ ቢጠይቅም የመለስን የቃሪያ ጥፊ ከማግኘት አልታቀበም። ከአዛዥነቱ በንፋስ ፍጥነት ተባረረ። ከዛ በኋላ ጆቦ በሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ከኪሱ በማውጣት አሜሪካን ሀገር ተማረ። በትምህርቱም “የአሰብ ኢትዮጵያዊነት” ተገለጠለት። መገለጡ ቀልብ ይስባልና በኢትዮጵያ አየር ሃይል ላይ በተነው። ጆቤ! ዛሬ በወር 150ሺህ ብር የሚከራይ ቪላ አለው። ያውም በአዱገነት እምብርት! ለ100 አመት ይዞ ቢቆይና ከደሞዙ ሰባራ ሳንቲም ባያወጣ አሁን ያለውን ሀብት ሩብ አይኖረውም። እርግጥ ከርቀት እንደሰማነው ባለቤቱ ብቸኛዋ ሴት ጄኔራል ሆናለች።)

እዚህ ላይ የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ውጤት ለህዉሃት የበላይነት መምጣትና የትግራይ ተጠቃሚነት ዋስትና የፈጠረው አደጋ ለህዉሃት መሰንጠቅ መሰረታዊ ምክንያት ቢሆንም ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች አሉት። እነዚህ አደጋዎች ከህዉሃት አፈጣጠር፣ የዘረጋው ስርአት ባህሪና ውስጠ- ድርጅት ሁኔታ ጋር የተያያዘ ነው። ህውሃት የበላይነቱን ያረጋገጠባት ኢትዮጵያ ካልቀጠለችና የአገር መበተን ካጋጠመ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ነፃ ሀገር ፈጥሮ መኖር እንደ መጨረሻ ግብ ያስቀመጠ ቢሆንም ከኤርትራ ጋር የገባበት ቁርሾና ደም መፋሰስ ይህን ፍላጎቱን ከሞላ ጎደል ዝግ አድርጎታል። Eriteria-Factor የተባለው አንዱ ገፅታ ይሄ ነው።… የጎንደር፣ አፋር፣ ወሎ ህዝብ ከታች ኤርትራ ከላይ ሆነው ትግራይን ሳንድዊች የሚያደርጉበት ሁኔታ ስለሚፈጠር ከዚህ በኋላ “የትግራይ ሪፐብሊክ” ከህልም የዘለለ አይሆንም። ትግራይን ገንጥለን በሰላም እንኖራለን የሚባል ህልም ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣……ወዘተ ወደ ትግራይ የተከለሉ ሰአትና የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በተነሳ ሰአት ወደ መቃብር ወርዷል። የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ በአንድ በኩል ነፃ ሀገር ለመመስረት ህልም የነበረችውን የህዉሃት አመራሮች ወሽመጥ የቆረጠ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ኢትዮጵያዊነቱን አጥብቆ ለሚፈልገው የትግራይ ህዝብ ትልቅ ብስራት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው። በአጭሩ ኢትዮጵያን ወዳድ ለሆነው የትግራይ ህዝብ የጦርነቱ አጨራረስ በመጥፎ ሁኔታ ውስጥ የሚፈጠር ጥሩ አጋጣሚ ነው። Blessing in disguise!!

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት አጨራረስ ህዉሃትን ለሁለት ሰንጥቋል የሚባልበት መሰረታዊ ምክንያት ይሄ ነው። የስዬ አብርሃ ቡድን የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብትና ደም መከታ አድርጎ ኤርትራ በመደምሰስ አሻንጉሊት መንግስት ለመመስረት ሲያስብ ሌሎች አላማዎችን ለማሳካትም ጭምር ነበር። ህዳጣኑ ህዉሃት ከትግራይ ውጭ ያለው የኢትዮጵያ ህዝብ መግዛት ካቃተውና ህዝባዊ ማዕበሉ ካናወጠው ያለ ኤርትራ ስጋት “ነፃ የትግራይ ሪፐብሊክ” መመስረት ይችላል። የስዬ ቡድን ኤርትራ ላይ ለራሱ ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት መመስረት አለመቻሉ በክፉ ጊዜ መጠጊያ የምትሆነውን “ሪፐብሊክ ትግራይ” የመመስረት ራዕይ ተጨናገፈበት። በተለይ በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ህዝብ ልጆቹን በመገብሩ ቁጭት ላይ የወደቀ መሆኑና ከዚህ በኋላ ጋሻነቱ ባከተመበት ሁኔታ ከኤርትራ ጋር ጦርነት መግጠም ማለት የህዉሃት ፍፃሜ መሆኑ አይቀርም። በሌላ በኩል ጓድ መለስ በስልጣን ለመቆየት ካለው ጥማት በመነሳት ጦርነቱ ሊገፋበት አለመቻሉ እዛው ሳለ የትግራይን ነፃ መንግስት ህልም ባጭሩ የቀጨ ሆኗል። ይህ በመሆኑ ምክንያት በህዉሃት/ኤህአዴግ ህገ-መንግስት ውስጥ የሰፈረው አንቀጽ 39 ከህዉሃትና ትግራይ ህዝብ አኳያ ከወረቀት አንበሳነት የዘለለ አይሆንም። የህዉሃት አፈጣጠር መነሻ የሆነው “የትግራይ ነፃ ሪፐብሊክ” መመስረት እውን ሊሆን የሚችለው ሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች ሲሟሉ ብቻ ነው።

አንደኛው :ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት (Centrifugal Forces) ….. የመሳሰሉ መሬቶችን ለባለቤታቸው ሲመልሱ;
ሁለተኛው: ኤርትራ ላይ (Eriteria-Factor) ዳግም ጦርነት በመክፈትና ኤርትራን ወደ ዳግም ሱማሊያ መውሰድ፤ ከተቻለም ለህዉሃት ተጠሪ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በመመስረት በተራዘመ ጊዜ በኮንፌደሬሽን መዋሃድ።

የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምትና ሌሎች ቀድሞ በትግራይ ክልል ያልነበሩ ቦታዎች ወደ ቀድሞ ቦታቸው ይመለሳል የሚለው ጥያቄ “በህዉሃት መቃብር” ላይ ብቻ የሚፈፀም ነው። ለዚህም ነው ከየትኛውም የኢትዮጵያ ቦታዎች በበለጠ ሁኔታ እነዚህ አካባቢዎች “የትግሉ ማዕከል” ናቸው የተባለበት ምክንያት። ኤርትራን በጦር ገጥሞ ለህዉሃት ተገዢ የሆነ አሻንጉሊት መንግስት በአስመራ እናቋቁማለን የሚለውም ፍላጎት ያለቀና የደቀቀ ተደርጎ ባይወሰድም ወደ ዜሮ የቀረበ እድል (Probability) ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ነው።

እርግጥ ሌሎች ህዉሃትን ለሁለት የሰነጠቁ እንጭፍጫፊ ምክንያቶች እዚህ ላይ ሊጨመሩ የሚችሉበት ሁኔታ መኖሩ እሙን ነው። የህዉሃት የፍጥረቱ የመጨረሻ ግብ ከመኮላሸቱ ጎን ለጎን የዘረጋው ስርአት ባህሪና የውስጠ- ድርጅቱ ሁኔታ ለመሰነጣጠቁ ምክንያት ነው። ህውሃት የዘረጋው ስርአት የፓርቲውን የበላይነትና የትግራይን የተለየ ተጠቃሚነት ዝርፊያ (ሙስና) አንዱ መለያ ባህሪው ነው። መንግስት እንደመሆኑ መጠን ወረራና ዝርፊያው “መንግስታዊ” መሆኑ አይቀርም። “መንግስታዊ ሌብነት”…. “መንግስታዊ ዝርፊያ”…. “መንግስታዊ ሙስና”…. “መንግስታዊ ውንብድና!”…. በመሆኑም የህዉሃት አንዱ መሰረታዊ መለያ ባህሪ በአዋጅ፣ በህግ፣ በመመሪያ የሚፈፅም የቡድን ዝርፊያ (“መንግስታዊ ሙስና”) ነው። ህዉሃት ገና ከጠዋቱ ቁልፍ ቁልፍ የሆኑ የመንግስትና ድርጅታዊ የስልጣን ቦታዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው በዚህ ምክንያት ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ውጭ ጉዳይ፣ መከላከያ፣ ደህንነት፣ ፖሊስ፣ ሚዲያ፣ የድርጅት ቢሮ፣ የክልሎች ሞግዚት በመሆን አይናቸውን በጨው ያጠቡት ለዚህ ነው። ይህም ሆኖ የህዉሃት ስርአት በትግራይ ህዝብና ልሂቃን ዘንድ ያለው አረዳድ ከሌላው አካባቢ ጋር ተመሳሳይ አይደለም።

አሁን ባለው ነባራዊ እውነታ ከትግራይ ህዝብ የወጡት ህዉሓቶች በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በሆኑበት፤ …ገዳዩ አሳሪው ገራፊውና መርማሪው እነሱ በሆኑበት፤ የመንግስት ስልጣንን በመጠቀም ከፍተኛ የኢኮኖሚ አቅም በገነቡበት፤ …በትግራይ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅና ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እልፍ አእላፍ ፋብሪካና የኢኮኖሚ አውታሮች በተገነቡበት፤… በጠብታ ኢኮኖሚ መልኩ በትግራይ ክልል የተገነቡት፤ መሰረተ ልማቶችና ማህበራዊ ፍትህ ማምጫ ተቋማት….. ወዘተ በፍጥነት ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ሊቀላቀላቸው አይችልም። ራሳችንን ማዋሸት ካልፈለግን በስተቀር የትግራይ ህዝብ በህዉሃት አገዛዝና አፈና ተማሮ ሊሆን ይችላል እንጂ “አዲስ ስርአት” ለመቀበል ዝግጁነቱ አይታይም። የህዉሃት አገዛዝ በፓርቲ መዋቅሩ አማካኝነት የሚፈጥረው ጭቆና፣ የዘመድ አዝማድ አድሎአዊ አሰራር፣ ኋላቀርነት፣ “አህያ ቢራገጥ…” የሚመስል አይነት ቂም በቀል፣… አሰልቺ ስብሰባዎች እና መዋጮ….. ወዘተ የትግራይን ህዝብ ሊያስመረምረው ይችል ይሆናል እንጂ ለስር-ነቀል ለውጥ የተዘጋጀ አይደለም። ግፋ ቢል ከአጭር ጊዜ አኳያ “ላም እሳት ወለደች” ከሚለው ብሂል የሚርቅ አይደለም። ይህ የብዙሃኑ የትግራይ ተወላጅ ፍላጎት አድርገን ልንወስደው የምንችል ነው።