Tag Archives: EPRDF Democracy

ጋዜጠኞቹ እና የዞን 9 ብሎገሮቹ ለጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀነ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው

  • ኤዶምና ማህሌት የመብት ጥሰት እንደተፈጸመባቸው ቅሬታ አቅርበዋል

የዞን 9 ብሎገሮቹና ሶስቱ ጋዜጠኞች ያቀረቡት መቃወሚያ ‹‹ተቀባይነት የለውም›› ተብሎ ለጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ተቀጠረባቸው፡፡ ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ የተከፈተባቸው ክስ አግባብ አለመሆኑን የሚገልጽ ስምንት ገጽ የክስ መቃወሚያ አቅርበው የነበረ ቢሆንም አቃቢ ህግ ‹‹ክሱ ምንም ችግር የለበትም፣ የሚሻሻል ነገር የለውም፡፡›› በሚል መቃወሚያውን ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

zone9 & journalismቃሊቲ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት ኤዶም ካሳዬና ማህሌት ፋንታሁን ማረሚያ ቤቱ ውስጥ የመብት ጥሰት እንደሚፈጸምባቸው ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡ ሁለቱ ታሳሪዎች በፍርድ ሂደት ላይ ያሉ ቢሆንም እስር ቤቱ ውስጥ ‹‹አሸባሪ›› የሚል ስም እንደሚሰጣቸው ቅሬታ ያቀረቡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ ‹‹ቤተሰብ ብቻ ነው የሚጠይቀን፡፡ ከቤተሰብ ውስጥም የምንጠየቅው ስማቸውን ባስመዘገቡት ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ የምንጠየቀው ለ10 ደቂቃ ነው፡፡ ለመጠየቅ የሚመጡ ቤተሰቦቻችንም ድብደባ ይፈጸምባቸዋል፡፡›› በሚል ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

ባለፈው ችሎቱ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኃላፊ ታሳሪዎቹ ይደርስብናል በሚሉት በደል ዙሪያ ለዛሬ ቀርበው እንዲያስረዱ ተጠይቀው የነበር ቢሆንም ሳይቀርቡ ቀርተዋል፡፡ ዛሬ ያልተገኙት የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ለጥቅምት 25/2007 ዓ.ም ቀርበው ያስረዳሉ ተብሎ የነበር ቢሆንም ኤዶምና ማህሌት ‹‹ይህ የመብት ጉዳይ ስለሆነ አጭር ቀጠሮ ሊሰጥልን ይገባል፡፡›› በማለታቸው ማረሚያ ቤቱ ውስጥ እየተፈጸመብን ነው ያሉትን በደል ብቻ ለማየት ጥቅምት 11 ቀን 2007 ዓ.ም.ቀነ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡ የማረሚያ ቤት ኃላፊው ቀርበው ያስረዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ኤዶምና ማህሌት ለዋናው ክስም ጥቅምት 25 ደግመው ይቀርባሉ፡፡

በዛሬው ችሎት የታሰሪዎቹ ቤተሰቦች፣ የአገር ውስጥና የውጭ ጋዜጠኞች፣ የኤምባሲና የተቋማት ተወካዮችን ጨምሮ በርከት ያለ ታደሚ ተገኝቶ ተከታትሏል፡፡ ጥቅምት 25 ቀን 2007 ዓ.ም አቃቢ ህግ ያቀረበው ክስና ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ ምርመራ ተደርጎ ሌላ የፍርድ ሂደት ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡- ነገረ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ

የፖለቲካ አመራሮቹ ችሎት ያለ ተከላካይ ጠበቃ ሲታይ፤ቀጣይ ቀጠሯቸው ግልፅ አይደለም

ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ፒያሳ አራዳ በሚገኘው የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የፖለቲካ  ፓርቲ አመራሮች ጉዳይ በዝግ ችከሎት ያለ ተከላካይ ጠበቃ ቀጠሮ መስጠቱ ተጠቆመ፡፡ የፖለቲካ አመራሮቹ አቶ ሀብታሙ አያሌው የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ የአንድነት ፓርቲ ምክትል የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ አቶ አብርሃ ደስታ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ መምህርና የአረና ፓርቲ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እንዲሁም አቶ የሺዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ከተከላካይ ጠበቆቻቸው ጋር ሳይገናኙ ከቀጠሮ ሰዓታቸው አርፍደው ከቀኑ 10 እና 11 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

detained politiciansበነበረው የፍርድ ቤት ችሎት ተከላካይ ጠበቃ ደንበኞቻቸውን ህጉ በሚፈቅደው መሰረት በማዕከላዊ ሄደው መጎብኘትና መነጋገር ቢፈልጉም፤ በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ማዕከል “ማዕከላዊ” ፖሊስ ስላልተፈቀደላቸው ፍርድ ቤት መገኘቱ ለፕሮፖጋንዳ ካልሆነ ከህግ አግባብ ትርጉም ስለሌለው እንደማይገኙ አስቀድመው ማሳወቃቸው ተጠቁሟል፡፡ በችሎትም ቤተሰብ፣ ጋዜጠኛ፣ ዲፕሎማቶች እና ወዳጅ ዘመድ እንዳይከታተል መከልከሉም ታውቋል፡፡ የእስረኞቹ ቀጣይ ቀጠሮ መቼ እንደሆነ እስካሁን ከፍርድ ቤቱ ማግኘት ባይቻልም፤ እንደ ነገረ ኢትዮጵያ ዘገባ ከሆነ የማዕከላዊ ምርመራ ኃላፊ አቶ ተክላይ ሹመት ተጠርጣሪዎቹ የተቀጠሩት ለጥቅምት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ሲሉ፤ ሌላ ፖሊስ ደግሞ ለጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ነው የሚል ጥቆማ መስጠታቸውን የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ እስረኞቹ እስካሁን በነበረው ምርመራ ፖሊስ ምንም ዓይነት ለወንጀል ክስ የሚያበቃ መረጃ ባለማግኘቱ፤ ወደ ኃይል እርምጃ በመሄድ ፖሊስ የሚፈልገውን ቃል እስረኞቹ ያልፈፀሙትን አስገድዶ የእምነት ቃል እንዳስፈረማቸው የማዕከላዊ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይሄም ለህዝቡና ለመገናኛ ብዙኃን እንዳይገለፅና ፍርድ ቤትም በቅሬታ መልክ እንዳይቀርብ ስለተፈለገ ነው ተከላካይ ጠበቆቹ እንዳይጎበኙ የተከለከሉት ሲሉ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡  በዚህም የዛሬው ችሎት ያለጠበቃ ጭምር በዝግ ችሎት መካሄዱ የተጠቆመ ሲሆን፤ የቀጠሯቸው ቀንም ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ እስካሁን ትክክለኛውን ከፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ እንዳልተቻለ መረጃዎእ አመልክተዋል፡፡ ችሎቱን ለመታደም ወደ ስፍራው ያቀኑ ሰዎችም ፍርድ ቤቱ ግቢ ሲገቡ ከወትሮ በተለየ በፖሊሶች ከፍተኛ ፍተሻ፣ እንግልትና ወከባ እንደተፈፀመባቸው  የዓይን እማኞች ገልፀዋል፡፡

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ፍርድ በአየር ለሌላ ጊዜ ተቀጠረ

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች የመጨረሻ ፍረድ ብይን ዛሬ ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም. ይሰጣል ተብሎ ቢጠበቅም ያለምንም ችሎት በአየር ላይ ለሌላ ጊዜ መቀጠሩ ታወቀ፡፡ ቀደም ሲል ጉዳዩ ልደታ ከሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ በሚገኘው ደራርቱ ቱሉ ትምህርት ቤት አካባቢ በሚገኘው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዝግ ችሎት እየታየ የነበረ ሲሆን፤ በብዙዎች ግምት የመጨረሻ የብይን ፍርዱ ልደታ በሚገኘው ፍርድ ቤት ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ በሁለቱም ፍርድ ቤት ችሎት አለመሰየሙ ታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና ዓለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ጉዳዩን እንዳይከታተሉ በዝግ ችሎት ሲያደርግ የቆየው አቃቂ ቃሊቲ የሚገኘው ፍርድ ቤት ዛሬ በመዝገብ ቤት በኩል ለአንዱ ተከላካይ ጠበቃ የመጨረሻ ይሆናል የተባለውን የፍርድ ብይን ለታህሳስ 3 ቀን 2006 ዓ.ም. ያለ ምንም ችሎት በአየር ላይ ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ ተከላካይ ጠበቆችም ከፍርድ ቤት አሰራር ውጭ ያለምንም ችሎት ቀነቀጠሮ መሰጠቱ እንዳስገረማቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ “313 ሚሊዮን ብር ለልማት” በሚል ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ

ብስራት ወ/ሚካኤል

ህዝበ ሙስሊሙ አርብ ሚያዝያ 18 ቀን 2005 ዓ.ም በአንዋር መስጂድ “313 ሚሊዮን ብር ለልማት” የሚል
መፈክር እያስተጋባ ተቃውሞውን አሰማ፡፡ ለጁምዓ ስግደት የወጣው የሙስሊሙ ህብረተሰብ ከስግደት በኋላ “313
ሚሊዮን ብር ለልማት” የሚል መፈክር አሰምቶ በሰላም ወደ የቤቱ ተበትኗል፡፡

የዕለቱ መፈክር ምን ማለት ነው? ለምን አስፈለገ? ምን መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነው በማለት በሥፍራው
ለነበሩ አንድ የሙስሊየም ሃይማኖት ተከታይ ፍኖተ ነፃነት ጥያቄ አቅርቦ   “መንግስት አህባሽ የተባለ ባዕድ
አስተምሮ አስመጥቶ ለማስፋት 313 ሚሊዮን ብር በጀት ለመጅሊሱ መመደቡን የሚያሳይ ሰነድ አግኝተናል፡፡ ይህ
በጣም ያሳዝናል፡፡ መንግስት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም እያለ ይክዳል፡፡ በተግባር ግን በጀት መድቦ
ሙስሊሙን ህብረተሰብ ለማተራመስ ይሠራል፡፡ ወታደርና ደህንነት አሰልፎም የእምነት ነጻነታችንን አፍኗል፡፡
በነጻነት እንዳናመልክ የእምነት ሥፍራችንን ይዳፈራል፡፡ ስለዚህ ሃይማኖታችንን ለመበከል ሙስሊሙን ለመከፋፈል
የመደበውን በጀት ለልማት እንዲያውለው ለማሳሰብ ነው” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡  አያይዘውም “ለልማት እያለ
ህዝብን ከማስጨነቅ በእጁ ያለውን ገንዘብ በመጀመሪያ ለልማት እንዲያውለው ለመጠየቅ መጥተነል” ሲሉ የተቃውሞ
ሰልፉን አላማ አስረድተዋል፡፡

ከሀሙስ ዕለት ጀምሮ በተለያዩ መስጂዶች ሁለት ገጽ ያለው በራሪ ወረቀት የተበተነ ሲሆን፤ “68ኛ የተቃውሞ
ሳምንት ድምጽ፤ ቁጥር 42” የሚለው ይኸው በራሪ ወረቀት ስድስት አብይ ርዕሶችን በመያዝ ይዘረዝራል፡፡ እነሱም
ሰላማዊነታችን ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንድሞቻችን ድጋፍ አስገኝቶልናል፣ ሰላማዊነታችን ዓለም አቀፍ ዲፖሎማሲያዊ
ድጋፍ አስገኝቶልናል፣ ሰላማዊነታችን ትግላችን ዕድሜና ክብር እንዲጎናፀፍ አስችሎናል፣ ሠላማዊ ትግል ለእርማት
ሁል ጊዜ ክፍት ነው፣ ሠላማዊነታችን ከአስከፊ እርምጃዎች እንድንጠበቅ ሰበብ ሆኖናል የሚልና ሠላማዊ ትግል
ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ማሰለፍ ይችላል የሚሉት ነጥቦች ናቸው፡፡

ምንጭ ፡- ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ