Ethiopia’s Cruel Con Game
David Steinman
In what could be an important test of the Trump Administration’s attitude toward foreign aid, the new United Nations Secretary-General, António Guterres, and UN aid chief Stephen O’Brien have called on the international community to give the Ethiopian government another $948 million to assist a reported 5.6 million people facing starvation.
Speaking in the Ethiopian capital, Addis Ababa, during the recent 28th Summit of the African Union, Guterres described Ethiopia as a “pillar of stability” in the tumultuous Horn of Africa, praised its government for an effective response to last year’s climate change-induced drought that left nearly 20 million people needing food assistance, and asked the world to show “total solidarity” with the regime.
Ethiopia is aflame with rebellions against its unpopular dictatorship, which tried to cover up the extent of last year’s famine. But even if the secretary general’s encouraging narrative were true, it still begs the question: Why, despite ever-increasing amounts of foreign support, can’t this nation of 100 million clever, enterprising people feed itself? Other resource-poor countries facing difficult environmental challenges manage to do so.
Two numbers tell the story in a nutshell:
1. The amount of American financial aid received by Ethiopia’s government since it took power: $30 billion.
2. The amount stolen by Ethiopia’s leaders since it took power: $30 billion.
The latter figure is based on the UN’s own 2015 report on Illicit Financial Outflows by a panel chaired by former South African President Thabo Mbeki and another from Global Financial Integrity, an American think tank. These document $2-3 billion—an amount roughly equaling Ethiopia’s annual foreign aid and investment—being drained from the country every year, mostly through over- and under-invoicing of imports and exports.
Ethiopia’s far-left economy is centrally controlled by a small ruling clique that has grown fantastically wealthy. Only they could be responsible for this enormous crime. In other words, the same Ethiopian leadership that’s begging the world for yet another billion for its hungry people is stealing several times that amount every year.
Read more… https://www.forbes.com/sites/realspin/2017/03/03/ethiopias-cruel-con-game/#586e691729d0
Source: Forbes
ተጠየቅ ህወሓት፣ኢህአዴግ እና ብሔራዊ ባንክ፤ በትግራይ ወርቅ ጉዳይ ”በጠራራ ጸሀይ አገር ሲዘረፍ”
አቻምየለህ ታምሩ
በያዝነው የፈረንጆች ዓመት በወርሀ ጥር የወያኔ ካድሬዎችና የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ተቋማት የሆኑት እነ ኤ.ቢ.ሲ.፣ ዋልታ፣ ፋና፣ ኤ.ዜ.አ. ወዘተ ትግራይ በታሪኳ ስላሉት የወርቅ ምርት መጠን በስፋት ዘግበው ነበር። የአገዛዙ ልሳን ኢ.ቢ.ሲ. እ.አ.አ. ጥር 07 ቀን 2016 ዓ.ም. ባቀረበው ርዕሰ አንቀጽ፤ ዋልታ እ.አ.አ. ጥር 09 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስደመጠም የዜና እወጃ ፤ ኤ.ዚ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስነበበን ሪፖርት ትግራይ እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ [በባህላዊ መንገድ] እንዳመረተችና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንዳቀረበች ነግረውናል።
ይህንን «ልማታዊ ዜና» የሰሙ ብዙ ሰዎች «ትግራይ ከየት አምጥታ ነው ይህንን ያህል ወርቅ አምርታ ለብሔራዊ ባንክ የምታቀርበው?» በማለት ከቁጥሩ ጀርባ ያለውን የምጣኔ ሀብት ትርጉም ሳያጤኑ አጣጥለውት አልፈዋል። ሆኖም ግን ከቁጥሩ ጀርባ ወያኔ ትልቅ አገራዊ ዘረፋና ወንጀል ፈጽሟል። ወያኔ በቁጥሩ ቁማር ተጫውቶ የኢትዮጵያን የሁለት አመት ባጀት ያህል ብሔራዊ ሃብት በአንድ ግብይት ብቻ ወደ ትግራይ አሸሽቷል ወይንም አሻግሯል። ነገሩ እንዲህ ነው።
እ.ኤ.አ.ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት በ42 ወር ውስጥ 597.7 ቶን ወርቅ ከትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ቀረበ ማለት ነው። ይህ ማለት ትግራይ በአመት በአማካኝ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባ ነበር ማለት ነው። በኢትዮጵያ የንግድ ህግ መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ብቸኛው ወርቅ ገዢና አስቀሟጭ ተቋም ነው። ክልሎች በየክልሎ የተመረተውን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ሲያቀርቡ ብሔራዊ ባንክ ክልሎች ላቀረቡት የወርቅ መጠን ክፍያ ይፈጽማል። ለምሳሌ ትግራይ 597.7 ቶን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሲታቀርብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለትግራይ ክልል የ597.7 ቶን ወርቅ ክፍያ በገንዘብ ይፈጽማል። ያልቀረበ ወርቅ ሪፖርት ተደርጎ ብሔራዊ ባንክ ላልቀረበ ወርቅ እንደቀረበ ተደርጎ ክፍያ ቢፈጽም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሀብት transfter ይኖራል ማለት ነው።
ወያኔ የነገረን ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ያቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ማለት
597, 700 ኪሎ ግራም ወርቅ ማለት ነው።ይህ ማለት ደግሞ 19,216,473 ወቄት ወርቅ ማለት ነው። ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት አመታት ውስጥ አማካኝ የአንድ ወቄት ወርቅ ዋጋ 1,100 የአሜሪካን ዶላር ነው። ይህ ማለት ትግራይ አቀረበችው የተባለው 597.7 ቶን ወርቅ ዋጋ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ይሆናል ማለት ነው።
ይህ ማለት [በወያኔ ዜና መሰረት] ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ላቀረበችው 597.7 ቶን ወርቅ ብሔራዊ ባንክ 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍሏታል ማለት ነው። የኢትዮጵያ ያለፈው አመት ባጀት አስር ቢሊዮን ዶላር ነው። ይህ ማለት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አቀረበችው ለተባለው 597.7 ቶን ወርቅ የተከፈላት 21. 376 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ የሁለት አመት በጀት በላይ ነው ማለት ነው።
ዋናውና ቁልፉ ጥያቄ እውነት ትግራይ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ 597.7 ቶን ወርቅ ወይንም ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ አቅርባለች ወይ? የሚለው ነው።
ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የአለም አገሮችን የወርቅና የሌሎች ማዕድናትን አመታዊ ምርት ማስረጃ የሚሰበስበውንና የሚያደራጀውን የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የአለም ማዕድናት ምርት ሰንጠረዥን ማየት በቂ ነው። ይህ የአሜሪካ ተቋም በአለም ላይ ያሉ ማዕድን አምራች አገሮችን የማእድን አመታዊ ምርት አሃዝ ሰብስቦ ደረጃ ያወጣና የአለም አገሮችን በማዕድን ምርት ያወዳድራል። በዚህ መስሪያ ቤት ማስረጃ መሰረት ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በአለም ላይ በወርቅ ምርት አንደኛ ቻይና ስትሆን አመታዊ የወርቅ ምርት መጠኗ 403 ቶን ነው።
ሁለተኛዋ የአለም ወርቅ አምራች አገር ደግሞ አውስትራሊያ ስትሆን አመታዊ የምርት መጠኗ ደግሞ 250 ቶን ወርቅ ነው። ሶስተኛ አሜሪካ [235 ቶን ወርቅ በአመት] ፤አራተኛ ሩስያ ፌድሬሽን [217.8 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ አምስተኛ ፔሩ [161 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ስድስተኛ ደቡብ አፍሪካ [160 ቶን ወርቅ በአመት]፤ ሰባተኛ ካናዳ [103 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ስምንተኛ ሜክሲኮ [96.7 ቶን ወርቅ በአመት] ፤ ዘጠነኛ ኢዝቤኪስታን [ 93 ቶን ወርቅ በአመት] እና ጋና [86.5 ቶን ወርቅ በአመት] በአለም ላይ አስሩ ከፍተኛ ወርቅ አምራች አገሮች ናቸው። የዚህ ምንጭ የሚከተለውን ትር መክፈትና መመልከት ይቻላል… http://www.indexmundi.com/minerals/…።
ወያኔ ኢትዮጵያ ትግራይ ብቻ ከሐምሌ 2012 ዓ.ም. እስከ ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች ያለው እውነት ቢሆን ኖሮ ኢትዮጵያ በወርቅ ምርት በአለም ደረጃ ፔሩን ቀድማ ሩስያን ተከትላ አምስተኛ ደረጃ ላይ ትሆን ነበር። ልብ በሉ ከአንድ እስከ አስር የወጡ አገሮች ሁሉ ወርቅ የሚቆፍሩት በጣም ዘመናዊ በሆነ መሰርሰሪያ ማሽን ነው። ወያኔ ግን ትግራይ በየ አመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቅርባለች የሚለን በባህላዊ መንገድ አምርታ ነው።
ከፍ ብዬ በለጠፍሁት የUnited States Geological Survey (USGS) Minerals Resources Program አመታዊ የወርቅ ምርት እውነተኛ ደረጃ መሰረት የኢትዮጵያ አመታዊ የወርቅ አምራችነት ደረጃ 29ኛ ሲሆን አመታዊ የወርቅ ምርቷ ደግሞ 12 ቶን ብቻ ነው። ልብ በሉ ይሄ አመታዊ የኢትዮጵያ የወርቅ ምርት ዶዶላ፣ መተከል፣ ለገደንቢና ወለጋ ሜድሮክ በዘመናዊ ቴክኖሎች ታግዞ የሚያመርተውን ይጨምራል። ወያኔ ግን የትግራይን አመታዊ ምርት ብቻ 171 ቶን ይለናል።
ሜድሮክ በዶዶላ፣ በመተከል፣ በለገደንቢና በወለጋ የሚያመርታቸውን ዜሮ አድርገን ኢትዮጵያ ያመረተችውን 12ቱን ቶን ወርቅ ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበ የወርቅ መጠን አድርገን ብንወስድ፤ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ እንደቀረበለት ተደርጎ ለትግራይ በጠቅላላ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ውስጥ በያመቱ ላልቀረበ 158 ቶን ወርቅ ክፍያ ፈጽሟል። ይህ ማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከትግራይ ቀረበ ተብሎ ከፍያ ከፈጸመበት 597.7 ቶን ወርቅ ውስጥ የተረከበው ወርቅ 42 ቶብ ብቻ ነው። የተቀረው 555.7 ቶን ወርቅ ወርቁ ከትግራይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሳይቀርብ ብሄራዊ ባንክ ግን ለትግራይ ክፍያ የፈጸመበት የውሸት ቁጥር ነው። ይህ ማለት ብሔራዊ ባንክ ለትግራይ ከከፈለው 21.3 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ለትግራይ የተከፈለው ላልቀረበ የውሸት ወርቅ ነው። ይህ ማለት ወያኔ ያልቀረበ ወርቅን አስታኮ 20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያገር ሀብት ወደ ትግራይ wealth transfter አድርጓል። ይህ ማለት የሁለት አመት የኢትዮጵያ የሁለት አመት አመታዊ በጀት ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ ወርቅ ባላቀረበችው ወርቅ ተሳቦ ተከፍሏታል። ይህ ማለት የሁለት አመታት የኢትዮጵያ አመታዊ ሀብት ወደ ትግራይ እንዲሄድ ዘረፋ ተፈጽሟል። This is a huge wealth transfter. ወያኔ ከጥር ወዲህም ማራኪ ቁጥር እያቀረበ የአገር ሀብት ወደ ተስፋዋ ምድሩ እያሸጋገረ ይገኛል።
የሚገርመው ትግራይ በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች በተባለ በወሩ የቀረበው ሌላ ዜና የስርዓቱ ዜና ነው። ፋና በየካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም [እ.ኢ.አ.] ያቀረበው ዜና ርዕስ እንዲህ ይላል…«ለብሄራዊ ባንክ እየቀረበ ያለው ወርቅ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ ነው።» ዜናው በዚህ ብቻ አያበቃም። ከ2004 ዓ.ም. እስከ 2008 ዓ.ም.[እ.ኢ.አ.] በየአመቱ 171 ቶን ወርቅ ትግራይ ለብሔራዊ ባንክ አቀረበች እንዳልተባለ «ብሄራዊ ባንክ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ መልኩ ተመርቶ የሚቀርበለት ወርቅ በእጅጉ ቀንሷል። በ2005 ለባንኩ የቀረበለት 8.1 ቶን ወርቅ ነበር። በ2006 ዓ.ም ደግሞ 7.4 ቶን ሆነ፤ በ2007ም በጣም አሽቆልቁሎ 5.4 ቶንድረስ ወርዷል።» አሉን። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከትግራይ ብቻ ለብሔራዊ ባንክ በአመት 171 ቶን ወርቅ ቀረበ ተብሎ 20 ቢሊዮን ዶላር እንደቀላል ወደ ትግራይ transfter እንዲሆን ባደረጉ በአንድ ወር ውስጥ ነው።
አይ አንቺ አገር! ማፍያዎች የውሸት ቁጥር እየቀቀሉ ሌላውን ጾም ደፍተፍና አራቁተው የድሆችን ሀብት ወደ መንደራቸው ያግዛሉ። በአንድ ማጭበርበር ብቻ ሀያ ቢሊዮን ዶላር የአገር ሀብት ወደ መንደራቸው አሸሹ! በቁጥር ሊሸውዱን ሲሞክሩ በትንተና እንዲህ ባጋለጥናቸው ጉዳይ ሀያ ቢሊዮን ዶላር በድብቅ ባልተወለደ አንጀታቸው ከገፈፉ ለሌላው ኢትዮጵያ ምን ያህል ያተርፉለት ይሆን?
በቅርቡ የተሰደደው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ ህይወቱ አለፈ
የማራኪ መፅሔት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር የነበረው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በስደት በሚገኝበት ናይሮቢ ኬኒያ ጥቅምት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በድንገት ህይወቱ ማለፉን ከማኀበራዊ ገፆች የተገኙ መረጃች እና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት በጅምላ ያደረገውን የመፅሔቶች እና ጋዜጣ ክስ እና የበርካታ ጋዜጠኞችን እና ብሎገሮችን እስርን ፍርሃት ተከትሎ በቅርቡ ከተሰደዱ ጋዜጠኞች መካከል ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ አንዱ ነበር፡፡
ጋዜጠኛው በስደት ኬኒያ ከሚገኝበት አንድ ናይሮቢ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለ ታውቋል፡፡ ጋዜጠኛው ከኢትዮጵያ ከተሰደደ ገና ሁለት ወር እንኳ እንዳልሞላው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ጋዜጠኛው ህይወቱ እስካለፈበት ድረስ በኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ውስጥ ከ12 ዓመታት በላይ እንዳገለገለና የድርሰት ስራም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡
ጋዜጠኛ ሚሊዮን በተወለደ በ33 ዓመቱ በስደት ናይሮቢ ኬንያታ ናሽናል ሆስፒታል ቢያርፍም፤የቀብር ስነስርዓቱ እሁድ ጥቅምት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. በትውልድ አካባቢው ይርጋ ጨፌ ከተማ ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተፈፅሟል፡፡ ጋዜጠኛው የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበር፡፡
አዲስ ሚዲያም በጋዜጠኛው ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ፤ ለጋዜጠኛ ሚሊዮን ፈጣሪ ነፍሱን በገነት እንዲያኖር፤ ለቤተሰቦቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል፡፡
የነፃነት ትግል እና ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ
ብስራት ወልደሚካኤል
የሽብር ትርጉም እና ድርጊት እጅግ ሰፊና እንደየሀገሮቹ መንግስታት ተጨባጭ ሁኔታና ስርዓት እንዲሁም ፍላጎት ይለያያል፡፡ በርግጥ የሽብር ተግባር መቼም በማንም ይፈፀም የሚወገዝና ትክክል ያልሆነ እኩይ ተግባር ነው፡፡ ይሁን እንጂ አምባገነን ስርዓት ያለባቸው ሀገሮች ገዥዎች የስልጣን ዘመናቸውን ዜጎችን በማሸማቀቅ ለማስቀጠል ሲሉ የነፃነት ታጋዮችን አሸባሪ ብለው እንደሚጠሩ፤ በኋላም የነፃነት ታጋይ መሆናቸው የተመሰከረላቸው በርካቶች ናቸው፡፡ ለዚህም በደቡብ አፍሪካ ዘረኛውን የአፓርታይድ የግፍ አገዛዝ በመቃወም በይፋ ለህዝቡ ነፃነት ይታገሉ የነበሩት እንደ ኔልሰን ማንዴላ ያሉ መሪዎች እና ሌሎች የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረንስ አባላት በጊዜው በነበረው አገዛዝና እንደነ አሜሪካ ያሉ ዘረኝነት የነገሰባቸው ምዕራባውያን ሀገሮች ጭምር አሸባሪ ተብለው ተፈርጀው ነበር፡፡
መሪው ኔልሰን ማንዴላን ጨምሮ ሌሎች አጋሮቻቸው ከ27 ዓመታት እጅግ ቀዝቃዛ ከሆነው አሰቃቂ የሮበን ደሴት እስር በኋላ በደቡብ አፍሪካውያን እና በዓለም አቀፍ የነፃነት ደጋፊዎች ጫና ከእስር ተለቀዋል፡፡ የዓለም የነፃነት አባት ከመባል አልፈው እስካሁን ባለው የዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ የትግሉ መሪ የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ ሲሞቱ እስከዛሬም ድረስ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በርካታ የዓለም አቀፍ መሪዎች በስፍራው በመገኘት ሀዘናቸውን ገልፀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ለማንም የሰው ልጅ ያልተደረገ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የተከታተለው ከፍተኛ አድናቆትና ሀዘኑን መግለፁ የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ በአንፃሩ የተለያዩ አምባገነን መሪዎች ሲሞቱ አብሮ ያልሞተው የገዥው ስርዓት ህዝቡን በግድ ልቅሶ እንዲወጣ ከፍ ሲልም የሙት ዓመት ልደቱን በአዞ እንባ ሙሾ እንዲያዝን ቢያደርግም፤ አብዛኛው ህዝብ ግን ከላዩ ላይ አንድ ትልቅ በሽታና ሸክም ከጫንቃው ላይ እንደወረደለት ያሰቡም አልታጡም፡፡
ራሳቸውን የነፃነት ታጋይ የሚያደርጉ በተለይ በኢትዮጵያ “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” በ2001 ዓ.ም. በአሸባሪነት የተፈረጁት አምስት ታጣቂ ቡድኖች ሲሆኑ፤3ቱ ከኢትዮጵያ፣ 2 ቱ ደግሞ ከውጭ የሚገኙ ናቸው፡፡ እነኚህም ዋና መቀመጫቸውን መካከለኛው ምስራቅ አረብ ሀገራት ያደረገው አልቃይዳ እና የሶማሊያው ታጣቂ አል-ሻዕባብ ከውጭ አሸባሪ ተብለው ተፈርጀዋል፡፡ ከኢትዮጵያውያን ታጣቂ አማፂያን መካከል ደግሞ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር(ኦብነግ)፣ግንቦት 7 ለዴሞክራሲና ለነፃነት ንቅናቄ (ግንቦት 7) እና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ይገኙበታል፡፡ ይሁን እንጂ የኢህአዴግ መራሹ መንግስት ተግባርን በመቃወም የትጥቅ ትግል እያደረጉ ያሉት በርካታ አመፂያን ሲሆኑ፤ እነኚህም ከሐረሪ ክልል፣ ከድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በስተቀር በሁሉም ክልሎች ታጣቂዎች እንዳሉ ይነገራል፡፡
ከኢህአዴግ መራሹ መንግስት ጋር እየተዋጉ እንዳለና ሊዋጉ “ኸረ ጥረኝ ጫካው፣ ኸረ ጥራኝ ዱሩ” ብለው የሚታገሉትና እስካሁን በአሸባሪነት ያልተፈረጁት የአፋር አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር(አርዱፍ)፣የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር (አርበኞች ግንባር)፣የሲዳማ አርነት ግንባር (ሲአግ)፣የምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ድርጅት፣የጋምቤላ ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር፣የቤኒሻንጉል ነፃ አውጭ ድርጅት እንዳሉ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲገለፁ ይስተዋላል፡፡
አሁን በኢትዮጵያ መንግስት ስልጣን ላይ ያለውና በትጥቅ ትግል በሌሎች የውጭ ኃይሎች ድጋፍ ወደ ስልጣን የመጣው ህወሓት/ኢህአዴግም ያኔ ታጣቂ አማፂ እንጂ ሰላማዊ የዴሞክራሲ ታጋይ ድርጅት አልነበረም፡፡ ያኔ ቀዳሚ ዓላማውም ቢሆንም የትግራይን ህዝብ ከእናት ሀገሩ መገንጠል ለዚሁም ኤርትራ እንድትገነጥል ድጋፍ ማድረግ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ኤርትራ እንድትገነጠል ማድረጉ ቢሳካም፤ የትግራይን ህዝብ ለመገንጠል በተደጋጋሚ የተደረገው ሙከራ ግን በትግራይ ህዝብ በተለይም በአዛውንቶቹ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳቱ ዓላማው ከመሪዎቹና ጠንሳሾች ህሊና ባይጠፋም ቀስ በቀስ መክሰሙ ይነገራል፡፡ ዓላማውን ለማሳካትም በርካታ ኢ-ሰብዓዊ የሆኑ የሽብር ተግባራትን መፈፀሙም ዛሬም ድረስ በዓለም አቀፉ የሽብርተኝነት መረጃ ድርጊቱ ከነ ጊዜው ተቀምጧል፡፡
በተለይ አሁን በስልጣን ላይ ያለውና የኢህአዴግ አስኳል በመሆን ሀገሪቱን እየመራ እንዳለ የሚታወቀው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ያኔ ከደርግ መራሹና ከኢሕዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጋር በሰሜን የሀገሪቱ በረሃ መሽጎ ሲፋለም በዓለም አቀፉ የሽብርተኝነት መረጃ ቋት(Global Terrorism Database/GTD) በአሸባሪነት ተመዝግቦ ነበር፡፡ በወቀቱ በሟቹ አቶ መለስ ዜናዊና ግብር አበሮቻቸው ሚመራው ታጣቂ አማፂ ቡድን “ህወሓት” ከሚፋለመው ከቀድሞው የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት በተጨማሪ በርካታ ንፁሃን እንደገደለ፣ እንዳቆሰለ፣ንብረት እንዳወደመ ዛሬም ድረስ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ለዚህም ህወሓት በአሜሪካ መንግስት በአሸባሪነት ጥቂር መዝገብ ዝርዝር ውስጥ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬም ያ ስሙ ከመረጃ ቋቱ ውስጥ ከፈፀመው አሰቃቂ ድርጊት ጋር ለአስረጅነት ቀርቧል፡፡
ህወሓት የሽብር ተግባሮች ፈፅሟል ተብሎ ከተመዘገበበት መካከል እ.አ.አ. ነሐሴ 2 ቀን 1990 ዓ.ም. በራያ ቆቦ 17 የኃይማኖት ተፅዕኖ ፈጣሪ አባቶችን በመግደልና ተቋማትን ማውደሙ፣እ.አ.አ. ጥቅምት 19 ቀን 1984 ዓ.ም. በላሊበላ 200 ንፁሃን ዜጎችን እንደገደለና 200 ያህል አቁስሎ ንብረት እንዳወደመ፣እ.አ.አ.የካቲት 18 ቀን 1988 ዓ.ም. በትግራይ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ንፁሃን ላይ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ አደጋ እንዳደረሰ ተጠቅሷል፡፡ ሌላው እ.አ.አ. በሚያዝያ 20 ቀን 1983 ዓ.ም. በትግራይ ኮረም እና እ.አ.አ. ነሐሴ 3 ቀን 1983 ዓ.ም. በጃሪ የሞቱትና የቆሰሉት ቁጥራቸው በግልፅ ባይታወቅም ለትርፍ ያልተቋቋሙና ግብረሰናይ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ላይ ጥቃት ማድረሱ በግልፅ ተቀምጧል፡፡
ለናሙና የተጠቀሱና ከላይ ተፈፀሙ የተባሉት አሰቃቂ የሽብር ተግባራት በህወሓት/ኢህአዴግ ስለመፈፀማቸው በይፋ ሲቀመጥ፤ ገዥው ስርዓት ግን እስካሁን በአደባባይ ተቃውሞም ሆነ ይቅርታ ያቀረበበት መረጃ የለም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየው ድርጊቱን አምኖ መቀበሉና እስካሁንም ትክክል ነው ብሎ እንደሚያምን ያሳያል፡፡ ስለሆነም ገዥው ህወሓት/ኢህአዴግ ሌሎች አማፂዓንን አሸባሪ ብሎ መፈረጁና ሌሎች የመብት ጠያቂ ኢትዮጵያውያንን አብሮ የመፈረጅ የሞራል ጥያቄን ማስነሳቱ አይቀሬ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሰላማዊ የፖለቲካ መንገድም ሆነ በትጥቅ ኃይል ለነፃነት በሚል የሚታገሉ እንደ ወንጀለኛ የሚታዩ ከሆኑ በመጀመሪያ ደረጃ በወንጀል ተከሶ ሒሳቡን ማወራረድና ተገቢውን ቅጣት አግኝቶ አርዓያ መሆን ያለበት በትጥቅ ትግል ወደ ሀገሪቱ መንበረ ስልጣን የመጣው ኢህአዴግ ነበር፤ ግን አልሆነም፡፡ አለበለዚያ መብትን መጠየቅና የነፃነት ትግል ማድረግ ለሌሎቹ ወንጀልና ስህተት ሆኖ ለኢህአዴግ ትክክልና ቅዱስ ተደርጎ ከበሮ የሚደለቅበት አግባብ ሚዛን ሊደፋ አይችልም፡፡
አሁን በስልጣን ላይ ያለው ህወሓት/ኢህአዴግ በደርግ “ገንጣይና አስገንጣይ ወንበዴ” በሚል ቀለል ያለ ስያሜ ሲሰጠው፤ በምዕራባውያን በተለይም በዓለም አቀፉ የሽብርተኝነት መረጃ ቋት አሸባሪነት ዝርዝር ውስጥ ከመስፈር ያገደው አልነበረም፡፡ አንባቢው ከላይ የተጠቀሰውን ለማረጋገጥ www.globalterrorismdatabase.org/TPLF (Tigray Peoples Libration Front) በሚል ህወሓት/ኢህአዴግ አሸባሪ እንደነበርና አሁንም ስሙ እንዳልተሰረዘ የበለጠ መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ማለት ኢትዮጵያ እየተመራች ያለችው በአሸባሪ ቡድን ነውን የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡
ሌላው በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶችስ በአሰቃቂ ድርጊትና ገደል ኑሮዓቸውን ገፍተው እንዲፋለሙ ያስገደዳቸው ምክንያት በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ካልሆነ መቼም ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው አካል ከተሻለ ኑሮ የሰቀቀን የቀበሮ የዱር ገደል ኖሮን የሚመርጥ ያለ አይመስለኝም፡፡ በየትኛውም የዓለም ሀገሮች ታሪክ እንደሚያስረዳው በሀገሮች ላይ የተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች ከገዥ ስርዓት ጋር የሚፋለሙት ዋና ምክንያት ገዥዎች በፖለቲካ ኃይሎች ላይም ሆነ በህዝቡ ላይ የሚፈፀሙ ኢ-ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ያልሆኑ ተግባራት መሆናቸው ነው፡፡ ለዚህም ያኔ የአመፅ የትጥቅ ትግል ይደረግባቸው የነበሩት ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ፣ጋና፤ ከላቲን አሜሪካ ብራዚልና አርጀንቲና፤ከሰሜን አሜሪካ ኩባና ራሷ ተባበሩት አሜሪካ፤ከአውሮፓ አየርላንድ፤ከእስያ ህንድን ብንጠቅስ ዛሬ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እና የዜጎቻቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት በገዥዎችም ሆነ በህብረተሰቡ በተግባር የተረጋገጠባቸው ሀገሮች በመሆናቸው ስለ ትጥቅ ትግል አይወራም፤የለም፡፡
በኢትዮጵያ ያለው እውነታ ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ ገዥዎች በዜጎች ላይ እየተፈፀሙ ያሉት አሰቃቂ ድርጊቶች ዛሬም አለመቆማቸው ነው፡፡ ስለሆነም አሁን ኢህአዴግ አሸባሪ ብሎ የጠራቸው ድርጅቶች ህወሓት/ኢህአዴግ በጫካ እያለ ከፈፀመው ተግባር ጋር ልዩነቱን እና አንድነቱን ህዝብ እንዲያውቅ ነፃ መድረክ አላመቻቸም፡፡ በዚህም አሸባሪ ብሎ የሰየማቸው የኢትዮጵያውያን ታጣቂዎች፤ ሽብርን በእጅጉ በሚኮንኑና በሚዋጉ ሀገሮች ቢሯቸውን መክፈታቸው እውን ኢህአዴግ እንዳለው አሸባሪ ናቸው? ወይስ የነፃነት ታጋይ? የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሁን በስልጣን ላይ ያለው አካል ከዚህ ቀደም በጫካ እያለ ከሚፈፅመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ አሸባሪ ከተባሉ አማፂዓን ያልተለየ እና ያልተናነሰ ተግባር በአዲስ አበባ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል “ማዕከላዊ” እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እንደተፈፀሙ፣ እየተፈፀሙ እንዳሉ ይነገራል፡፡
ከላይ የተጠቀሰውን ድርጊት ስንመለከት ህወሓት/ኢህአዴግ እውን የነፃነት ታጋይ ነበርን? ብለን መልሱን አዎን ካልን፤ በአሁን ሰዓት የሰላማዊ ትግል በር በመዘጋቱ ስርዓቱን በኃይል ለመጣል የታጠቁ ኃይሎችን እንዴት አሸባሪ እንበላቸው? ታጣቂዎቹን አሸባሪ የምንላቸው ከሆነስ፤ለዚህ ተግባር ግፊት በማድረግ በቀዳሚነት ተባባሪ የሆነው ራሱ ገዥው ስርዓት እጁ የለበትምን? ምላሹን ለራሱ ለኢህአዴግ አባላትና አመራሮች እንዲሁም ለህዝብ መተው ነው፡፡ ሌላው በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እጅግ በጠበበው መንገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉትን መሪዎች በተለይም ወጣቶችን በሽብር እየወነጀሉ ማሰሩስ ሽብርተኝነትን ትርጉም አልባ አያደርገውም ወይ? የሚለውንም መልሱን ለአንባቢው እተዋለሁ፡፡ በተለይ የሀገሪቱ ዜጎች የሆኑ በርካታ ጋዜጠኞች እና ብሎገሮችስ እስካሁን በተፈረደባቸውም ይሁን ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያሉ ተጠርጣሪዎችን አሸባሪ ብሎ መፈረጅ በፍትህ ስርዓትና በአሰቃቂ የሽብርተኝነት ድርጊት ላይ መቀለድ ይመስላል፡፡ ስለዚህ የነፃነት ትግልና ጋዜጠኝነት ከሽብርተኝነት ጋር ምንም ቁርኝትም ሆነ ግንኙት ስለሌላቸው ተለይተው መታየት አለባቸው፡፡ ለገዥዎች በስልጣን ለመቆየት አስጊ ተደርገው የተገመቱ ተዋናዮች እና ድርጊቶች የሀገሪቱና የዜጎች ስጋት ተደርገው ሊወሰዱ አይገባም፡፡
በአንፃሩ በሽብርተኝነት የተፈረጁ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የተፈረደባቸው ግለሰቦች ፍላጎታቸው፣ ዓላማቸውና ግባቸውን ህዝቡ እውነታውን ያለማንም ጣልቃ ገብነትና ቅንብር ተረድቶ ፍርዱን እንዲሰጥ ነፃና ገለልተኛ መድረክ መኖር ነበረበት፡፡ አለበለዚያ የገዥ ቡድኖችን ፍላጎትና ፍርሃት በማንፀባረቅ ዜጎችን አሸባሪ ማለቱ ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ ከ1928-1935 ዓ.ም. ድረስ በፋሽቱ ጣሊያን ወረራ ወቅት ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ብሎም ለራሳቸው ነፃነት ሲታገሉ የነበሩ አርበኞች አሸባሪ ተብለው በወቅቱ በነበረው የጣሊያን ገዥ ስርዓት በተቋቋመው ነፃና ገለልተኛ ባልሆነው ፍርድ ቤት እንደነ ሰማዕቱ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ያሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ስለዚህ የነፃነት ታጋዮችን አሸባሪ የምንል ከሆነ የቀድሞ የሀገራችን አርበኞች እና ኔልሰን ማንዴላ ዛሬም ድረስ አሸባሪዎች ናቸው ልንል ነው፡፡ እነሱን እና አሁን በስልጣን ላይ ያለውን የኢህአዴግ አመራሮችን የነፃነት ታጋይ የምናደርግ ከሆነ ደግሞ፤ አሁን ለሀገራቸው፣ለህዝባቸውና ለራሳቸው ነፃነት የሚታገሉትን፣ ያመኑበትን እውነት በአደባባይ የሚናገሩ ዜጎችን ወንጀለኛ ማድረግ በየትኛውም አመክንዮ (Logic) ተቀባይነት ይኖረዋል ማለት አይቻልም፡፡
ሌላው ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ተቋም ወይም ፍርድ ቤት አለመኖር ደግሞ ገዥዎችንም ነገ ፍትህ ሊያሳጣ እንደሚችል ካለፈው የደርግ ስርዓት መማሩ ተገቢነት አለው፡፡ የግብፁ ፕሬዘዳንት የነበሩትና በህዝባዊ አመፅ ከስልጣን የተወገዱት ሆስኒ ሙባረክ በቻሉት መጠን ነፃና ገለልተኛ ፍርድ ቤትና መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የፀጥታ ኃይል በመገንባታቸው በአስተዳደር ዘመናቸው በፈፀሙት ግፍ በክብር ታስረው ተገቢው ፍትህ ከማግኘት አላገዳቸውም፡፡ በአንፃሩ በዕድሜ ዘመናቸው ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርዓት መገንባት ያልቻሉት የሊቢያው ሙዓሙር ጋዳፊ ግን ከክብር ቤተመንግስታቸው ወጥተው ለፍትህ እንኳ ሳይቀርቡ እንደ ጎዳና ውሻ ከተደበቁበት ከፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ አሰቃቂ ሞት የታደጋቸው ፖሊስ፣መከላከያ ሰራዊትም ሆነ የደህንነት ኃይል አልነበረም፡፡
በፍትህ መቀለድ መዘዙ ዛሬ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ብለው የጠረጠሩትን ዜጋ ለማጥቃት ብቻ ሳይሆን ነገ ገዥዎች በድንገት ከስልጣን ሲወርዱ የሚጠብቃቸው ተመሳሳይ ከመሆን አያድንም፡፡ ስለዚህ ነፃና ገለልተኛ የፍትህ ስርዓት፣ የፖሊስና የፀጥታ ኃይል መገንባት ጠቀሜታው ነገ ለራስም ጭምር ከስልጣን ውጭ በህይወት ለመቆየት ትልቅ ዋስና ስለሚሆን ከወዲሁ መንቃቱ ብልህነት ነው፡፡ አለበለዚያ በቆፈሩት ጉድጓድ መቀበር አይቀርም የሚለው ተረት እንዲሰምር መስራት ዳፋው ለሁሉም መትረፉ ስለማይቀር ቢዘገይም ቢታሰብበት መልካም ነው፡፡ ምክንያቱም ለሌላው ተብሎ የሚሰራው ክፉም ሆነ መልካም ነገ ለራስ መትረፉ አይቀርምና፡፡ ይህ ሁሉ እየተከናወነ ያለው የኢህአዴግ አስኳልና ዋነ ዘዋሪው ህወሓት ራሱ የመጣበት መንገድ በአሸባሪነት ስለሆነ ሁሉም እንደራሱ ስለሚመስለው ያንኑ ሽብር ተግባር በከተማም እየደገመው ይገኛል፡፡ ይሄ ደግሞ ይዋል ይደር እንጂ ምናልባትም በቅርቡ ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሌላው ዓለም በተለየ ህጋዊ ሽፋንን አስመስሎ የሚጠቀም አሸባሪ መንግስታዊ ቡድን መኖሩን ለኢትዮጵያውያን መንገር ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል እንዲሉ፤ ኢህአዴግ በተለያየ የሀገሪቱ አካባቢ በተለይም በአዲስ አበባ በምርጫ 1997 ዓ.ም. ምርጫ ውጤትን ተከትሎ፣ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል አካባቢ ያለው የቀድሞ ትግራይ ሆቴል ላይ፣የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አጠገብ ታክሲ ውስጥ እና አዲስ አበባ ስታዲየም ላሊበላ አይቤክስ አካባቢ ራሱ የተለያዩ ቦንቦችን ማፈንዳቱን ከዊክሊክስና ከሀገሪቱ የደህንነት ምንጮችን መረጃ ማስታወሱ በቂ ነው፡፡ ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ለኢህአዴግ ነፃነት እንዲሁም የመብት ጥያቄን ማንሳት ወይንም የነፃነት ትግል ማለት ሽብር ነው፡፡ ይሄ ደግሞ ሌባ እናት ልጇን አታምንም እንዲሉ መሆኑ ነው፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ለእምነታቸው ዘብ ቆመው ዋሉ!
ከጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውና ሦስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው 32ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ከቀትር በኋላ በነበረው ውሎ የተለየ ክሥተት አስተናግዷል፡፡ ‹‹የሃይማኖት መቻቻል›› በሚል ርእስ በአጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተካሄደው ውይይት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ባለሥልጣናት ጋራ በተለይም በመቻቻልና በኢትዮጵያ የክርስትና ታሪክ ዙሪያ ሲከራከሩና በአንዳንድ ኹኔታዎችም ኤክስፐርቶቹን ሲገሥጹ ውለዋል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ÷ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ እንድርያስ÷ ከየአህጉረ ስብከታቸው ተጨባጭ ኹኔታና ከቀረበው ጽሑፍ እየተነሡ በመረጃ፣ በጥያቄና በትችት ስለ መቻቻል ጽሑፍ ያቀረቡ የሚኒስቴሩን ባለሥልጣናት ፈተና ላይ ጥለዋቸው አምሽተዋል፡፡ የሊቃነ ጳጳሳቱ ምስክርነት ‹‹የባዕድ እምነት አራማጆች በቤተ ክርስቲያንና በካህናት ላይ ልዩ ልዩ ተጽዕኖ እንደሚያደርጉና ሕገ መንግሥቱን የጣሰ ታላቅ ድፍረት እንደሚፈጽሙ›› ቀደም ሲል ለአጠቃላይ ጉባኤው የቀረቡ ሪፖርቶችን በገሃድ የሚያጠናክሩና የሚያጸኑ ናቸው፡፡
የሚኒስቴሩ አማካሪዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ቅሬታዎቹ በተጨባጭ ማስረጃዎች ተደግፈው በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በኩል ቢቀርቡላቸው መፍትሔ እንደሚሰጧቸው፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ከተገለጹት በላይ ያልተነገሩ ቅሬታዎች ስለመኖራቸው በየወረዳው ተዘዋውረው መረጃዎችን አሰባስበው ማረጋገጣቸውን አስታውቀዋል፡፡ በ‹‹ሕግ የተያዙት ጉዳዮች በሕግ እንደተያዙ ተጠብቀው እንዲቀጥሉ›› ለዚህም የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥንካሬ አስፈላጊ መኾኑን አሳስበዋል፡፡
የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ጥያቄ፣ አስተያየትና ትችት በከፍተኛ ጥሞና የተከታተለው የአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊ የሞቀ ድጋፉን ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህ የውይይት አጀንዳ አጋጣሚውን እንደ ምቹ ኹኔታ ለመጠቀም ያሰቡ የሚመስሉትና ልዩ ፍላጎት ያላቸው የሚመስሉት አቡነ ሳዊሮስ ውይይቱን ሳይጨርሱ አቋርጠው ሲወጡ ታይተዋል፡፡
‹‹አክራሪነት/ጽንፈኝነት የሚለው ቋንቋ እናንተ ናችኹ ያሰማችኁን፤ ከዚህ በፊት አይታወቅም፤ ዕድሜ ሰጥታችኁም ያበለጸጋችኋቸው እናንተው ናችኹ፡፡ አባቶቻችን የእረኛ ሰነፍ ከሩቅ ይመልሳል ይላሉ፤ በሩቅ መቅጨት ሲገባ ታሪካቸው እየተተረከ ብዙ አተራመሱት፤ [የአክራሪነት]መረባቸውን ከላይ ዘርግተዋል፤ መሬት አልነኩም ተባለ፤ መረባቸውን መሬት ዘርግተው፣ ሕዝብ እያተራመሱ ሙስሊሙ ራሱ እኛ አናውቃቸውም እያለ እየጮኸ እንዴት መሬት አልነኩም ይባላል? በእናንተ አነጋገር መሬት ሲነኩ እንዴት ሊያደርጉን ኖሯል? . . . ተቻቻሉ? እስከ ምን ድረስ ነው መቻቻል? ምንድን ነው መቻቻል? አሁን በወለጋ ያለው ኹኔታ መንግሥት በአገሩ ያለ ያስመስላል? ሰው እግሩን እሳት እየበላው ቻል ይባላል? እንድንቻቻል አድርጉን፤ እንችላለን!!›› /ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ፣ የሰሜን ወሎና ዋግ ኽምራ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
‹‹በምዕራብ ወለጋ ሀ/ስብከት በሦስት ወረዳዎች – ነጆ፣ ባቦ ገምቤል፣ ቤጊ – በፖሊቲካና የመናፍቃን አባላት የኾኑ ባለሥልጣናት በሥነ ልቡና ጦርነት ምእመኖቻችንን እየነጠቁን በደል አድርሰውብናል፡፡ አገሩ ለፕሮቴስታንት የተፈቀደና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አታስፈልግም የተባለ ነው የሚመስለው፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፣ የምዕራብ ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
‹‹ከዚህ በፊት በዚህ መድረክ ክቡር ዶ/ር ሽፈራው ተክለ ማርያም መጥተው ብዙ ነገር አስጨብጫቸው ነበር፤ ምላሽ አላገኘኹም፤ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታይቶ የማይታወቅ ነገር በጋሞጎፋ ሀ/ስብከት ተፈጥሯል፡፡ የደመራ በዓል በሚከበርበት ቦታ ላይ ምትክ ሳይሰጥ ተወስዶ ሱቅ በመከፈቱ ዘንድሮ በመቶ ወረዳዎች የደመራ በዓል ሳይከበር ሕዝቡ እያዘነ፣ እያለቀሰ ቤቱ ውሏል፡፡ በሴቻ ከተማ ባልተፈቀደ ቦታ ለስምንት ቀን ጉባኤ አዘጋጅተው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ጽላት፣ ቅዱሳን መላእክት እያነሡ ሲቃወሙ ነበር፡፡ ይህ ነዳጅ የተረከፈከፈበት ክብሪት ማለት ነው፡፡ ሕዝብ ሰልፍ እንውጣ ሲለን ሰላማችንን፣ ልማታችንን እንወደዋለን፤ መብታችንን በሕግ ነው የምንጠይቀው ብለን ከልክለናል፡፡ ጉባኤ ማካሄዳቸውን አንቃወምም፤ ግን ስማችንን ማንሣት ምን ማለት ነው? ይሄ ነው መቻቻል? እኛ ሌላውን አንነካም፤ ስንነካ ግን መብታችንን እንጠይቃለን፤ ቤተ ክርስቲያኗ መሬት መያዟን የወረዳው ባለሥልጣናት መሬቷን ቆርሳችኹ ጉባኤ አድርጉ ይላሉ፤ ይህን እንደ በቀል ነው የሚያዩት›› /ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፤ የጋሞጎፋና ደቡብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
‹‹በሶማሌ ክልል እስከ ቀበሌ ድረስ ባሉ የመንግሥት መሥ/ቤቶች ብዙ ሠራተኞች ምእመናን አሉ፡፡ ያሉን አብያተ ክርስቲያናት ግን አምስት ብቻ ናቸው፡፡ በየወረዳው ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ምእመናን ይጠይቃሉ፡፡ እስከ ክልሉ መስተዳድር ድረስ ለምእመናን የምንጮኸበት፣ መብታችንን የምናስከበርበት ኹኔታ ግን የለም፡፡. . .ምእመናን እምነታቸውን በካሴትና በዘመናዊ መሣርያ ካልኾነ እኛ ተንቀሳቅሰን ለማገልገል የምንችልበት ኹኔታ የለም፡፡ በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች የምእመናኑን ብዛት ዐውቀንና አጥንተን ያዘጋጀነው ስላለ የሚመለከተው ክፍል መፍትሔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን፡፡›› /ብፁዕ አቡነ ያሬድ፣ የሶማሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
‹‹ታሪክ ክፉ ይኹን ደግ እንደ ታሪኩ ነው የሚተረክ፤ ወንድማችን [ከዕለቱ የሚኒስቴሩ ሦስት ተናጋሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን] ይህን ታሪክ ስታቀርብ ምን ያህል ላይሰንስ አለኽ? ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ፤. . .ክርስትና በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው የሚለው ሌላ ጊዜ እንዳይደገም፣ ዛሬ ግራጁዌት አድርጉት፤ ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ክርስቶስ ካረገ ዓመት አልሞላውም፤ ገና ከኢየሩሳሌም አልተወጣም፤ ከሰው አይደለም ደግሞ ከእግዚአብሔር ነው የተቀበለችው፡፡ (የሐዋ.8÷26) ባለሥልጣን ሁሉ አገር የሚጠላ ምንድን ነው? በዓለም በትልቁ መጽሐፍ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፏል፤ በእግዚአብሔር ማመንንም የተቀበልን ከአይሁድ በፊት ነው፡፡ ታሪኩን አታዛቡ፤ ከዚህም ስትመጡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሠለጠነ፣ ቢቻል ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ የኾነ፣ በጳጳሳቱ ፊት ለመናገር የሚገባው መኾን አለበት፤ አታስቆጡን! . . .ቤተ ክርስቲያን እንግዳ ሲመጣ ሃይማኖትኸ ምንድን ነው አትልም፡፡ እግር አጥባ፣ አብልታ ነው፤ ግን ልታስተምሩን ስትመጡ ሳብጀክቱን ግራጁዌት አድርጋችኹ ኑ!›› /ብፁዕ አቡነ ማርቆስ፣ የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
‹‹. . .ችግሮቹ መፍትሔ አጥተው ቀርተዋል፡፡ ስድስት አድባራት ተቃጥለዋል፤ ሦስቱ በአንድ አካባቢ፣ ሦስቱ በተራራቀ ኹኔታ፡፡ ቢጮኽ የክልሉ መንግሥት አይሰማም፤ መልስም አይሰጠም፤ እንዲያውም ያስተባብላል፤ የተበደለ ሲናገር ፖሊቲካ ነው እያሉ ያተራምሱናል፤ ሐቅ ሲነገር ድብቅ የለውም፤ ሌትም ቀንም ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ፣ የሚጮኽበት እየታጣ ነው፡፡. . .የመንግሥት ሥልጣን የተረከቡ ወንድሞች የእኛን አንደበት ብቻ ነው እንዴ የሚጠብቁት? ለሌላው ብቻ ነው የቆሙት? ይህ የሰላም መደፍረስ አይደለም? መቻቻል የሚባለው አማርኛ ምንድን ነው? አማርኛ ነው እንዴ የምታመርቱት? በየቢሯቸው ሄጃለኹ፣ አንዱ እንደውም ተቆጣኝ፤ ይኸው ዘመን ተቆጥሯል፤ ዐርባ ዓመት ኾኗል፤ ለሕዝቡም ለመንግሥትም የምንኖረው እኛ ብቻ ነን፡፡ ለምንድን ነው በሽፋንነት የምትጠቀሙብን? ሁሉም ሲያጭበረብረን፣ ሲያታኩሰን፣ ሲያቃጥለን የሚኖረው መንግሥትን ሽፋን አድርጎ ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልን፡፡›› /ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ የደቡብ ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ/
ምንጭ፡- ሐራ ተዋህዶ